#FAKENEWS
የፈጠራ ወሬ ወይም FAKE NEWS አንባቢን ወይም አድማጭን ለማታለል ወይም ትክክለኛ መረጃ እንዳያገኝ ሆን ተብሎ የሚሠራጭ አሳሳችና የሃሰት ዜና ነው።
FAKE NEWS ወይም የፈጠራ ወሬ በተለይ አሁን አሁን ብዙ አድማጭና አንባቢ ከሚታወቁ የዜና ማሠራጫ ጣቢያዎች ይልቅ ከተለያዩ ማኅበራዊ መገናኛዎች ዜና በሚፈልግበት፣ በሚቃርምበትና ሃሣቡንም በሚያንሸራሽርበት ዘመን አደጋው ከፍተኛ ሆኗል።
FAKE NEWS ወይም የፈጠራ ወሬ በማኅበረሰብ ውስጥ መተማመንን ያሳጣል፤ መንግሥትና ሕዝብን፣ ሕዝብን ከሕዝብ ያጋጫል።
Via #VOA
@tsegabwolde @tikvahethiopia

በእነ ብርጋዴየር ጄኔራል ተፈራ ማሞ ክስ መመስረቻ ላይ ውሳኔ ለመስጠት ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጠ!
ከሰኔ 15ቱ የባሕር ዳር ጥቃት ጋር በተያያዘ በቁጥጥር ስር ያሉትን የእነ ብርጋዴየር ጄኔራል ተፈራ ማሞን ጉዳይ እየተመለከተ ያለው የባህርዳር እና አካባቢው ፍርድ ቤት በተጠርጣሪዎች ላይ ክስ ለመመስረት ወይም ተጨማሪ የጊዜ ቀጠሮ መስጠት የሚያስችል ውሳኔ ለመስጠት ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጠ። ፍርድ ቤቱ ውሳኔውን ከሁለት ቀናት በኋላ ለመስጠት ቀጠሮ ይዟል።
ከባሕሩ ዳሩ ጥቃት ጋር በተያያዘ በሶስት የተለያዩ መዝገቦች የተካተቱ ተጠርጣሪዎች ብዛት 61 ናቸው። በተጠርጣሪዎቹ ላይ ሲቀርብ የቆየውን የምርመራ የጊዜ ቀጠሮዎችን ሲፈቅድ የቆየው የባሕር ዳር ወረዳ ፍርድ ቤት ከሁለት ሳምንት በፊት ባስቻለው ችሎት የ15 ቀናት የክስ መመስረቻ ቀጠሮ ሰጥቶ ነበር። ፍርድ ቤቱ “በተጠርጣሪዎች ላይ የቀረበው የሰው እና የሰነድ ማስረጃ ለክስ በቂ ነው” በማለት ነበር ከዚህ በኋላ የምርመራ ጊዜ እንደማይፈቅድ በማስታወቅ መዝገቡን የዘጋው።
ጉዳዩን የያዘው መርማሪ ቡድን ግን “ምርመራዬን አላጠናቀቅሁም” በማለት ለባሕር ዳር እና አካባቢው ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቤት ብሏል። የተጠርጣሪ ጠበቆች “የጊዜ ቀጠሮ ይግባኝ የማይባልበት አሰራር ስለሌለው ፍርድ ቤቱ የመርማሪ ቡድኑን ጥያቄ ውድቅ ሊያደርገው ይገባል” ሲል ተቃውመዋል። ዛሬ ጉዳዩን ሲያከራክር ያረፈደው የባሕር ዳር እና አካባቢው ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሁለቱንም ወገኖች ክርክር መርምሮ ውሳኔ ለመስጠት ለነሐሴ 16 ቀን 2011ዓ. ም. ከሰዓት በኋላ ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቶ የዕለቱን የችሎት ውሎ ቋጭቷል።
Via #DW

በመሬት ናዳ የሰው ህይወት አለፈ!
በወላይታ ሶዶ ከተማ የተከሰተው ድንገተኛ የመሬት ናዳ የእናትና ልጅ ሕይወት መጥፋቱን ፖሊስ አስታወቀ። የከተማዋ ፖሊስ አዛዥ ኢንስፔክተር ወጋየሁ ዳና እንደገለጹት አደጋው የደረሰው እናትና ልጅ ከምንጭ ውሃ ለመቅዳት በሄዱበት በተከሰተ ናዳ ሕይወታቸው አልፏል።
አደጋው የተከሰተው ከጠዋቱ አንድ ሰዓት ገደማ በከተማው ድል በትግል ቀበሌ ሆርባቢቾ መንደር እንደነበርም አስረድተዋል። የአደጋው ተጎጂዎች ያሰሙትን ጥሪ ተከትሎ ፖሊስና የአካባቢው ማህበረሰብ ሟቾችን ለማትረፍ ጥረት አድርጎ እንደነበር ገልጸዋል። የሟቾቹ አስከሬን ለቤተሰቦቻቸው መሰጠቱንም አዛዡ ተናግረዋል።
ማህበረሰቡ በተለይም ከፍተኛ ዝናብ የሚጥልበትን ወቅት በመለየት ጥንቃቄ እንዲያደርግ ኢንስፔክተር ወጋየሁ አሳስበዋል። በወላይታ ዞን ኦፋና ኪንዶ ኮይሻ ወረዳዎች ሰሞኑን በተከሰቱ አደጋዎች በሕይወትና በንብረት ላይ ጉዳት አድርሷል።
ምንጭ፦ ኢዜአ

ጥቁር ለሊት!
ሞጣ ሁለት የቁርጥ ቀን ልጆቿን አጣች!
በሞጣ ከተማ አስተዳደር 01 ቀበሌ ውስጥ ነው አቶ መለሰ ማናየ እና አቶ አዱኛ አስማማው እንደተለመደው የሞጣን ሰላምና ጸጥታ ለመጠበቅ ወጥተው ነበር፡፡ ግን አልተመለሱም ከምሽቱ 4፡00 ሰዓት ሲሆን አቶ እንደግ እንየው የተባለ ህገ ወጥ መሳሪያ አዟዟሪን አገኙት ቁም ሲሉት መቆም አልቻለም፡፡ መሳሪያ መያዛቸውን ያረጋገጠው ገዳይ እንደገና እንየው ሁለቱንም ጸጥታ ስራ ላይ ያሉ ጓዶች በያዘው ሽጉጥ አውቶማቲክ በመተኮስ መታቸው፡፡ ሞቾችም ከወደቁ በኋላ ባደረጉት ተኩስ ገዳይ እንደገና እንየውን ገደሉት፡፡ ሶስት አስከሬን አንድ ቦታ ላይ በተመሳሳይ ሰዓት ተነሳ፡፡ የአቶ መለሰና የአቶ አዱኛ የቀብር ስነስርዓታቸው የከተማው አመራሮች የፖሊስ አባላት የሚሊሻ አባላትና ተክልል የተመደቡ ልዩ ሀይሎች እንዲሁም ወዳጅ ቤተሰቦቻቸው ባሉበት በሞጣ ደብረ ገነት ቅዱስ ጊወርጊስ ቤተ ክርስቲያን ከቀኑ6፡30 ላይ ተፈጽሟል፡፡ ለሁለቱም የሚሊሻ አባሎቻችን ለከፈሉት መስዋትነት እግዚ አብሔር ነፍሳቸውን በአጸደ ገነት ያስቀምጥልን እያልን ለቤተሰቦቻቸውና ለቅርብ ጓዶቻቸው መጽናናትን ተመኘን፡፡
ሞጣ ከተማ ኮሚኒኬሽን ቢሮ

#update የጎንደር ዩንቨርሲቲ በባዮ ቴክኖሎጂ መስክ በርካታ የምርምር ሥራዎችን ላበረከቱት ለዶክተር ሳሙኤል ሳህሌ የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ሰጠ፡፡
@tsegabwolde @tikvahethiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ቃና ቴሌቪዥን ተቀጣ!
የንግድ ውድድርና የሸማቾች ጥበቃ ባለስልጣን አስተዳደራዊ ችሎት ቃና ቴሌሌቪዥን አሳሳች የጥርስ ሳሙና ማስታወቂያ አስተላልፏል በሚል ከዓመታዊ ገቢው ላይ አምስት በመቶውን እንዲከፍል ሐምሌ 12/2011 ቅጣት ጣለበት።
የብሮድካስት ባለስልጣን ‹‹ሌሎች የጥርስ ሳሙናዎች በቂ አይደሉም፤ ለዚህም ነው ምርጫዬ ዳቦር ኸርባል የሆነው›› በሚል አረፍተ ነገር እናት እና ልጅ የሚነጋገሩበት ማስታወቂያ በጥናት ያልተረጋገጠ እና ለሌሎቹ ተወዳዳሪዎችም ፍትሃዊ ያልሆነ ነው በማለት አቤቱታ ማስገባቱን ተከትሎ ግንቦት 12/2011 በባለስልጣኑ አቃቤ ህጎች ክስ ተመስርቶበት ነበር። ባለስለጣኑ በማስታወቂያው ላይ ሙያዊ ጥናት በማካሄድ እና ማስታወቂያውን በማስረጃነት በማቅረብ አስረድቷል።
ከቃና ቴሌቪዥን ባሻገር የዳቦር ኸርባል የጥርስ ሳሙና አስመጪ ድርጅት ባለቤት አብዱራዛቅ ታከለ ፍትሃዊ ያልሆነ ማስታወቂያ አሰርተዋል በሚል በተመሳሳይ ከአመታዊ ገቢያቸው ላይ የአምስት በመቶ ቅጣት ተጥሎባቸዋል። ማስታወቂያውን ያዘጋጀው ቢ ሚዲያ እና የማስታወቂያ ድርጅትም በተመሳሳይ ከዓመታዊ ገቢው ላይ የአምስት በመቶ ቅጣት እንደተጣለበት የባለስልጣኑ የውሳኔ መዝገብ ያስረዳል። የቃና ቴሌቪዥን የህዝብ ግንኙነት ኀላፊ ኀይሉ ተክለ ሃይማኖት ለባለስልጣኑ ይግባኝ ሰሚ ችሎት ይግባኝ ማለታቸውን እና ውሳኔው ላይም ምንም አይነት አስተያየት መስጠት እንደማይችሉ ተናግረዋል።
Via አዲስ ማለዳ

#መተማ
የመከላከያ ሠራዊት ንብረት ናቸው የተባሉና በመተማ ዮሐንስ በኩል ጭነት ይዘው ወደ ሱዳን ሊሻገሩ ሲሉ እንዲቆሙ በተደረጉ አምስት ከባድ ተሽከርካሪዎች ላይ ምርመራ እየተደረገ መሆኑን የአካባቢው ፖሊስ ለቢቢሲ ገለጸ።
ትናንት ከሰዓት ከዘጠኝ ሰዓት በኋላ አምስት የመከላከያ ሠራዊት ከባድ ተሽከርካሪዎች ወደ ሱዳን ለመሻገር ሲሞክሩ መተማ ዮሐንስ ላይ በአካባቢው ማኅበረሰብ ታግደው እንዳያልፉ መደረጋቸውን በስፋት እያነጋገረ ይገኛል።
ከስፍራው የሚወጡ መረጃዎችና ፎቶግራፎች እንደሚጠቁሙት ጭነት የያዙት ከባድ ተሽከርካሪዎች ጥቂት በማይባሉ ሰዎች ተከበው መንገድ ዳር እንደቆሙና የአካባቢው ባለስልጣናትም ስለጭነቱ ህጋዊነት ለማወቅ የማጣራት ጥረት እያደረጉ መሆናቸውን ያመለክታሉ።
ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/Metema-08-19

የዘጠኙ ተጠርጣሪዎች ዋስትና ታገደ!
የደቡብ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በሀዋሳ ከተማና በሲዳማ ዞን የተለያዩ አካባቢዎች ተከስተው የነበሩ ሁከቶችን አስተባብረዋል ለተባሉ ዘጠኝ ተጠርጣሪዎች የስር ፍርድ ቤት የፈቀደውን ዋስትና አገደ። ፍርድ ቤቱ የእግድ ትዕዛዙን የሰጠው ፖሊስ ዋስትናውን በመቃወም ያቀረበውን የይግባኝ አቤቱታ በመቀበል ነው።
በእነ ታሪኩ ለማ መዝገብ የተጠረጠሩ ዘጠኝ ሰዎችን የጊዜ ቀጠሮ ጉዳይ ሲመለከት የቆየው የሀዋሳ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ለተጠርጣሪዎች የዋስትና መብት የፈቀደው ባለፈው አርብ ነሐሴ 10 በዋለው ችሎት ነው። ፍርድ ቤቱ እያንዳንዳቸው ተጠርጥሪዎች የ50 ሺህ ብር ዋስትና በማቅረብ ጉዳያቸውን በውጭ ሆነው እንዲከታተሉ ወስኖ ነበር።
በተጠርጣሪዎች ላይ ምርመራ በማካሄድ ላይ የሚገኘው ፖሊስ አርብ ዕለት ለደቡብ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት አቤቱታ በማስገባቱ ተጠርጣሪዎቹ ሳይፈቱ ቀርተዋል። አቤቱታውን ዛሬ የተመለከተው የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ለተጠርጣሪዎቹ በተፈቀደላቸው ዋስትና ላይ የእግድ ትዕዛዙን አስተላልፏል።
ፍርድ ቤቱ ግለሰቦቹ የተጠረጠሩበት ወንጀል የዋስትና መብትን የሚፈቅድ ወይም የሚከለክል መሆኑን ለማከራከር እና ለፖሊስ የተሰጠው የምርመራ ጊዜ በቂነቱን በመመርመር ብይን ለመስጠት ለነሐሴ 24 ቀን 2011 ዓ.ም ቀጠሮ ሰጥቷል። በሀዋሳ ከተማ እና በሲዳማ ዞን ተከስተው ከነበሩ ሁከቶች ጋር በተያያዘ በቁጥጥር ስር ከዋሉት ተጠርጣሪዎች መካከል የሲዳማ ሚዲያ ኔትዎርክ ዋና ስራ አስኪያጅ ጌታሁን ደጉዬ ፣ ምክትላቸው ታሪኩ ለማ እና የእዚሁ ጣቢያ የቦርድ አባል የሆኑት በላይ ባልጉዳ ይገኙበታል።

#update በአዲስ አበባ አማራ ወጣት ማህበር አዘጋጅነት የተሰናዳው የቡሄ፣ የሻደይ፣ አሸንድዬ እና የሶለን በዓል በጃን ሜዳ እየተከበረ ይገኛል።
Via Henok View
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Via Henok View
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"ዛሬ በሁሩታ ከተማና ባካባቢዉ ካሉ ቀበሌዎች ጋር የቡሄ በአልን #በጅራፍ ግርፍ በዚህ መልኩ አክብረናል።" መክብብ ከሁሩታ
@tikvahethiopia @tsegabwolde
@tikvahethiopia @tsegabwolde
ፎቶ📸በ2011 #አርባምንጭ ከቱሪስት ፍሰት ከ82 ሚሊዮን ብር በላይ ማግኘቷን ሸገር ራድዮ ዘግቧል። #ETHIOPIA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በከፍተኛ ትምህርት ዘርፍ የለውጥ ስራዎችን ማስጀመሪያ ውይይት መድረክ!
የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር በአገራችን የመጀመሪያውን የትምህርትና ስልጠና ፍኖተ ካርታ ከሶስት ዓመታት በላይ ከፈጀ የዝግጅት ምዕራፍ በኃላ ከ2012 የትምህርት ዘመን ጀምሮ ተግባራዊ ያደርጋል፡፡ ይህ ፍኖተ ካርታ አጥኚ ቡድን ተቋቁሞ የትምህርትና ስልጠና ስርዓቱ ያለበትን ሁኔታ ከፈተሸ ወዲያ የደረሰባቸውን ችግሮች ሊቀርፉ የሚችሉ የመፍትሄ ሃሳቦች የተካተቱበት ነው፡፡ ፍኖተ ካርታው እስከ 2022 ዓ.ም ድረስ የሚተገበር ሲሆን 2012 ዓ.ምም የመጀመሪያው የትግበራ ዓመት ይሆናል፡፡ ፍኖተ ካርታው በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ያሉ ችግሮችን ለይቶ መፍትሔዎችን አስቀምጧል፡፡
በፍኖተ ካርታ ዝግጅት ወቅት የተለዩ ችግሮች፦
•የሥርዓተ ትምህርት አዘገጃጀት ይዘትና ትግበራ ችግር
• የዩኒቨርስቲዎችዎች በተልዕኮ አለመለየት
• የትምህርት አደረጃጀት ችግር
• የህጎች፣ የአሠራሮችና ስታንደርዶች አለመኖርና አለመናበብ
• በቂና ብቁ የሰው ኃይልና የቁሳቁስ ግብዓቶች ከትምህርት መስፋፋቱ ጋር አለመጣጣም
• ዩኒቨርስቲ-ኢንዱስትሪ ትስስር ዝቅተኛ መሆን/አለመኖር
• የሲቪል ሰርቪሱ አለመዘመን - ሥልጠና መስክና የሥራ ገበያ አለመጣጠም
ሲሆኑ በዚህ ምክንያት የመጡ ችግሮች ደግሞ የሚከተሉት ናቸው፡፡
• የስነምግባር እና የሞራል ውድቀት
• ስርዓት አልበኝነትና ምክንያታዊ ያለመሆን
• የስራ ጠባቂነትና ጥገኝነት
• የወቅታዊ አገራዊና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮችን ያለማወቅና ያለመረዳት
• የተግባቦትና የመረዳዳት ችግር
• ዘመኑ የደረሰበት የቴክኖሎጂ እውቀትና ክህሎት ይዞ አለመገኘት
ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ET-08-19

New Year New Thinking
ከተነሱ የመፍትሄ ምክረ-ሃሳቦች፦
• የዩኒቨርስቲ ትምህርት ቆይታ 4 አመት እንዲሆን (ለኢንጂነሪንግ 5፤ ለሜዲሲን 6)፣ 2 አመት Masters, 4 ዓመት Ph.D.
Ministry of Science and Higher Education - Ethiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከተነሱ የመፍትሄ ምክረ-ሃሳቦች፦
• የዩኒቨርስቲ ትምህርት ቆይታ 4 አመት እንዲሆን (ለኢንጂነሪንግ 5፤ ለሜዲሲን 6)፣ 2 አመት Masters, 4 ዓመት Ph.D.
Ministry of Science and Higher Education - Ethiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የደቡብ ክልል የ2012 በጀት አለመጽደቅ ውዝግብ አስነሳ!
የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ክልል ምክር ቤት ላለፉት ስምንት ወራት መሰብሰብ ባለመቻሉ የክልሉን በጀት ያላፀደቀ ሲሆን የ2011 በጀት ላይ በመመስረት የአንድ ወር በጀት ብቻ ታስቦ መለቀቁ የዋጋ ግሽበትን ያላማከለ እና የዞን አመራሮችን ጫና ውስጥ የከከተ ነው ተባለ።
‹‹የተለቀቀው አንድ አስራ ሁለተኛ በጀት ያለፈው አመት ቀመር ላይ በመመስረቱ መደበኛ ስራዎችን ለማከናወንም ሆነ ለአስቸኳይ ወጪዎች በቂ አይሆንም፡፡ በተጨማሪም ገንዘቡ የግብር ከፋዩ ገንዘብ እንደመሆኑ ይህንን መከልከል አግባብነት የለውም›› ሲሉ የወላይታ ብሄራዊ ንቅናቄ (ወብን) የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ ተከተል ላቤና ገለፀዋል።
የክልሉ ፕሬስ ሴክሪታሪያት ኀላፊ ፍቅሬ አማን በበኩላቸው የመንግስት ሰራተኞችን ደመወዝ ለመክፈል፣ መደበኛ ስራዎችን ለማስኬድ እንዲሁም #አስቸኳይ ስራዎችን ለማከናወን ጊዜያዊ በጀቱ በቂ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ አክለውም ክልሉ የገቢ ግብር ማሰባሰብ ስራውን በማካሄድ ላይ መሆኑን ገልጸው የገንዘብ እጥረት አይኖርም ብለዋል፡፡
ምክር ቤቱ በየትኛውም አይነት ሁኔታ ተሰብስቦ መደበኛ ስራውን መስራት በአዋጅ የተሰጠው ተግባሩ ነው ያሉት የወብን የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ ይህንን ስራውን በተቀመጠለት ጊዜ ገደብ ማከናወን አለመቻሉም አግባብ አይደለም ሲሉ ይተቻሉ፡፡
#አዲስማለዳ
ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ET-08-19-2

የደብረ ታቦር (ቡሄ) በአል የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ም/ከንቲባ ኢ/ር ታከለ ኡማ በተገኙበት እየተከበረ ነው። #ETHIOPIA #AddisTV
@tsegabwolde @tikvahethiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ፎቶ📸የቡሄ ትውፊታዊ ስርዓት በከተማ አስተዳደሩ ቅጥር ጊቢ ውስጥ እየተካሄደ ይገኛል፡፡ ኢ/ር ታከለ ኡማ የጅራፍ ማጮህ ትውፊታዊ ክንውን አድርገዋል፡፡
Via MayorOfficeAA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Via MayorOfficeAA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የኢትዮጵያ አርታኢያን ማህበር #ዛሬ በይፋ ተመስርቷል። ማህበሩ ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ፣ የመረጃ ነጻነትና የመደራጀት መብቶች እንዲከበሩ የህግ፣ የፖሊሲና የማዕቀፎች እንዲሁም የአፈጻጸም ማሻሻያዎች እንዲስፋፉ ለማድረግ ያለመ ነው ተብሏል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሞሞና ኤፍ ኤም 96.4
የመቐለ ዩኒቨርሲቲ ማሕበረሰብ ተኮር የማሕበረሰብ ሬድዮ ጣብያ ሞሞና ኤፍ ኤም 96.4 የሙከራ ስርጭቱን ጀምረዋል። የሙከራ ስርጭቱ በኤፍ ኤም 96.4 ሜጋኸርዝ ወደ አድማጮቹ በመድረስ ላይ ይገኛል።

❤️ከ3000 በላይ አባል❤️
6710 ላይ የህፃናት የልብ ህክምናን ለማገዝ በተከፈተው ግሩፕ ላይ እስካሁን ከ3 ሺህ የሚበልጡ የቤተሰባችን አባላት ተቀላቅለውናል!! በሺዎች የሚቆጠር ገንዘበ እንደ አቅማችን አስተዋፆ እያደረግን እንገኛለን!! ሀገር ወዳድነት መገለጫው ይህ ነው!!
Screenshot ወደዚህ ግሩፕ👇
https://t.iss.one/joinchat/FCD9AhWFZJX_rX95-4rWNQ
እኔ ካለኝ ላይ አካፍያለሁ?? እናተስ??
ለአንድ መልዕክት የሚቆርጠው 1 ብር ብቻ ነው!!
በትንሹ 3 መልዕክት ይላኩ!
#አንድነት #ተስፋ #መተሳሰብ #ፍቅር #ቲክቫህ

እኛ አለንላችሁ!!
6710
❤️"ልባችን ከናተው ጋር ነው!"
❤️"እኔም የአቅሜን አረጋነሁ፤ እነሱም የኔ ልጆች ናቸው፤ እስከመጨረሻው እረዳለሁ"
❤️"ህመማቸው ህመሜ ነው"
❤️"1 ልብ በ1 ብር"
የቤተሰባችን አባላት፦
•በሀገራቸው ስም
•በባለቤታቸው ስም
•በልጆቻቸው ስም
•በፍቅረኛቸው ስም
•በሚወዷቸው ታዋቂ ሰዎች ስም
•በአባባሎች ... 6710 ላይ እንደ ዜጋ ሃላፊነታቸውን እየተወጡ ነው። እርሶስ?
ወደዚህ ግሩብ ግቡና እየሆነ ያለውን ተመልከቱ፤ ሀገር አለን የምንለው ለዚህ ነው። ሁሌም ለበጎ ስራ አብረን ስለቆምን!!

ዩኒቨርሲቲዎች የፌዴራል ተቋምነታቸው ሊረጋገጥ፤ የአካዳሚክ ነጻነታቸውም ሊከበር ይገባል!
አሁን ባለው ሁኔታ ዩኒቨርሲቲዎች የሚስተዋለው እንደ ፌዴራል ሳይሆን እንደ አንድ አከባቢ ተቋም የመንቀሳቀስ አዝማሚያ ፈር ሊበጅለትና የፌዴራል ተቋምነታቸው ሊረጋገጥ እንደሚገባ ተገለጸ፡፡ የአካዳሚክ ነጻነታቸው ተከብሮ እንዲሰሩ ማድረግ እንደሚያስፈልግም ተጠቁሟል፡፡
የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ተቋምም ምልከታው ተገቢና ሊታረም እንደሚገባው በመጠቆም፤ ዩኒቨርሲቲዎች የፌዴራል ተቋም ሆነው እንዲሰሩ እንደሚደረግና የአካዳሚክ ነጻነታቸው እንዲከበር የሚያስችሉ እርምጃዎችም እንደሚወሰድ አረግግጧል፡፡
በ2012 የትምህርት ዘመን ወደትግበራ የሚገባውን የትምህርት ፍኖተ ካርታ አስመልክቶ በሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴት አዘጋጅነት ዛሬ በሸራተን አዲስ በተካሄደው የባለድርሻዎች የውይይት መድረክ ላይ እንደተገለጸው፤ ዩኒቨርሲቲዎች በአደረጃጀታቸውም ሆነ በአሰራራቸው የፌዴራል ሳይሆን የአከባቢ ተቋማት መስለዋል፡፡
ከተማሪዎች ምደባ እስከ መምህራንና አስተዳደር አካላት ያለው እውነትም ይሄንኑ ያሳያል፡፡
ይህ ደግሞ በዩኒቨርሲቲዎች ለሚስተዋለው አለመረጋጋት ጭምር ምክንያት ስለሚሆን ሊታረም፤ ዩኒቨርሲቲዎችም የፌዴራል ተቋምነታቸው ሊረጋገጥ ይገባዋል፤ ሲሉ ተሳታፊዎች ጠይቀዋል፡፡
ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/et-08-19-3