TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.44K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#GedeoZone : አቶ አብዮት ደምሴ በምክትል ማዕረግ የጌዴኦ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ሆነዉ ተሾሙ።

በአሁን ሰዓት የጌዴኦ ዞን ምክርቤት በዲላ ከተማ 4ኛ ዙር 9ኛ አስቸኳይ ጉባኤ እያካሄደ ይገኛል።

በዚሁ ጉባኤ አቶ አብዮት ደምሴ በምክትል ማዕረግ የጌዴኦ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ሆነዉ ተሹመዋል፤ ቃለመኃላም ፈፅመዋል።

@tikvahethiopia
#GedeoZone , #Yirgachefe 📍

ከያቤሎ ወደ አዲስ አበባ 65 ሰዉ ጭኖ ስጓዝ የነበረ የሰሌዳ ቁጥር ኦሮ 34983 የሆነ የህዝብ ማመላለሻ መኪና ተገልብጦ በሰዉና በንብረት ላይ ጉዳት ደረሰ።

አደጋው የደረሰው በጌዴኦ ዞን በይርጋጨፌ ወረዳ " ቆንጋ ቀበሌ " ነው።

በተከሰተው የትራፊክ አደጋ የ #ስድስት ሰዎች ህይወት ወዲያውኑ ሲያልፍ በ13 ሰዎች ላይ ከባድ አደጋ ደርሷል።

ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች በይርጋጨፌና ዲላ ሪፈራል ሆስፒታል የህክምና ድጋፍ እየተደረገላቸው ይገኛል።

የአደጋው መንስኤ እየተጣራ እንደሚገኝ የይርጋጨፌ ወረዳ ፖሊስ አሳውቋል።

@tikvahethiopia