TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.8K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ስውር እስር ቤቶች በአዲስ አበባ‼️

በአዲስ አበባ ከሰባት(7) በላይ የሚደርሱ #የስውር እስር ቤቶች እንዳሉ ተሰምቷል። በሌሎችም የክልል ከተሞች የድብቅ ማሰሪያ ቤት እንዳሉ አቃቤ ህግ ተናግሯል፡፡

ወንጀል ሰርተዋል ተብለው የሰብዓዊ መብት የተጣሰባቸው ሰዎች #በአምቡላንስ ተጭነው እንደሚያዙ አይናቸውም ታስሮ በስውር ማረሚያ ቤት በድብደባ እንዲያምኑ እንደተደረገ በምርመራ መደረሱን የፌዴራል አቃቤ ህግ ተናግሯል፡፡

ይህም ከህገ መንግስቱ ጋር ሙሉ ለሙሉ የተጣረሰ እንደሆነ አቃቤ ህግ #ብርሃኑ_ፀጋዬ ተናግረዋል፡፡

የፖለቲካ ፓርቲ አባላት ተገደው እንዲወጡ ይህንንም ካላደረጉ ከፍተኛ ድብደባ እንደሚፈፀምባቸው ተሰምቷል፤ መሳሪያ እላያቸው ላይ ተተኩሷል፡፡

በሚስጥራዊ እስር ቤት የቆዩ ሰዎችም የተለያዩ ሰብዓዊ መብት #ጥሰት እና #የማሰቃየት ስራ ተደርጓል።

አካልን በኤሌክትሪክ ማንዘር የብልት ቆዳን በፒንሳ መሳብ፣ እስክሪቢቶ አፍንጫ ውስጥ መክተት፣ ጫካ ውስጥ ከአውሬ ጋር እርቃን ማሳደር፣ ምግብ መከልከል እና ሌሎችም የሰው ልጅ ለራሱ ዝርያ ማድረግ የማይገባውን የሰብዓዊ መብት ጥሰት መደረጉን የጠቅላይ አቃቤ ህግ በአምስት ወር የምርመራ ጊዜ አረጋግጫለው ብሏል፡፡

በዚህም ምክንያት ሴቶች እንደተደፈሩ በወንዶች ላይም የግብረሰዶም ጥቃት እንደተፈፀመ ጨለማ ውስጥም የቆዩ አይናቸው እንደጠፋ የተለያዩ መረጃዎች አስረድተዋል፡፡

ተጠርጥረዋል የተባሉት ኢትዮጵያውያን የራሳቸው ያልሆኑ የጦር መሳሪያዎች እና ሰነዶች ላይ በግድ እንዲፈርሙ በዚህ ሂደትም የተገደሉ እና የተሰወሩ መኖራቸው ታውቋል።

በዚህ መሰረትም ይህንን በደል የፈፀሙ ከፍተኛ የደህንነት መስሪያ ቤት ኃላፊዎች ለምርመራ ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡

ምንጭ፦ ሸገር 102.1
@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ጋዜጣዊ_መግለጫ : " በኢትዮጵያ እየጨመረ የመጣው ሰዎችን አስገድዶ የመሰወር (Enforced Disappearance) ድርጊት በአፋጣኝ ሊቆም ይገባል " - የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን @tikvahethiopia
#EHRC

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ( #ኢሰመኮ ) በተለይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በኢትዮጵያ ውስጥ የተለያዩ አካባቢዎች እየጨመረ የመጣውን የአስገድዶ መሰወር (Enforced Disappearance) እና ተይዘው የሚገኙበት ሁኔታ ሳይታወቅ በእስር ላይ የሚገኙ (incommunicada Detention) ሰዎችን ጉዳይ ሲከታተል ከቆየ በኃላ ዛሬ መግለጫ አውጥቷል።

ኢሰመኮ ምን አለ ?

- በተለይ በአዲስ አበባ ከተማ፣ በኦሮሚያና በአማራ ክልሎች በርካታ የአስገድዶ መሰወርን ድርጊት የሚያቋቁሙ ድርጊቶች መከሰታቸውን ተረጋግጧል።

- አብዛኛውን ጊዜ የዚህ ድርጊት ሰለባ የሆኑ ሰዎች ከመኖሪያ ቤታቸው፣ ከሥራ ቦታ ወይም ከመንገድ ላይ የሲቪልና የደንብ ልብስ በለበሱ የመንግሥት ጸጥታና ደኅንነት ሠራተኞች ያለ ፍርድ ቤት የመያዣ ትእዛዝ ተይዘው ከታሰሩ በኋላ ወዳልታወቀ ስፍራ እየተወሰዱ እንዲሰወሩ የተደረጉ ሲሆን፣ ከፊሎቹ ከተወሰኑ ቀናት፣ ሳምንታት ወይም ወራት መሰወር በኃላ የተገኙ መሆናቸው የተገለጸ ቢሆንም፣ ሌሎች ይህ መግለጫ እስከተሰጠበት ጊዜ ድረስ በግዳጅ እንደተሰወሩ የቀጠሉ ናቸው፡፡

- ከተጎጂዎች መካከል የተወሰኑት ሲያዙ በወንጀል ተጠርጥረው የሚፈለጉ መሆኑ ተነግሯቸው ወደ መደበኛ ፖሊስ ጣቢያ ከተወሰዱ በኋላ የተሰወሩ ሲሆን ከፊሎቹ ደግሞ ምንም ሳይነገራቸው በጸጥታ ኃይሎች ተወስደው የተሰወሩ ናቸው፡፡

ምሳሌ ፦

#1

በአዲስ አበባ ከተማ ከሚያዝያ 24 ቀን 2015 ዓ.ም. ጀምሮ ባለው ጊዜ ውስጥ ብቻ በማስገደድ ተሰውረው ከነበሩ ሰዎች ውስጥ ከተለያየ የጊዜ መጠን መሰወር በኃላ ወደ ፌዴራል ፖሊስ ጣቢያ ተወስደው የተገኙ ሲኖሩ፣ አስገድደው በተሰወሩበት ወቅት በኦሮሚያ ክልል ሸገር ከተማ ውስጥ " ገላን " ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የሚገኝ የቀድሞው ልዩ ኃይል ካምፕ ውስጥ ተይዘው እንደቆዩ ለማወቅ ተችሏል። በአስገድዶ መሰወሩ ወቅት ተፈጽሟል ስለተባለ ተገቢ ያልሆነ አያያዝ ወይም #የማሰቃየት ተግባር ኮሚሽኑ ምርመራውን ቀጥሏል።

#2

በአማራ ክልል በባሕር ዳር እና በደብረ ብርሃን ከተማ የአስገድዶ መሰወር ሰለባዎች የሆኑ ሰዎችን ጉዳይ ኮሚሽኑ ሲከታተል ቆይቶ ነበር። ከነዚህም ውስጥ አንድ የሀገር መከላከያ ሠራዊት አባል " ከሠራዊቱ ከድቷል " በሚል በባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር ወረብ ቀበሌ ነዋሪ የሆኑት ወላጅ #አባቱን " ልጅህን አምጣ " በሚል ሚያዝያ 28 ቀን 2015 ዓ.ም. በግዳጅ ተወስደው ተሰውረው ከቆዩ በኋላ ግንቦት 16 ቀን 2015 ዓ.ም. ተለቀዋል፡፡

#3

አንድ የቀድሞ የ " ሶማሊ  ክልል  ልዩ  ኃይል " አባል ታኅሣሥ 6 ቀን 2015 ዓ/ም ከቀኑ 11፡00 ከቢሮ ተደውሎለት ለሥራ ጉዳይ ቢሮ እንዲመጣ ተጠርቶ ከሄደ በኋላ በዕለቱ ከምሽቱ 2፡00 ሰዓት ጅምሮ ስልኩ የተዘጋ ሲሆን ከዚያ ቀን ጀምሮ የት እና ምን ሁኔታ ላይ እንዳለ ለማወቅ አልተቻለም፡፡

#4

ከኦሮሚያ ክልል የተለያዩ ቦታዎች ቢያንስ #ሰባት ሰዎች የአስገድዶ መሰወር ድርጊት ሰለባ መሆናቸው ለኢሰመኮ አቤቱታ ቀርቦ ክትትል እየተደረገባቸው ነው።

ከእነዚህ መካከል በምዕራብ ወለጋ ዞን ጎቡ ሰዮ ወረዳ ነዋሪ የሆነ አንድ ሰው ይገኝበታል፡፡

ይህ ግለሰብ ግንቦት 24 ቀን 2014 ዓ.ም. በወረዳው ፖሊስ ከሌሎች ሦስት ጓደኞቹ ጋር ተይዞ ፖሊስ ጣቢያ ከገባ በኋላ ሰኔ 9 ቀን 2014 ዓ.ም. ከሌሎቹ ታሳሪዎች ተለይቶ ነቀምት ከተማ የሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ መዘዋወሩ ለቤተሰብ የተነገረ ቢሆንም ከዚያ ቀን ጀምሮ ያለበትን ቦታ እና ሁኔታ ማወቅ አልተቻለም፡፡

በተመሳሳይ የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) ማዕከላዊ ኮሚቴ አባልና የምሥራቅ ወለጋ ዞን የኦፌኮ አስተባባሪ የሆነ ሌላ ሰው ጥቅምት 8 ቀን 2015 ዓ.ም. ከቀኑ 10፡00 ሰዓት አካባቢ ላይ ከሚሠራበት መሥሪያ ቤት በመንግሥት #የደኅንነት_ኃይሎች ተይዞ ነቀምት ከተማ በሚገኘው የጸጥታ ቢሮ ውስጥ ታስሮ ከፍተኛ ድብደባ ደርሶበት እንደነበረና እጁ በሰንሰለት በመታሰሩ ምክንያት ከቤተሰብ የሚሄድለትን ምግብ ተቀብሎ መመገብ ሲያቅተው ሰዎች የተመለከቱት መሆኑን ለማወቅ ተችሏል።

ግለሰቡ ከጥቅምት 13 ቀን 2015 ዓ.ም. ጀምሮ ሊገኝ አልቻለም።

ቡራዩ በተለምዶ " አሸዋ ሜዳ " ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ ከሚገኘው መኖሪያ ቤቱ በኦሮሚያ ልዩ ኃይል ፖሊሶች ተይዞ በቡራዩ ወረዳ 3 ፖሊስ ጣቢያ በቁጥጥር ስር ውሎ የቆየ አንድ ሰው ከሁለት ወራት የፖሊስ ጣቢያ ቆይታ በኋላ አንድ ቀን ከምሽቱ 4፡00 ሰዓት አካባቢ (ቀነ በትክክል አልታወቀም) ከሌሎች እስረኞች ተለይቶ መወሰዱ የታወቀ ቢሆንም ፣ ከዚያን ቀን ጀምሮ ያለበትን ቦታ እና ሁኔታ ማወቅ አልተቻለም፡፡

ሚያዚያ 19 ቀን 2015 ዓ.ም. ከምሽቱ 2፡00 ሰዓት ላይ ቁጥራቸው ከሃያ ያላነሱ የሀገር መከላከያ ሠራዊት አባላት በሰሜን ሸዋ ዞን ፣ ሱሉልታ ወረዳ ፣ ለገጦ ቀበሌ ገበሬ ማኅበር ፣ ልዩ ስሙ " ረቡዕ ገበያ " ፣ 04 ቀበሌ ተብሎ ከሚጠራው ቦታ በመምጣት አንድ ሰው ይዘው የሄዱ ሲሆን፤ በማግስቱ ቤተሰቦቹ ታሳሪውን ለመፈለግ ወታደሮቹ ይኖሩበት ወደነበረው ደርባ ቶኒ፣ አበባ ልማት ካምፕ ቢሄዱም ወታደሮቹ የተያዘው ግለሰብ ያበትን ሁኔታ ሊያሳውቁ ፍቃደኛ አለመሆናቸውን፤ ይልቁንም ለመጠየቅ የሄዱ ሰዎች እስር እና ማስፈራርያ የደረሰባቸው መሆኑን ገልጸዋል። የተያዘው ግለሰብም እስከ አሁን ድረስ ያለበት ሁኔታ እና ቦታ ማወቅ አልተቻለም፡፡

(ሙሉ መግለጫው በዚይ 👉 https://t.iss.one/tikvahethiopia/78928?single ተያይዟል)

@tikvahethiopia