TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
62.8K photos
1.61K videos
216 files
4.36K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
አልቀመስ ያለው ኑሮ!

ለዓመታት በአገሪቱ የታየው የምግብ ሸቀጦች ዋጋ መናር ዕለት ተዕለት እየጨመረ መጥቶ፣ የሚሊዮኖችን ህልውና #በመፈታተን ላይ ይገኛል። የምግብ ነክ ሸቀጦች የዋጋ ግሽበት፣ የምንዛሬ እጥረት፣ የትምህርት ቤት ክፍያዎች ማሻቀብና ሌሎችም ማኅበረሰቡን ሰቅዘው ከሚገኙት ችግሮች መካከል የሚጠቀሱ ናቸው። የገንዘብ የመግዛት አቅሙ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያሽቆለቆለ ሲሔድ እንጂ ከወቅቱ የገበያ ሁኔታ ጋር ሲጣጣም አይታይም።

ዕድሜው በ30ዎቹ መጨረሻ ላይ የሆነው ተዘራ ዓለምነው ነዋሪነቱ አዲስ አበባ ውስጥ ነው። ዘወትር ከታዛው ሥር የሦስት ሕፃናት ልጆቹ ከርታታ ዓይኖች ይጠብቁታል። ወጣት ነው፤ ግን ቋሚ ሥራ የለውም። በሥራ አመራር የትምህርት ዘርፍ በዲፕሎማ የተመረቀ ቢሆንም ቅሉ፣ በቀን ሠራተኝነት በሚያገኘው አነስተኛ ገቢ ኑሮን ለመግፋት ይታትራል። የኑሮው ውድነት ግን ፈፅሞ አልገፋ ያለው ይመስላል።

“ከወራት በፊት 14 ብር ይሸጥ የነበረው ሽንኩርት 28 ብር ገብቷል፣ 70 ብር የሚሸጠው ዘይት 95 ብር እየተሸጠ ነው፣ ኩርማን የምታክል ዳቦ በ3 ብር መግዛት ከጀመርን ወር ሆኖናል፤ ጤፍ 2300 ብር እንገዛው የነበረው 3500 ብር እየተባለ ነው፤ ታዲያ በዚህ ዋጋ ገዝቼ ልጆቼን መመገብ እችላለሁ?” ሲል የሚጠይቀው የሦስት ልጆች አባት የሆነው ተዘራ፣ ልጆቹ የሚያስፈልጋቸውን ሳይሆን፣ ለመኖር የሚያበቃ አመጋገብ እየመገባቸው መሆኑን ይገልጻል።

/በአዲስ ማለዳ ጋዜጣ/

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-08-20-3