TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.44K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
13 ሰዎች በነብር ጥቃት ህይወታቸው አለፈ‼️

በህንድ 13 ሰዎች በነብር #ጥቃት ደርሶባቸው ህይወታቸው አለፈ።

የህንድ ባለስልጣናት 13 ሰዎችን #የገደለች ነብር #እንድትገደል ትዕዛዝ ሰጥተዋል፡፡

የ16 እድሜ እንዳላት የተነገረው ነብር ለሁለት ዓመታት ጫካው ለማውጣት ጥረት ሲደረግ መቆየቱን ነው የተነገረው፡፡

የእንስሳት መብት ተሟጋቾች ነብሯ እንዳትገደል ሰፊ ቅስቀሳ አድርገው እንደነበርና የሀገሪቱ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ነብሩ እንዲገደል ትእዛዝ አስተላልፎ እንደነበርም ተጠቁሟል፡፡

በቫንዳክዋዳ ከተማ ውስጥ በነሀሴ ወር ብቻ ሁለት የዘጠኝ ወር ነብሮች ሶስት ሰዎች መግደላቸውም ተጠቁማል፡፡

በአካባቢው የሚገኙ 5000 ሺህ ነዋሪዎች እንዳሉና ነብሮች በሚፈጽሙት ጥቃት በስጋት እንደሚኖሩ ተጠቁማል፡፡

ነዋሪዎቹ በአካባቢያቸው ሲንቀሳቀሱ በዚሁ ስጋት ሳቢያ በቡድን በመሆን ለመንቀሳቀስ መገደዳቸውን ለቢቢሲ ገልጸዋል፡፡

ምንጭ፦ ቢቢሲ
@tsegabwolde @tikvahethiopia