TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.7K photos
1.44K videos
207 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ከድሬደዋ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽን የተሰጠ መግለጫ⬇️

በድሬደዋ አስተዳደር ባሳለፍናቸው ጥቂት ቀናት በከተማው ግጭቶችና ሁከቶች ሊፈጠሩ ይችላሉ በሚል በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎችና የተለያዮ የህ/ብ ክፍሎች #የስጋት ሀሳቦች መመንጨታቸውን ተከትሎ ፖሊስ በወቅታዊ ጉዳይ ላይ መግለጫ መስጠቱ የሚታወቅ ነው::

ይህንንም ተከትሎ ፖሊስ ሌሎች የፀጥታ ሀይሎችና መላው ህብረተሰብ ባከናወናቸው ተግባራት ስጋቶቹን #እያመከነ በከተማው አሁን ላይ ያለው አጠቃላይ የፀጥታ ሁኔታ በአስተማማኝ ደረጃ ላይ እንዲገኝ ያደረገ ሲሆን ይህው የፀጥታ ሀይልና ህብረተሰብም ይህንኑ ሰላምና ፀጥታ አጠናክሮና የበለጠ አስጠብቆ በማስቀጠል ላይም ይገኛል። በዚህም ፖሊስ ለመላው የአስተዳደሩ ነዋሪና ወጣቶች ምስጋናውንም ያቀርባል።

ይህ ይሁን እንጂ ከፀጥታ ማስፈንና የህግ የበላይነት ከማረጋገጥ ተግባር ጋር ተያይዞ እያጋጠሙ ያሉና ሊታረሙ የሚገባቸው ጉዳዮች እንዳሉም ልብ ሊባል ይገባል።

በመሆኑም አሁን ላይ ያለውን ሰላምና ፀጥታ ወደ ላቀ ደረጃ በማሸጋገር የተጀመሩ የለውጥ ሂደቶች ለማስቀጠል ብሎም የትርምስና የብጥብጥ አላማ ያላቸውን ሀይሎች ከምንጫቸው ለማድረቅና እኩይ ተግባራቸውን ለማምከን ትኩረት መስጠትና ጥንቃቄ ማድረግ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ፖሊስ በሚከተሉት ጉዳዮች ላይ ክልከላ የተደረገ መሆኑን ያሳውቃል።

1ኛ:- ለፖሊስና ለፀጥታ ሀይሉ አሳዉቆ ተገቢውን ባጅና መለያ ሳያደርጉና ሳይዙ በቡድን ተደራጅቶ የጥበቃ እገዛ ሰጪነን ብሎ መንቀሳቀስ

2ኛ:-በተናጥልም ይሁን በቡድን የስለት መሳሪያዎችን ይዞ መንቀሳቀስ

3ኛ:-ከአስተዳደሩ የፀጥታ ምክር ቤትና ከሚመለከተው አካል ፍቃድ ሳያገኙ ህዝባዊ ስብሰባ ማካሄድ የተከለከለ መሆኑን #በጥብቅ ያሳስባል።

መላው የአስተዳደራችንም ነዋሪ ይህንኑ በመገንዘብና በመረዳት ለሰላሙና ለህግ የበላይነት መረጋገጥ እያደረገ ያለውን አስተዋፆና እያሳየ ያለውን እጅግ ከፍተኝ ትብብርና እገዛውን አጠናክሮ እንዲቀጥል ጨምሮ ፖሊስ ጥሪውን ያቀርባል።

መስከረም 12 ቀን 2011 ዓ.ም
የድሬደዋ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽን

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#UpdateSport የአውሮፓ ሊግ የፍጻሜ ጨዋታ በአዘርባጃኗ ዋና ከተማ ባኩ መካሄዱ ብዙ ቅሬታዎችን አስነስቷል።

የፊታችን ቅዳሜ የሚደረገው የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ የፍጻሜ ጨዋታ ላይ ለመታደም ብዙ እንግሊዛውያን ወደ ስፔኗ መዲና ማድሪድ እንደሚጎርፉ ይጠበቃል።

ነገር ግን ዛሬ የሚካሄደውን የአውሮፓ ሊግ የፍጻሜ ጨዋታ ለማየት ወደ አዘርባጃን መዲና ባኩ መምጣት የሚችሉት የአርሰናልና የቼልሲ ደጋፊዎች ቁጥር ከ6000 እንደማይበልጥ ተገልጿል።

ከዚህ በተጨማሪ የአርሰናሉ ሄነሪክ ሚኪታሪያን #በአርሜኒያዊ ዜግነቱ ምክንያት ደህንት አይሰማኝም በማለት ወደ አዘርባጃን እንደማይሄድ አስታውቋል። አርሜኒያ እና አዘርባጃን 'ናጎርኖ ካራባክ' የተባለው #ክልል የይገባኛል ፍጥጫ ውስጥ ያሉ ሲሆኑ የሚኪታሪያንም #የስጋት ምንጭ ይሄው ነው።

ብዙዎችም የፍጻሜ ጨዋታውን ለምን በአዘርባጃን ማካሄድ አስፈለገ? በማለት ቅሬታቸውን እየገለጹ ነው። የአውሮፓ እግር ኳስ ማህበር ግን ሃገሪቱ ለምስራቅ አውሮፓ ሩቅ በመሆኗ ምክንያት ውድድሩን ከማዘጋጀት ልትታገድ አይገባም ብሏል።

ባላት የነዳጅ ሃብት ምክንያት እጅግ የበለጸገችው አዘርባጃን ብዙ ሚሊዮን ዶላሮችን ፈሰስ በማድረግ በዓለማቀፍ ስፖርት ቤተሰቦች ዘንድ ያላትን ተቀባይነት ከፍ ለማድረግ እየሰራች ነው።

Via #ቢቢሲ
@tsegabwolde @tikvahethiopia