TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.8K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#Mekelle መቐለ ያሉ ቤተሰቦቻቸው ያሉበትን ሁኔታ ለማየትና ለመጠየቅ እየተዘጋጁ ያሉ ዜጎች የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ መቐለ በቀን የሚያደርገውን በረራ ቁጥር እንዲጨምር እየጠየቁ ይገኛሉ። ሄርመን የተባለችና በአዲስ አበባ ነዋሪ የሆነች የቲክቫህ ኢትዮጵያ የቤተሰብ አባል፤ እናት እና አባቷ በመቐለ እንደሚኖሩ ገልፃ በረራ መጀመሩን በመስማቷ እጅግ ከፍተኛ ደስታ እንደፈጠረባት ገልፃለች። ትላንት…
#AddisAbaba #Mekelle

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በመቐለ ያለው የቴሌኮም መሰረተ ልማት እንደተስተካከለ በየዕለቱ የሚካሄደውን በረራ እንደሚያሳድግ አሳውቋል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰው ለጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት በሰጡት ቃል አየር መንገዱ የአውሮፕላን ችግር እንደሌለበትና በቀን አራትም፣ አምስትም በረራ ማድረግ እንደሚችል ገልፀዋል።

አቶ መስፍን ጣሰው ፤ " አሁን የተቸገርነው መቀለ የቴሌኮም አገልግሎት ስለሌለ የስልክ ግንኙነት እንኳን ማድረግ አልቻልንም። ከእዛ ለሚመለሱት እንኳን የ boarding pass እና የ baggage process እየተደረገ ያለው አዲስ አበባ ነው። የቴሌኮም ጥገናው እየተሰራ እንደሆነ አውቃለሁ፣ ስለዚህ ይህ እንደተስተካከለ እኛም በራራውን እንጨምራለን። " ሲሉ አሳውቀዋል።

" ይህ ምናልባት በመጪው #ሶስት እና #አራት ቀናት ሊስተካከል ይችላል። " ሲሉም አክለዋል።

በሌላ በኩል ከየአውሮፕላን ትኬት ዋጋ ጋር በተያያዘ 3 ሺህ የነበረው አሁን እስከ 9 ሺህ እየተሸጠ እንደሆነ ይነገራል ይህ ለምን ሆነ? ተብለው ለተጠየቁት ጥያቄ ምላሽ ሰጥተዋል።

" ዘጠኝ ሺህ የተሸጠው business class ነው " ያሉት አቶ መስፍን " የeconomy class ትኬት ቀድመው የገዙ ሶስት ሺህ ብር ገደማ ነበር፣ በአለም አቀፍ አሰራር መሰረት ትንሽ ዘግይቶ የሚገዛ ደግሞ ወደድ ይላል፣ አራት ሺህ ገደማ ገብቷል " ብለዋል።

ከዚህ ባለፈ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዛሬ ለበረራ የሚጠቀምበት አውሮፕላን 138 ሰው የሚጭን ቦይንግ 737 መሆኑን ጠቁመዋል።

" ወደፊት ፍላጎቶችን እያየን ከዛም በላይ የመጫን አቅም ያላቸውን አውሮፕላኖችን መጠቀም እንችላለን " ሲሉ ተናግረዋል።

#ኤልያስመሰረት

@tikvahethiopia
#ErmiasAyele

ኢትዮጵያዊው ሮም ላይ በባዶ እግሩ ሊሮጥ ነው።

ከቀናት በኃላ (እሁድ) የ2023 የሮም ማራቶን ይካሄዳል።

በዚህም ማራቶን ታሪክ ራሱን ይደግማል የተባለ ሲሆን ኢትዮጵያዊው የባዶ እግር ሯጭ እንዲሁም ለረጅም አመታት በኢትዮጵያ ታላቁ ሩጫ ቁልፍ ሰው (ዳይሬክተር) በመሆን የሰራው የ45 ዓመቱ ኤርሚያስ አየለ ሙሉ ማራቶን በባዶ እግሩ ይሮጣል።

ኤርሚያስ አየለ ይህንን የሚያደርገው ለኢትዮጵያው ታላቅ አትሌት አበበ ቢቂላ ክብር እንዲሁም ለሀገር ገፅታ ግንባታ ሲል ነው።

" አበበ ቢቂላ በኦሎምፒክ ጨዋታዎች የወርቅ ሜዳሊያ በማግኘት የመጀመሪያው ጥቁር በመሆኑ ለኢትዮጵያውያን አትሌቶች ብቻ ሳይሆን በአጠቃላይ ለአፍራካውያን ስኬት መሰረት ጥሏል " የሚለው ኤርሚያስ " ሆኖም ግን ለሰራው ታሪክ የሚገባውን ያህል እውቅና እንዳላገኘ ይሰማኝ ነበር " ብሏል።

ኤርሚያስ ፤ የአትሌት አበበ ቢቃላ ታሪክ ሁሌም እንደሚያነሳሳው ገልጾ ለዚህም እሱ ለአትሌቲክስ እና ለኢትዮጵያ ላደረገው ነገር ክብር እና ምስጋና ለመስጠት በተመሳሳይ ቦታ እና በተመሳሳይ መንገድ ታሪክ በሰራበት ቦታ በባዶ እግሩ እንደሚሮጥ አስረድቷል።

የሮም ውድድሩ  ቀላል እንደማይሆንና ስሜታዊም የሚያደርግ እንደሆነ የገለፀው ኤርሚያስ " ይህን ትልቅ ትርጉም ያለውና ታሪካዊ ውድድር ለማድረግ ዝግጅቴን አጠናቅቄያለሁ " ብሏል።

ኤርሚያስ ውድድሩን ከ3:30 እስከ 4:00 ባለው አጠናቅቃለሁ ብሎ እንደሚጠብቅ  ገልጾ የሮሙ ማራቶን በመጪዎቹ 18 ወራት ከአበበ ቢቂላ ጋር በአንድም ይሁን በሌላ መልኩ ግንኙነት ባላቸው በአቴንስ ፣ ቶኪዮ እና ፓሪስ ማራቶን በባዶ እግር ለሚያደርገው የማራቶን ሩጫ ትልቅ እገዛ እንደሚያደርግለት አመልክቷል።

የባዶ እግር የማራቶን ሩጫው አትሌት አበበ ቢቂላ ለሰራው ታሪክ ክብር ለመስጠት ከማድረግ ባለፈ ለሀገር ገፅታ ግንባታ ያለው አስታዋፆ ከፍተኛ ስለመሆኑ ገልጿል።

ኤርሚያስ ከዚህ ቀደም የታላቁ ሩጫን ሙሉውን ሁለት ጊዜ ፤ የሀዋሳ ግማሽ ማራቶን ሙሉ በባዶ እግሩ የሮጠ ሲሆን ለእሁዱ የሮም ማራቶን ዝግጅት ሲያደርግ ቆይቷል። 

ኤርሚያስ አየለ በሮም ስለሚያደርገው የባዶ እግር የማራቶን ሩጫ የውጭ መገናኛ ብዙሃን ያዘጋጁት ዘገባዎች ፦

https://www.aipsmedia.com/aips/pages/articles/2023/33598.html

https://www.aipsmedia.com/aips/pages/articles/2023/33598.html

Credit 👇
#ኤልያስመሰረት #ሀይለእግዚአብሔር_አድሃኖም

@tikvahethiopia