TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
በፍርድ ቤት ታሪክ የመጀመሪያው⁉️

የሰብዓዊ መብት ጥሰት በመፈፀም የተጠረጠሩ 36 ግለሰቦች ትናትና #ምሽት ፍርድ ቤት ቀርበዋል።

36ቱ ተጠርጣሪዎች የብሔራዊ መረጃና ደንህነት፤ የፌዴራል ፖለሲ ምርመራ ቢሮ፤ ከአዲስ አበባ ፖሊስ፤ ከፌዴራል ማረሚያ ቤቶች በስራ ሃላፊነትና በሰራተኛነት ሲያገለግል የነበሩ ናቸው።

ትላንት ከ11 ሰዓት እስከ ምሽቱ 3 ሰዓት 30 በኢትዮጵያ ፍርድ ቤቶች ታሪክ #ለመጀመሪያ ጊዜ ጉዳዩን የተመለከተው የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 10ኛው የወንጀል ችሎት ፖሊስ #ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር ያዋለበትን ምክንያት አድምጧል።

በቁጥጥር ስር ውለው ፍርድ ቤት ከቀረቡት ተጠርጣሪዎች መካከል 16 ከብሄራዊ መረጃና ደህንነት፣ ስድስቱ ከፌዴራል ፓሊስ ምርመራ ቢሮ፣ ሁለቱ ከአዲስ አበባ ፓሊስ ኮሚሽን፣ ስምንቱ ከፌዴራል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር ሲሆኑ፥ ሶስቱ ግለሰቦች ደግሞ ተጠርጣሪን በማስመለጥና #ሰነድ በማጥፋት የተጠረጠሩ ናቸው።

ተጠርጣሪዎቹ ያልተሰጣቸው ስልጣን በመጠቀም ሰዎችን የኦነግ፤ የአርበኞች ግንቦት ሰባት እና የተለያዩ የሽብር ቡድኖች አባል ናቹ በማለት ፊታቸውን በጥቁር ጨርቅ በመሸፈን በአንቡላንስ ጭነው በማይታወቅ ቦታ እስከ 1 ዓመት በማሰር የሰብዓዊ መብት ጥሰት በመፈፀም የተጠረጠሩ መሆናቸው ተገልጿል።

በተጨማሪም ከቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ቃጠሎ ጋር በተያያዘ በማረሚያ ቤት እየታረሙ የሚገኙና ተጠርጥረው ጉዳያቸው የሚከታተሉ ሰዎችን ወደ ሸዋሮቢት እንዲሄዱ በማድረግ በማረሚያ ቤቱ ጠባቂዎች ድብደባ እንዲፈፀም አድርገዋል ሲል ፖሊስ ለፍርድ ቤት አስረድቷል።

እንዲሁም ተጠርጣሪዎቹ ሴቶችን መድፈር፣ጥፍር መንቀል እና ሌሎች ኢሰብዓዊ ድርጊቶችን ሲፈፅሙ እንደነበረ ፓሊስ ገልጿል።

ተጠርጣሪዎቹ በተለይም ባልታወቀ ቦታ የሚያስሯቸውን ሰዎች ከአይን ማጥፋት ጀምሮ የተለያዩ የአካል ጉዳት እንዳደሩ ፓሊስ ከተጠቂዎቹ በተቀበለው የምስክርነት ቃል ማረጋገጡን አብራርቷል።

በዚህም የበርካታ ዜጎች የአካልና የስነ ልቦና ጉዳት እንደደረሰባቸው ነው ፓሊስ ለፍርድ ቤት ያስታወቀው።

ምርመራውን ለአምስት ወራት ሲያከናውን ቢቆይም ተጠርጣሪዎቹ በስራ ላይ የነበሩ በመሆኑ በዚህ መንገድ ጥቃት የደረሰባቸው ዜጎች የምስክርነት ቃላቸውን ለመስጠት ፍርሃት እንደነበረባቸው ፖሊስ ጠቁሟል።

ፓሊስ ተፈፅሟል የተባለውን ወንጀል ውስብስብ በመሆኑና የበርካታ ምስክሮችን ቃል ለመቀበል 14 ቀን የምርመራ ጊዜ ለፍርድ ቤቱ ጠይቋል።

ሁሉም ተጠርጣሪዎች የሰባዊ መብታቸው ተጠብቆ ውጪ ሆነው እንዲከታተሉ፤ ከአያያዛቸውና በሌሎቹ ጉዳዮች ለፍርድ ቤቱ ጥያቄ አቅርበዋል።

ፍርድ ቤቱም የሁሉንም ተጠርጣሪዎች የዋስትና መብት ውድቅ በማድረግ የ33 ተጠርጣሪዎች በጉዳዩ ያላቸው ተሳትፎ በተናጥል እንዲቀርብ በማድረግ የ14 ቀን የምርመራ ጊዜውን ፈቅዷል።

ሶስቱ ተጠርጣሪዎች መረጃ በማሸሽና ተጠርጣሪዎችን በመሰወር የተጠረጠሩ በመሆኑ ለሐሙስ ህዳር 6 2011 ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

ምንጭ፦ ፋና ብሮድካስቲንግ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በቅርቡ በሶስት የሀገራችን ከተሞች #ለመጀመሪያ ጊዜ #በአካል_ተገናኝተን በሰላም ጉዳይ እና በሌሎች ለሀገራችን እና ለህዝባችን ጠቃሚ በሆኑ ጉዳዮች ላይ የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት ውይይት እናደርጋለን።

የትኞቹ ከተሞች የሚለውን ሰሞኑን አሳውቃለሁ!!

ሰላም+ፍቅር+አንድነት=ኢትዮጵያ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#EBOLA ጎማ ከተማ ውስጥ #ለመጀመሪያ ጊዜ የኢቦላ በሽታ መገኘቱ ዛሬ ተሰምቷል። በነገራችን ላይ #ጎማ ምስራቅ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የምትገኝ ከተማ ስትሆን #የኢትዮጵያ_አየር_መንገድ በሳምንት 7 ጊዜ ወደ ከተማይቱ ይበራል።

Via ሸገር 102.1
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በ2012 ዓ.ም በዩኒቨሲርቲዎች፦

ለመጀመሪያ ዓመት ተማሪዎች 15 አዳዲስ ትምህርቶች ይሰጣሉ
• የዲግሪ ፕሮግራም አራት ዓመት ይሆናል

በ2012 ዓ.ም ወደ መንግሥትም ሆነ የግል ዩኒቨርሲቲዎች የሚገቡ አዲስ የመጀመሪያ ዓመት ተማሪዎች ትምህርት የሚጀምሩት በ15 አዳዲስ ትምህርቶች መሆኑን የከፍተኛ ትምህርት አግባብነትና ጥራት ኤጀንሲ አስታወቀ። በሦስት ዓመታት ይጠናቀቅ የነበረው የዲግሪ ፕሮግራም ወደ አራት ዓመት ከፍ ብሏል።

ዩኒቨርሲቲዎቹ በ2012 ዓ.ም ለመጀመሪያ ዓመት ተማሪዎች የሚሰጡት ክሪቲካል ቲንኪንግ፣ ሂስትሪ(ታሪክ) ኤንድ ዘሆርን፣ ጂኦግራፊ ኤንድ ዘሆርን፣ አንትሮፖሎጂ፣ ሳይኮሎጂ፣ ሂሳብ እና ሌሎቹም ለሁሉም የሚሰጡ የጋራ (ኮመን ኮርሶች ) ሲሆኑ ይህም ተማሪዎች በአስተሳሰብ ምጡቅ እንዲሆኑ፣ ብዝሀነትን፣ የሀገርን ባህል፣ አገር በቀል ዕውቀቶችንና ታሪክ እንዲያውቁ የሚያደርጉ ናቸው።

የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር ዶክተር አንዱአለም አድማሴ በተለይ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደገለጹት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የትምህርት ጥራት፣ ስነምግባር እና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮችን በሚመለከት የሀገሪቱ የትምህርት ስርዓት እንዴት ይቃኝ በሚለው ላይ ከ2007 ዓ.ም ጀምሮ በምሁራን ሰፊ ጥናት ሲደረግና በርካታ ህዝብም ሲወያይበት ቆይቷል። ይሄንኑ መነሻ በማድረግም ብዙ ማሻሻያ እና ለውጦች ተደርገዋል።

በዚሁ መሰረት በ2012 ዓ.ም #ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ዩኒቨርሲቲ ለሚገቡ ተማሪዎች አዳዲስ ኮርሶችን መስጠት እንዲችሉ ስምምነት ላይ ተደርሶ ለዚሁ ዝግጅት መደረጉን ጠቅሰው፣ አሁን ያለው ሁኔታ ትምህርቱን ለመጀመር የሚቻል ነው ብለዋል።

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ET-08-18

Via #EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በስፔን ባለፉት 24 ሰዓት የሰው ህይወት አላለፈም!

በኮሮና ቫይረስ በእጅጉ በተጎዳቸው ስፔን ውስጥ ከየካቲት ወር በኃላ #ለመጀመሪያ ጊዜ ባለፉት 24 ሰዓት በቫይረሱ ምክንያት የሰው ህይወት #አለማለፉን አሶሼትድ ፕሬስ ዘግቧል።

በአጠቃላይ በሀገሪቱ 286,718 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ሲረጋገጥ ከነዚህ መካከል 27,127 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል ፤ 196,958 ሰዎች በተደረገላቸው ህክምና አገግመዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#ASTU

አዳማ ሳይንሳና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ በታሪኩ #ለመጀመሪያ ጊዜ ለሁለት መምህራንና ተመራማሪዎች የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ሰጠ።

ዩኒቨርሲቲው የፕሮፌሰርነት ማዕረግ የሰጠው ለፕሮፌሰር አሰፋ አባሁና እና ለፕሮፌሰር አማን ደቀቦ መሆኑን ከኤፍ ቢ ሲ ያገኘነው መረጃ ይጠቁማል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የከፍተኛ ትምህርት መቁረጫ ነጥብ ይፋ ሆነ።

የ2013 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና ማለፊያ ነጥብ ፦

#ለመጀመሪያ_ዙር_ተፈታኞች !

👉 በመንግስት ዩኒቨርስቲዎች ለመማር

• ለተፈጥሮ ሳይንስ መደበኛ ተፈታኞት ማለፊያ ነጥብ ለወንድ 363 ለሴት 351

• በተፈጥሮ ሳይንስ በታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች ላሉ መደበኛ ተፈታኞች ለወንድ 351 ለሴት 339

• ለተፈጥሮ ሳይንስ መስማት ለተሳናቸው ሁለቱም ፆታ 300

• በተፈጥሮ ሳይንስ ድጋሜ ተፈታኞች ማለፊያ ነጥብ 380

🔹በግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ትምህርት ለመከታተል የተፈጥሮ ሳይንስ መቁረጫ ነጥብ 300

• ለማህበራዊ ሳይንስ መደበኛ ተፈታኞች ማለፊያ ነጥብ ለወንድ 264፣ ለሴት 254

• በማህበራዊ ሳይንስ በታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች ላሉ መደበኛ ተፈታኞች ለወንድ 254፣ ለሴት 250

• ለማህበራዊ ሳይንስ መስማት ለተሳናቸው ሁለቱም ፆታዎች 250

• በማህበራዊ ሳይንስ ድጋሜ ተፈታኞች ለሁለቱም ፆታ ነጥብ 280

🔹በግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ትምህርት ለመከታተል የማህበራዊ ሳይንስ መቁረጫ ነጥብ 250

#ለሁለተኛ_ዙር_ተፈታኞች !

👉 በመንግስት ዩኒቨርስቲዎች ለመማር

• ለተፈጥሮ ሳይንስ መደበኛ ተፈታኞት ማለፊያ ነጥብ ለወንድ 423 ለሴት 409

🔹 በግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ትምህርት ለመከታተል የተፈጥሮ ሳይንስ መቁረጫ ነጥብ ከ350

• ለማህበራዊ ሳይንስ መደበኛ ተፈታኞች በመንግስት ዩኒቨርሲቲ ለመማር የማለፊያ ነጥብ ለወንድ 317 ፣ ለሴት 305

🔹 በግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ትምህርት ለመከታተል የማህበራዊ ሳይንስ መቁረጫ ነጥብ ከ300 በላይ

(ተጨማሪ መረጃ ከላይ በምስሉ ላይ ተያይዟል - ያንብቡ)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update በደቡብ አፍሪካ የሚካሄደው የኢትዮጵያ መንግስት እና የህወሓት የሰላም ንግግር ዛሬ ተጀምሯል። የደቡብ አፍሪካ ፕሬዝዳንት ቃል አቀባይ ቪንሰንት ማግዌንያ ፤ የሰላም ንግግሩ እስከ እሁድ ጥቅምት 20 እንደሚዘልቅ አሳውቀዋል። ፕሬዝዳንት ራማፎሳ የደቡብ አፍሪካ መንግስት በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ መንግስት እና ህወሓት መካከል የሚካሔደውን የሰላም ንግግር እንድታስተናግድ በመመረጧ ክብር…
#AU

የ " ኢትዮጵያ መንግስት " እና የ " ህወሓት " ን የሰላም ንግግር በተመለከተ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ-መንበር የሆኑት ሙሳ ፋኪ ማህማት መግለጫ አውጥተዋል።

በመግለጫው ምን አሉ ?

- የኢትዮጵያ መንግስት እና ህወሓት #ለመጀመሪያ ጊዜ ፊት ለፊት የተገናኙበት የሰላም ንግግር ዛሬ በደቡብ አፍሪካ ተጀምሯል።

- በሰላም ንግግሩ ላይ የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ድርጅት (IGAD)
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (UN) ፣ የአሜሪካ መንግስት ተወካዮች በታዛቢነት እየተሳተፉ ነው።

- ደቡብ አፍሪካ የሰላም ንግግሩን ለማስተናገድ ፍቃደኛ ስለሆነች ለሀገሪቱ መንግስት እና ለፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፖሳ ምስጋና አቅርበዋል።

- ሙሳ ፋኪ ማሀመት የኢትዮጵያ መንግስት እና ህወሓት የኢትዮጵያን ጥቅም ባስጠበቀ ሁኔታ ሰላምን ለማስፈን እና ለግጭቱ ዘላቂ ፖለቲካዊ መፍትሄ እንዲገኝ ለማስረግ ባሳዩት ቁርጠኝነት ይበልጥ እንደተበረታቱ ገልፀዋል።

- የአፍሪካ ህብረት " የሰላም ንግግር " ተሳታፊ ወገኖች ኢትዮጵያ፤ በኢትዮጵያውያን ባለቤትነት እና በአፍሪካ ህብረት መሪነት ሰላም እንዲሰፍን ፣ የተረጋጋችና አንድነቷ የተጠበቀ እንድትሆን ህብረቱ ድጋፉን እንደሚቀጥል ቁርጠኛ መሆኑን ገልፀዋል።

@tikvahethiopia
ፎቶ፦ የፌዴራል መንግሥት እና የህወሓት የሰላም ስምምነት ኮሚቴ አባላት ለመጀመሪያ ጊዜ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ በተገኙበት መገናኘታቸው ተሰማ።

የሰላም ስምምነት ኮሚቴ አባላቱ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተገኙበት ለመጀመሪያ ጊዜ የተገናኙት በ " ሐላላ ኬላ " እንደሆነ ተነግሯል።

NB. ሐላል ኬላ የገበታ ለሀገር ፕሮጀክት አካል ነው።

ጠ/ሚር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ #ለመጀመሪያ ጊዜ ከሰላም ስምምነት ትግበራ አስተባባሪ ኮሚቴ ጋር ምክክር አድርገዋል ተብሏል።

በውይይታቸው እስካሁን በሰላም ስምምነቱ አፈፃፀም ዙሪያ የተከናወኑ ተግባራት መገምገሙና በቀጣይ ትኩረት በሚያስፈልጋቸው ጉዳዮች ላይ አቅጣጫ መቀመጡን ብሔራዊው የቴሌቪዥን ጣቢያ ዘግቧል።

@tikvahethiopia
ትምህርት ሚኒስቴር የመውጫ ፈተና ድጋሚ ተፈታኞች የምዝገባ ጊዜን አሳወቀ።

በ2016 ዓ/ም ሰኔ ወር ላይ የሚሰጠውን የመውጫ ፈተና በድጋሚ ለመውሰድ በመጠባበቅ ላይ የሚገኙ ተፈታኞች ምዝገባ የሚከናወነው ከግንቦት 14 እስከ 21/2016 መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል።

የምዝገባ ክፍያ 500.00 ብር በመክፈል በ https://exam.ethernet.edu.et በኩል መመዝገብ ይችላሉ ተብሏል።

የአገልግሎት ክፍያ  500.00 ብር በ ' ቴሌ ብር ' ብቻ የሚፈጸም መሆኑ አስገንዝቧል።

#ለመጀመሪያ_ጊዜ የመውጫ ፈተና የሚፈተኑ እጩ ተመራቂዎች ምዝገባ የሚካሄደው እና የአገልግሎት ክፍያ በተቋማቸው በኩል መሆኑን የገለጸው ሚኒስቴሩ አስፈላጊ የመፈተኛ መረጃዎችን በተቋማቸው በኩል እንደሚደርሳቸው አሳውቋል።

@tikvahethiopia