TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.8K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
አዲስ አበባ ፖሊ ስ‼️

በዓሉ በሰላም እንዲከበር የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች ለጸጥታ አካላቱ የተለመደ #ትብብሩን አጠናክሮ እንዲቀጥል የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ጥሪ አስተላልፏል።

ህብረተሰቡ የፖሊስ አገልግሎትን ለማግኘትም ሆነ #አጠራጣሪ ነገሮች ሲያጋጥሙ ጥቆማ ለመስጠት በ991 ወይም 816 ነፃ የስልክ መስመሮችን እና 011-1-11 01 11፤011-1-26 43 59 011-1 01 02 97 ፤011-8-69 88 23፤011-8-69 90 15 መጠቀም እንደሚቻል ኮሚሽኑ አሰታቋል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከአ/አ ወደ ወላይታ ዞን የገባው የኮቪድ-19 ታማሚ!

ባለፉት 24 ሰዓት ዉስጥ በአዲስ አበባ የኮሮና ቫይረስ በሽታ (COVID-19) ላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጎ የኮሮና ቫይረስ በሽታ እንዳለበት የተረጋገጠበት አንድ ዕድሜው 20 የሆነ ግለሰብ ትክክለኛ ባለሆነ መንገድ ተደብቆ ህብረተሰቡን ለአደጋ ሊያጋልጥ በሚችል መልኩ ቤተሰቦቹ ወደሚገኙበት ወላይታ ዞን ገብቷል።

ግለሰቡ ወደ ወላይታ ዞን ከገባ በኋላ በህብረተሰቡ ትብብርና በመንግስት በኩል በተደረገ ክትትል እንዲያዘ ተደርጎ ወደ ህክምና ማዕከል እንዲገባ ተደርጓል።

ግለሰቡ ወደ ወላይታ የመጣበትን ተሸከርካሪ በቁጥጥር ስር ለማዋል የሚመለከታቸው አካላት ከጸጥታ ኃይሎች ጋር በመተባበር ክትትል እያደረጉ የሚገኝ በመሆኑ ህብረተሰቡ የተለመደውን #ትብብሩን እንዲያደርግ የደቡብ ክልሉ ጤና ቢሮ ጥሪውን አስተላልፏል።

የኮሮና ቫይረስ ከተስፋፋባቸዉ የሀገሪቱ ክልሎች የሚመጡ የክልሉ ነዋሪዎች ራሳቸውን ከቫይረሱ ይበልጥ በመጠበቅ ለራሳቸው፣ ለቤተሰባቸው ፣ ብሎም ለአጠቃላይ ማህበረሰቡ ያላቸው ፍቅርና አክብሮት እንዲገልፁና ቫይረሱን በጋራ በመከላከል መደጋገፍ እንዲኖር ቢሮው ጥሪውን አቅርቧል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia