የቡሄ በዓል ባህላዊና ሃይማኖታዊ ይዘቱን እንደጠበቀ በደቡብ ጎንደር ዞን ደብረ ታቦር ኢየሱስ ተራራ ላይ ተከበረ። በዓሉ ከትውልድ ወደትውልድ እንዲተላለፍ ከጎንደር፣ ከላል ይበላና መሰል የቱሪዝም ሃብቶች ጋር በማስተሳሰር ለቱሪስት መስህብ ለማዋል እየተሰራ መሆኑን የደብረ ታቦር ከተማ ከንቲባ አቶ አበባው እምቢአለ በበዓሉ ላይ ገልፀዋል።
Via #ENA
ፎቶ፡ ዳኒ/TIKVAH-ETH/
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Via #ENA
ፎቶ፡ ዳኒ/TIKVAH-ETH/
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#UPDATE
የአቶ አብዲ ጠበቆች ይዘው የሚቀርቡትን የክስ መቃወምያ ለመቀበል ችሎቱ ዛሬ ረፋድ ላይ ቢሰየምም ጠበቆች ግን ሳይሰየሙ ቀርተዋል።
አቶ አብዲ ኢሌ በበኩላቸው ባለፈው ቀጠሮ ከተፈጠረው ሁኔታ በኋላ ተነጋግረናል መቃወምያውም በምን መልኩ መቅረብ እንዳለበት ስንመካከር ነበር ዛሬ ለምን እንዳልቀረቡ አላውቅም ብለዋል።
ችሎቱ ጠበቆች ያልተሰየሙበትን ምክንያት በፅሁፍ እንዲያስረዱና መቃወምያቸውን እስከ ነሀሴ 30 እንዲያቀርቡ ቢያዝም ብይኑን ግን ለ2012 ጥቅምት አሻግሮታል።
Via ሳምራዊት

#update የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አራተኛ ወንጀል ችሎት በቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ቃጠሎ ክስ በቀረበባቸው አራት እስረኞች ላይ የመጨረሻ የቅጣት ውሳኔ ለመስጠት ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጠ። ተከሳሾቹ “ክሱን እውቅና ሰጥተን የፍርድ ማቅለያ አናቀርብም” ሲሉ ተቃውሟቸውን አሰምተዋል።
ፍርድ ቤቱ ነሐሴ 1 ቀን 2011 ዓ. ም. በዋለው ችሎት በአራቱም ተከሳሾች ላይ የጥፋተኝነት ፍርድ ያሳለፈ በመሆኑ በዛሬ ውሎው የተከሳሾችን የቅጣት ማቅለያ ተቀብሎ የቅጣት ውሳኔ ይሰጣል ተብሎ ተጠብቆ ነበር። ሆኖም በዛሬው ችሎት ዳኞቹ ሰፋ ያለ ጊዜ የወሰዱት ተከሳሾች በባለፈው ችሎት ጥፋተኛ ሲባሉ ያሳዩት ተግባር ተገቢ እንዳልነበር በመምከር ነበር። ተከሳሾቹ “ወንበር መሰባበራቸውን እና ጥይት እስኪተኮስ ድረስ መረበሻቸውን” ዳኞቹ አስታውሰው ይህ ተገቢ አለመሆኑን በአጽንኦት ገልጸዋል።
የዛሬው የችሎት ውሎም ከወትሮው በተለየ ጠንከር ባለ ጥበቃ ስር የተከናወነ ነበር። በስፍራው የነበረው የዶይቼ ቬለ ዘጋቢ በችሎት አዳራሽ ውስጥ ብቻ 30 ፖሊሶች እንደነበሩ ተመልክቷል። የቅጣት ማቅለያ እንዲያቀርቡ በዛሬው የችሎት ውሎ የተጠየቁት አራቱ ተከሳሾች ጌታቸው እሸቴ፣ ፍጹም ጌታቸው፣ ሸምሱ ሰይድ እና አቶ ቶፊቅ ሽኩር “ባልፈጸምነው ወንጀል የጥፋት ማቅለያ አናቀርብም፤ የፈለጋችሁትን ፍረዱብን፤ የእውነት አምላክ ይፈርዳል” በማለት በቁጣ ሲናገሩ ተደምጠዋል።
ተከሳሾቹ “ድራማ” ሲሉ ለጠሩት ክስ “እውቅና” እንደማይሰጡም ለችሎቱ ተናግረዋል። “በዚህ ጉዳይ 159 ሰዎች ተከስሰን ነበር ግማሹ ከግንቦት 7 እና ኦነግ ጋር ተደራርድሮ ሲወጣ እኛ ድሆች ስለሆንን፤ የሚጮህልን የፖለቲካ ፓርቲ እና ሚዲያ ስለሌለ ብቻ ይሄው ታስረን ጥፋተኛ ለመባል በቅተናል” ሲሉም ለችሎቱ ተናግረዋል።
https://telegra.ph/ETH-08-19-2
Via #DW

በአቶ አብዲ መሐመድ ዑመር የክስ መዝገብ ስር የተከሰሱ ሰዎች ጉዳያቸው በሌሉበት እንዲታይ ተወስኗል!
የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት 4ኛ የወንጀል ችሎት በቀድሞ የሶማሌ ክልል ፕሬዝዳንት አብዲ መሐመድ ዑመር /አብዲ ኢሌ/ የክስ መዝገብ ተጠቅሰው ያልተገኙ 11 ተከሳሾች ጉዳያቸው በሌሉበት እንዲታይ ብይን ሰጠ።
በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ጥሪ ተደርጎላቸው ሳይቀርቡ በሌሉበት ጉዳያቸው እንዲታይ ከተበየነባቸው ተከሳሾች የክልሉ ልዩ ኃይል አዛዥ የነበሩት ጄኔራል አብዱራህማን አብዱላሂ፣ ሻለቃ ሼክ ሙክታር እና ሄጎ የተሰኘውን የአመፅ ቡድንን በምክትልነት ሲመሩ ነበር የተባሉት የወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ መሐመድ አህመድ ይገኙበታል።
ችሎቱ ከነዚህ በተጨማሪ በክስ መዝገቡ የመኖሪያ አድራሻ ተፈልገው ያልተገኙ ሌሎች 7 ተከሳሾችም እንዲቀርቡ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ጥሪ እንዲደርሷቸው ትዕዛዝ ሰጥቷል።
በተሻሻለው ክስ ላይ 1ኛው ተከሳሽ የቀድሞ የሶማሌ ክልል ፕሬዝዳንት አብዲ ዑመር ከጠበቆች ጋር ተማክሬ የክስ መቃወሚያ አቀርላሁ ብለዋል።
ጉዳያቸውን በአካል እየተከታተሉ ከሚገኙ 14 ተከሳሾች የተፋጠነ ፍትሕ ተጠቃሚ መሆን አልቻልንም፤ ጉዳያችንን ፍርድ ቤቱ በትኩረት ይመልከትልን በማለት አመልክተዋል።
እንደ ኢቢሲ ዘገባ ችሎቱ የክስ መዝገቡ በጋራ የሚታይ በመሆኑ የተከሳሾች የግል አቤቱታ የክስ መቃወሚያ እና ከሌሎች መሰል ጉዳዮች ጋር በተያያዘ የተጠቀሰውን ጊዜ ሊቆጠር ችሏል ብሏል፡፡
Via #EPA

#update በህገ ወጥ መንገድ ከአገር ሊወጣ የነበረ 8 ነጥብ 79 ኪሎ ግራም ወርቅና የተለያዩ የውጭ አገር የገንዘብ ኖቶች መያዛቸውን የጉምሩክ ኮሚሽን አስታወቀ። የጉምሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ደበሌ ቃበታ እንደገለጹት በቁጥጥር ስር የዋለው 8 ነጥብ 79 ኪሎ ግራም ወርቅ፣ 41 ሺህ ዩሮ፣ 55 ሺህ ሪያል እንዲሁም ሁለት ተሽከርካሪዎች ይገኙበታል።
በቁጥጥር ስር የዋለው በሶማሌ ክልል ሞምባስ ኬላ በኩል ከለሊቱ 10 ሰዓት ላይ በህገ ወጥ መንገድ ከአገር ሊወጣ ሲል መሆኑን ገልጸዋል። የተያዙት የኮንትሮባንድ እቃዎችና የገንዘብ ኖቶች ዛሬውኑ ለብሄራዊ ባንክ ገቢ መደረጋቸውንም ተናግረዋል። ባለፈው ሀምሌ ወር ብቻ 134 ነጥብ 3 ሚሊዮን ብር የሚገመቱ ኮንትሮባንድ የገቢና ወጪ እቃዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውንም አስታውሰዋል።
Via #ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በቁጥጥር ስር የዋለው በሶማሌ ክልል ሞምባስ ኬላ በኩል ከለሊቱ 10 ሰዓት ላይ በህገ ወጥ መንገድ ከአገር ሊወጣ ሲል መሆኑን ገልጸዋል። የተያዙት የኮንትሮባንድ እቃዎችና የገንዘብ ኖቶች ዛሬውኑ ለብሄራዊ ባንክ ገቢ መደረጋቸውንም ተናግረዋል። ባለፈው ሀምሌ ወር ብቻ 134 ነጥብ 3 ሚሊዮን ብር የሚገመቱ ኮንትሮባንድ የገቢና ወጪ እቃዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውንም አስታውሰዋል።
Via #ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#ኢትዮጵያ
የሚወደውን ሰው፣ አምላክ ይፈትናል
ቃሉም እውነት አለው፣ ያንቺ #ስቃይ በዝቷል
ፈተናሽም ታይቷል፣ ስቃይሽም በዝቷል
ኢትዮጵያ ሀገሬ፣ ምድራዊ ገነት
ለበጎ ይሆን ወይ፣ ያንቺ ስቃይ መብዛት
ያንቺ ስቃይ መብዛት
ያንቺስ ድህነት
ኋላ ቀርነት።
ታንፀን፣ በሰላም፣ #በተስፋ፣ በፍቅር፣ እምነት
ማለፍ እንድንችል ፣ ስንፍና ይውጣ ከቤት
እኛ ተቀምጠን ፣ ስለምን ወገኔ ይራባል
ጠንክረን ከሰራን ፣ ልመና ታሪክ ይሆናል
ያልተነካ ጉልበት ኦሆ ከቤት ተቀምጦ ኦሆ
ወገን ለምን ይለቅ ኦሆ በጠኔ ተውጦ ኦሆ
ልጅ አዋቂ ሳንል ኦሆ ሁላችን ባንድነት ኦሆ
እንውጣ ከችግር ኦሆ የሰው እጅ ከማየት ኦሆ
የያዝነውን ይዘን ኦሆ ተባብረን እንስራ ኦሆ
ስሟም ያገራችን ኦሆ በበጎ ይጠራ ኦሆ
ኢትዮጵያ
ኢትዮጵያ
ኢትዮጵያ
ኢትዮጵያ
ኢትዮጵያ
ቅድስት ሀገሬ፡ ኢትዮጵያ
የብሄር አምባ፡ መጠለያ
ታሪካዊት ናት፡ እናታችን
ሁሉም ሙሉ ነው፡ ከቤታችን
ዞር ብለን ለምን፡ እንይ ሌላ
እያለችን ዋርካ፡ መጠለያ
ይለወጥ ስሟ፡ ያገራችን
በስራ ጥረት፤ በክንዳችን
#MisikerAwol
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የሚወደውን ሰው፣ አምላክ ይፈትናል
ቃሉም እውነት አለው፣ ያንቺ #ስቃይ በዝቷል
ፈተናሽም ታይቷል፣ ስቃይሽም በዝቷል
ኢትዮጵያ ሀገሬ፣ ምድራዊ ገነት
ለበጎ ይሆን ወይ፣ ያንቺ ስቃይ መብዛት
ያንቺ ስቃይ መብዛት
ያንቺስ ድህነት
ኋላ ቀርነት።
ታንፀን፣ በሰላም፣ #በተስፋ፣ በፍቅር፣ እምነት
ማለፍ እንድንችል ፣ ስንፍና ይውጣ ከቤት
እኛ ተቀምጠን ፣ ስለምን ወገኔ ይራባል
ጠንክረን ከሰራን ፣ ልመና ታሪክ ይሆናል
ያልተነካ ጉልበት ኦሆ ከቤት ተቀምጦ ኦሆ
ወገን ለምን ይለቅ ኦሆ በጠኔ ተውጦ ኦሆ
ልጅ አዋቂ ሳንል ኦሆ ሁላችን ባንድነት ኦሆ
እንውጣ ከችግር ኦሆ የሰው እጅ ከማየት ኦሆ
የያዝነውን ይዘን ኦሆ ተባብረን እንስራ ኦሆ
ስሟም ያገራችን ኦሆ በበጎ ይጠራ ኦሆ
ኢትዮጵያ
ኢትዮጵያ
ኢትዮጵያ
ኢትዮጵያ
ኢትዮጵያ
ቅድስት ሀገሬ፡ ኢትዮጵያ
የብሄር አምባ፡ መጠለያ
ታሪካዊት ናት፡ እናታችን
ሁሉም ሙሉ ነው፡ ከቤታችን
ዞር ብለን ለምን፡ እንይ ሌላ
እያለችን ዋርካ፡ መጠለያ
ይለወጥ ስሟ፡ ያገራችን
በስራ ጥረት፤ በክንዳችን
#MisikerAwol
@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-EDU ላለፉት ወራት ተቋርጦ የነበረው የቋንቋ ትምህርት ቀጥሏል። ዛሬ የአፋን ኦሮሞ ቋንቋ 6ኛው ቀን ትምህርት ይቀጥላል።
√የትግርኛ
√ግዕዝ ትምህርቶችም እንዲቀጥሉ ይደረጋል!
በቋንቋ ትምህርት ላይ መሳተፍ የምትፈልጉ የቤተሰባችን አባላት መድረኩ ክፍት ነው። የኢትዮጵያን ቋንቋዎችና ባህሎች ለወንድሞቻችን እናስተምራለን፤ እንማማራለን ለምትሉ ሁሉ መድረኩ ክፍት ነው።
ሀገርን መውደድ የኛ የኢትዮጵያውያን ዜጎች የሆኑ ነገሮችን ከማክበርና ከመውደድ ይጀምራል!!
TIKVAH-EDU👇
https://t.iss.one/joinchat/AAAAAEWA_-Jt2zIM5COJqw

#ETHIOPIA
የሻደይ፣ አሸንድየ እና ሶለል በዓል በክልል ደረጃ ለሁለተኛ ጊዜ በባህርዳር ከተማ የፊታችን እሁድ እና ሰኞ ይከበራል። በዓሉ ከወዲሁ በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች ከነሃሴ 16 እስከ 18 ቀን 2011 ዓ.ም ድረስ የሚከበር ሲሆን፥ በደማቅ ሁኔታ ለማክበር የቅድመ ዝግጅት ስራዎች ማጠናቀቁን የአማራ ክልል ባህል እና ቱሪዝም ቢሮ አስታውቋል።
Via #FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የሻደይ፣ አሸንድየ እና ሶለል በዓል በክልል ደረጃ ለሁለተኛ ጊዜ በባህርዳር ከተማ የፊታችን እሁድ እና ሰኞ ይከበራል። በዓሉ ከወዲሁ በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች ከነሃሴ 16 እስከ 18 ቀን 2011 ዓ.ም ድረስ የሚከበር ሲሆን፥ በደማቅ ሁኔታ ለማክበር የቅድመ ዝግጅት ስራዎች ማጠናቀቁን የአማራ ክልል ባህል እና ቱሪዝም ቢሮ አስታውቋል።
Via #FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ABH ምላሽ ሰጠ!
“ኤጀንሲው ሕግን መሰረት ሳያደርግ ለፈጸመው ስህተት #ይቅርታ ይጠይቀን”–ዶ/ር ማርቆስ ፈለቀ/የኤቢኤች ዋና ሥራ አስፈጻሚ
.
.
ሰኞ ነሐሴ 13/2011 ዓ.ም. ቦሌ በሚገኘው የጅማ የኒቨርሲቲ የአዲስ አበባ ካምፓስ በተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ የኤቢኤች ፓርትነርስ ዋና ሥራ አስፈጻሚ የሆኑት ዶ/ር ማርቆስ ፈለቀ እንደተናገሩት “እኛ ሕግን ተከትለን እየሰራን ነው፤ ኤጀንሲውም በአዋጅ የተሰጠንን ስልጣን በፌስቡክ አይሽርም፤“ ብለዋል፡፡ “በመገናኛ ብዙሃን የተገለፀው ጉዳይም፣ የጅማ ዩኒቨርሲቲን ስም የሚያጎድፍና የተሳሳተ እንደሆነም” ዋና ሥራ አስፈጻሚው ይፋ አድርገዋል፡፡
የጅማ ዩኒቨርሲቲን እንደገና ለማቋቋም በወጣው የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ አዋጅ 240/2003 አንቀጽ ሶስትን ጠቅሰው የተናገሩት ዶ/ር ማርቆስ፣ “የዩኒቨርሲቲው ዋና ግቢ ጅማ ሆኖ በሌሎች ቦታዎች ላይ የትምህርት ክፍሎችና የምርምርና የሕብረተሰብ አገልግሎት ሊያቋቁም እንደሚችል” አብራርተዋል፡፡
Via #MollaMultimedia
ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ABH-08-19

የሶማሌ ክልል ምክር ቤት አስቸኳይ ጉባዔ ያካሂዳል!
የሶማሌ ክልል ምክር ቤት አራተኛ አስቸኳይ ጉባዔውን ነገ እንደሚያካሂድ የክልሉ ምክር ቤት ጽህፈት ቤት አስታወቀ። የጽህፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ አብዱረሺድ ዓሊ እንደገለጹት ምክር ቤቱ ለአንድ ቀን በሚቆየው ጉባዔ በሁለት ረቂቅ ዓዋጆች ላይ ተወያይቶ ያጸድቃቸዋል ተብሎ ይጠበቃል።
ምክር ቤቱ ከሚመለከታቸው ረቂቅ ዓዋጆች አንደኛው የክልሉን አስፈጻሚ አካላት እንደገና ለማደራጀት፣ተግባርና ኃላፊነታቸውን መወሰንን የሚመለከተው ነው። በተጨማሪም የሸሪዓ ፍርድ ቤቶችን እንደገና ለማቋቋም የተዘጋጀውን ረቂቅ ዓዋጅም መርምሮ ያጸድቃል ተብሎ እንደሚጠበቅ ኃላፊው አመልክተዋል።
ምንጭ፦ ኢዜአ

#update ሀዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ በስሩ ካሉ ኩባንያዎች ጋር በመተባበር ለ500 ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ። የቁሳቁስ ድጋፍ የተደረገላቸው የልማት ተነሺ ቤተሰብ ልጆች ሲሆኑ በእዚህም ቦርሳ፣ ደብተር እና የጽህፈት መሳሪያዎች ተበርክቶላቸዋል። ለወላጆችም ለትምህርት ቤት ማስመዝገቢያና ለተጓዳኝ ወጪዎች የሚሆን የገንዘብ ስጦታ መሰጠቱን ነው የገለጸው።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ቻይና እንደ ቢትኮይን ያለ ዲጂታል የኢንተርኔት የመገበያያ ገንዘብ ወይም ክሪፕቶከረንሲ ስራ ላይ ልታውል መሆኗን አስታወቀች፡፡ ለ5 ዓመታት ጥናት ሲደረግበት መቆቱንና ወደ ስራ ለማስገባት ዝግጅት መደረጉን ነው የሀገሪቱ ብሔረዊ ባንኩ ያስታወቀው፡፡ ስልክን በመጠቀም ያላንዳች ባንክ ገንዘብ ዲጂታል በሆነ መልኩ ለማንቀሳቀስ የሚያገለግለው ክሪፕቶከረንሲ በዓለም አቀፍ ደረጃ በስፋት ትኩረት እያገኘ መጥቷል፡፡
ምንጭ፡-ኢንዲፔንደንት/etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ምንጭ፡-ኢንዲፔንደንት/etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Audio
መተማ ስለተያዙት ተሳቢዎች በአካባቢው የሚገኙ የፀጥታ አካላት ምንም እንደማያውቁ ገለፁ!

የመተማ አካባቢ የመከላከያ አዣዥ ሳያውቅ ጥይት ጭነው ወደ ሱዳን ሊሻገሩ የነበሩ “የሠራዊቱ ንብረት ናቸው” የተባሉ አምስት የጭነት ተሽከርካሪዎች በፖሊስ ቁጥጥር ሥር ውለው ምርመራ እየተደረገባቸው መሆኑን የአማራ ክልል ልዩ ሃይል - ምዕራብ ጎንደር ብርጌድ አዣዥ ኮለኔል ሰለሞን አሻግሬ አስታወቁ።
መነሻና መድረሻቸው የት እንደሆነ ለጊዜው ያልተገለፀው አምስቱ ባለተሳቢ የጭነት ተሽከርካሪዎች ድንበሩን ከማለፋቸው በፊት መተማ ዮሃንስ ላይ የተያዙት የአካባቢው ወጣቶች መንገድ ዘግተው ካስቆሟቸው በኋላ መሆኑ ታውቋል።
ማንኛውም ድንበር የሚያቋርጥ የመከላከያም ሆነ ሌላ ማጓጓዣ እንቅስቃሴ መረጃ ወትሮ ቀድሞ እንደሚደርሳቸው ለቪኦኤ የገለፁት በአካባቢው የሚገኘው መከላከያ ሠራዊት የ33ኛ ክፍለ ጦር አንደኛ ብርጌድ፣ አንደኛ ሻለቃ አዛዥ ኮለኔል ሸዋገኝ አብዬ አሁን ስለተያዙት አምስት ተሽከርካሪዎች ግን የሚያውቁት ነገር እንደሌለ ተናግረዋል። ጉዳዩ በፖሊስና በመከላከያ ኃይሉና አጠቃላይ አካባቢው ላይ ባለ የፀጥታ ኃይል በጥምር እየተመረመረ መሆኑንም ሁለቱም አዛዦች ገልፀዋል።
Via #VOA

የ2019 የጤና እና ሥነ ህዝብ ዳሰሳ ቅድመ - ውጤት ይፋ ሆነ!
የ2019 የጤና እና ሥነ ህዝብ ዳሰሳ ቅድመ - ውጤት ይፋ ሆነ። በዚህም መሰረት እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር (እ. ኤ.አ) የ2019 ከ2016 የዳሰሳ ውጤት ጋር ሲነፃፀር አበረታች ውጤቶች ተመዝግበዋል።
🔷የቤተሰብ ዕቅድ አገልግሎት ተጠቃሚዎች ሽፋን ከ35% ወደ 41%
🔷አራተኛው የቅድመ ወሊድ ክትትል ሽፋን ከ32% ወደ 43%
🔷እናቶች በሰለጠኑ ጤና ባለሙያዎች የመውለድ ሽፋን ከ28%ወደ 50%
🔷የፔንታ ሶስት ክትባት አገልግሎት ሽፋን ከ53% ወደ 61%
🔷ከአምስት አመት በታች የህፃናት ሞት ቅነሳ ከ67 ወደ 55 ከ1000 ህፃናት
🔷ከአምስት አመት በታች የህፃናት የመቀጨጭ ምጣኔ ከ10% ወደ 7% የቀነሰ ሲሆን
ከላይ ለተገለጹት ውጤቶች መመዝገብ የጤና ባለሙያዎችና ባለድርሻ አካላት የጥረት ውጤት ሲሆን መሻሻል ባላሳዩት የጨቅላ ህፃናት ሞት ቅነሳ፣የሁሉንም አይነት ክትባት አገልግሎት ሽፋንና ከስነ - ምግብ ጋር የተያያዙ መለኪያዎች ላይ ትኩረት ሰጥተን በጋራ በመስራት የተሻለ ውጤት ማስመዝገብ ይገባል ሲል ጤና ሚኒስቴር ገልጻል።

#uodate የቀድሞው ጠቅላይ ሚንስትር አቶ መለስ ዜናዊን 7ኛ ዓመት መታሰቢያ አስመልክቶ ጉለሌ በሚገኘው መለስ ዜናዊ መታሰቢያ ፓርክ የችግኝ ተከላ መርሃ-ግብር ተከናውኗል፡፡
በመታሰቢያ ስነ-ስርዓቱ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የመለስ ዜናዊ ፋውንዴሽን ቦርድ ፕሬዝዳንት ወ/ሮ አዜብ መስፍን የቀድሞው የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚንስትር የአቶ መለስ ዜናዊን አጭር የህይወት ታሪክ አቅርበዋል፡፡
አቶ መለስ ዜናዊ በህይወት በነበሩበት ጊዜ ዓለም በአረንጓዴ ኢኮኖሚ መመራት እንዳለባት ያደረጉት ንግግር በተንቀሳቃሽ ምስል በመታሰቢያ ስነ-ስርዓቱ ላይ ቀርቧል፡፡
አቶ መለስ በዚህ ንግግራቸው ያደጉ አገራት ለምድሪቱ ስጋት የጋረጠውን የዓለም ሙቀት መጠን መጨመርን እንደ አፍሪካ ካሉ ታዳጊ አገራት ጋር በመሆን እንዲዋጉ ጠይቀው ነበር፡፡
በመቐለ ከተማም ለቀድሞው ጠቅላይ ሚንስትር አቶ መለስ ዜናዊ 7ኛ ዓመት መታሰቢያ ዛሬ ከሰዓት በኋላ የሻማ ማብራት ስነ-ስርዓት እንደሚካሄድ ይጠበቃል፡፡
Via #ETV

#update በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሰላማዊ የመማር ማስተማር ሂደት ለመፍጠር በየተቋማቱ የአካዳሚክ ነፃነት ሊኖር እንደሚገባ ምሁራን አሳሰቡ። የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር በበኩሉ ከዚህ በኋላ ሁሉም አካላት ተጠያቂ የሚሆኑበት አሰራር ተግባራዊ አደርጋለሁ ብሏል።
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መምህርና የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የቦርድ አባል ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ እንዳሉት፤ መንግስት በተማሪዎች ህብረት ስም ለፖለቲካ ጥቅም የሚያደርገውን እንቅስቃሴ ማቆም አለበት።
በዩኒቨርሲቲዎች ያሉ የተማሪዎች ህብረት የሚባሉ ማህበራት በቡድን ተድራጅተው ተማሪዎችን እርስ በእርስ ሲያጋጩ እንጂ መፍትሄ ሲያመጡ አላየንም ብለዋል ፕሮፌሰሩ። “በዩኒቨርሲቲዎች ሰላም ስለመደፍረሱ መስማት ያሳፍራል” ያሉት ፕሮፌሰር በየነ፤ መንግስትም ለተማሪዎች የአካዳሚክ ነጻነት ሊሰጣቸው ይገባል ነው ያሉት።

በአልሸባብ ላይ ጥቃት መፈፀሟን አሜሪካ ገለፀች!
ዛሬ በተካሄደ ድንገተኛ የአየር ላይ ጥቃት የአልሸባብ ታጣቂ ህይወት ማለፉን አሜሪካ ገልፃለች። በአፍሪካ የአሜሪካ የጦር አዛዥ ሜጀር ጀነራል ዊሊያም ጌለር እንዳስታወቁት ጥቃቱ የተፈፀመው ከሶማሊያ የመንግስት ወታደሮች ጋር በጥምረት ነው። በጥቃቱ በንፁሀን ዜጎች ላይ ጉዳት አለመድረሱንም የጦር አዛዡ አስታውቀዋል። በተከታታይ እየተፈፀመበት ባለው ጥቃት የተነሳ የአልሸባብ ነፃ እንቅስቃሴ መገታቱንም ተናግረዋል።
ዛሬ በሶማሊያ ቁንያ ባሮው በተባለ አካባቢ በተፈፀመ የአየር ላይ ጥቃት የአልሸባብ ታጣቂ ህይወት ማለፉንም ገልፀዋል። አሁን ላይ ከአል ቃይዳ ጋር ትሥሥር ያለው አልሸባብም ሆነ ሌሎች የታጠቁ ኃይሎች አቅም እየተዳከመ እንደሆነም ነው የተዘገበው። ባለፈው ሳምንት በሶማሊያ ታችኛው የሸበሌ ቀጣና አልሸባብ በመንግስት ወታደሮች መጠለያ ላይ በወሰደው እርምጃ 50 የመንግስት ወታደሮች መገደላቸውን፤ ለዚህም ኃላፊነት እንደሚወስድ መግለፁ ይታወሳል።
አልሸባብ ከ2007 (እ.አ.አ) ጀምሮ የሀገሪቱን #ያልተረጋጋ መንግስት ለመጣል እየተዋጋ የሚገኝ ታጣቂ ቡድን ነው። ለምስራቅ አፍሪካ ቀጣና ሥጋት ተደርጎ የተፈረጀውን ታጣቂ ቡድን ለማጥፋትም 20 ሺህ የሚሆኑ የአፍሪካ ኅብረት አባል ሀገራት ወታደሮች እና የተባበሩት መንግስታት ጥረት እያደረጉ ይገኛሉ።
ምንጭ፦ አልጀዚራ/AMMA

በተሽከርካሪ የጦር መሳሪያ ሲያዘዋውር የተያዘው ተከሳሽ በእስራት ተቀጣ!
ተከሳሽ አብዱራህማን ዩኑስ ከሚመከለተው የመንግስት ፈቃድ ውጪ ወደ ሀገር እንዳይገቡ ገደብ የተደረገባቸው የጦር መሳሪያዎችን በተሸከርካሪ ደብቆ ወደ ሀገር ሊያስገባ ሲል ተይዞ ዐቃቤ ሕግ በመሰረተው ክስ በእስራት ተቀጥቷል፡፡
ተከሳሽ 53 ቱርክ ስሪት ሽጉጦችንና 35 ሺህ 766 ጥይቶችን የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ 3-A50931 አ.አ በሆነ ላንድክሩዘር መኪና ደብቆ ወደ ሀገር ሊያስገባ ሲሞከር በተደረገው ክትትል በአዲስ አበባ የካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 14 ክልል ልዩ ቦታው ጣፎ አደባባይ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በተሸከርካሪው ላይ በተደረገ ፍተሻ ተይዟል፡፡
ተከሳሽ ክሱ በችሎት ተነቦለት እንዲረዳ ከተደረገ በኃላ ድርጊቱን ክዶ በመከራከሩ ዐቃቤ ሕግ እንደ ክሱ አቀራረብ ምስክሮች አሰምቷል፡፡ ፍርድ ቤቱም መዝገቡን መርምሮ ተከሳሽ ሽጉጥና ጥይት በመኪና ደብቆ በፍተሻ ስለመያዙ በመረጋገጡና መከላከልም ባለመቻሉ በተከሰሰበት ድንጋጌ ጥፋተኛ መሆኑን በይኗል፡፡
የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 8ኛ ወንጀል ችሎት መዝገቡን መርምሮ የግራ ቀኙን የቅጣት አስተያየት በመመልከት ተከሳሽ በ2 ዓመት ጽኑ እስራት እና በ5 ሺህ ብር መቀጮ እንዲቀጣ ወስኗል፡፡
ምንጭ፡- ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ

እገዳ የተጣለባቸው የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በዩኒቨርሲቲው የተላለፈውን ውሳኔ እንደሚቃወሙትና ተገቢ አለመሆኑን ገልፀዋል። የበላይ አካል ጉዳዩን ይወቅል፤ ችግራችንን ይረዳልን ሲሉም መልእክታቸውን አስተላልፈዋል፦
"ደብተር ይዞ ግቢውስጥ መንቀሳቀስ ለህይወት አስጊ ነበር፤ በለሊት በተኛንበት ፌደራል ፖሊስ ምንም መረጃ ሳይኖራቸው የዶርማችንን በር ሰብረው ተቀጥቅጠናል ይሄም ተማሪው ለብዙ ቀናት ከግቢ ውጪ እንዲያድር እና እስኪረጋጋ ሲጠብቅ ነበር፤ በጊዜው ኢንተርኔት ተዘግቶ ስለነበር ጩኸታችንን የሚሰማን አካል አላገኘንም። ከአንዴም ሁለቴም የተማሪውን የተስማማበትን ፊርማ አስገብተናል ግን ቀና ምላሽ አልተሰጠንም። በአጠቃላይ ውሳኔውን እንቃወማለን የበላይ አካል አቤት ይበለን።"