TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.4K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የቀዳማዊት እመቤት ፅህፈት ቤት ያስገነባቸው አራት ትምህርት ቤቶች በመስከረም ስራ ይጀምራሉ!

የአይነስውራን ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤትን ጨምሮ በቀዳማዊት እመቤት ፅህፈት ቤት ከሚገነቡት 21 ትምህርት ቤቶች ውስጥ አራቱ በነሀሴ ወር መጨረሻ ላይ ግንባታቸው ተጠናቆ ለመጪው ዓመት ተማሪዎችን የሚቀበሉ መሆኑ ተገለጸ፡፡

የጽህፈት ቤቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሙሉቀን ፈንታ በተለይ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደገለጹት፤ በኦሮሚያና አማራ ክልሎች የተገነቡትና ሊበን ጭቋላ፣ ጉጂ፣ ጃኮና ሎዛ ማርያምየተባሉት አራት ትምህርት ቤቶች ግንባታ ከ80 እስከ 87 ከመቶ የደረሰ ሲሆን በዚህ ክረምትም ግንባታቸው ሙሉ በሙሉ ተጠናቆ ወደ ስራ ይገባሉ፡፡

አራቱ ትምህርት ቤቶች በመጪው የትምህርት ዘመን ተማሪዎችን ተቀብለው ለማስተማር ዝግጅት እያደረጉ መሆኑን የጠቆሙት አቶ ሙሉቀን ለተማሪዎቻቸውም የደንብ ልብስና ቦርሳ የሚበረክትላቸው እንደሆነ ገልፀዋል፡፡

Via #EPA

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የመጀመሪያ ዓመት ኮርሶች👆በ2012 የትምህርት ዘመን በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የፍረሽማን መርሃ-ግብር ውስጥ በመጀመሪያውና በሁለተኛው ሴሚስተር የሚሰጡት ኮርሶች!

#share #ሼር
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከ50 በመቶ በላይ ወጣቶች የጫት ሱስ ተጠቂ ሆነዋል ተባለ!

የሴቶች ሕፃናት እና ወጣቶች ጉዳይ ሚኒስቴር ባሳፍነው ሳምንት ይፋ ባደረገው ጥናት በኢትዮጵያ ካሉ አዋቂዎች እና ወጣቶች መካከል 51 በመቶ የሚሆኑት ጫት ቃሚዎች መሆናቸውን እና ከዚህም ውስጥ የወንድ ጫት ቃሚዎች ቁጥር ከፍተኛው እንደሆነ ጥናቱ አመላክቷል።

ከከተሞች ይልቅ #በገጠራማ የኢትዮጵያ አካባቢዎች ጫት መቃም እንደበለጠ የገለጸው ጥናቱ፤ በተለይም በድሬዳዋ፣ ሐረር፣ ሶማሌ እና በአማራ ክልሎች ከሌላው የአገሪቱ አካባቢዎች በበለጠ በገጠራማ ክፍሎቻቸው የጫት ቃሚዎች ቁጥር እንደሚበዛም አመላክቷል። ጥናቱ በማከልም ከተለዩት የጫት ቃሚዎች በአማካኝ በ17 ዓመት ዕድሜያቸው ጫት መቃም እንደሚጀምሩ ገልጿል።

በጫት ምርት፣ ንግድ እንዲሁም ማኅበራዊ ውጤቶች ላይ በርካታ ምርምሮችን እንዲሁም መጽሐፍትን ያዘጋጁት ፕሮፌሰር ሕዝቅኤል ገቢሳ፤ ጥናቱ በተለይም የጫት ቃሚዎች ቁጥር በገጠራማ አካባቢዎች ቁጥሩ ከፍ ያለ ነው የሚለውን እንደማይስማሙበት ገልጸው በተለያዩ ዓመታት በሠሯቸው ጥናቶች ከተሜው የበለጠ ጫትን እንደሚቅም ማረጋገጣቸውን ተናግረዋል።

#አዲስማለዳ

ተጨማሪ የንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-08-19
ቅሬታዎች ወደTIKVAH-ETH መምጣታቸው ቀጥሏል!

ከዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ፈተና ውጤት ጋር በተያያዘ አሁንም ቅሬታዎች እየቀረቡ ናቸው። ኤጀንሲው ላቀረብንለት ጥያቄ ምላሽ እንዲሰጠን እንፈልጋለን ብለዋል ውጤታችን ትክክል አይደለም ያሉ ተማሪዎች።

#ከአፕቲትዩድ ውጪ ያሉት ትምህርቶች ቢፈተሹ ጥሩ ናቸው ያሉት ቅሬታ አቅራቢ ወላጆችና መምህራን ሲሆኑ ከተስተካከለው ትምህርት ጋር ተመሳሳይነት ያለው ችግር ባይኖር እንኳን የሚቀርበውን ጥያቄው ተቀብሎ መልስ መስጠት ይኖርበታል ብለዋል።

🏷TIKVAH-ETH ኤጀንሲው እየቀረበለት ለሚገኘው ቅሬታ ምን አይነት ምላሽ ለመስጠት ጥረት እያደረገ ነው?? እስካሁንስ ቀርበዋል በተባሉት የ9,000 ተማሪዎች ቅሬታ ላይ ምን ችግር ተገኘ?? በተጨማሪ የታገደባቸው ተማሪዎች እጣ ፋንታ ምን ይሆናል?? የሚለውን የሚመለከታቸውን አካላት አነጋግሮ ምላሽ ለማግኘት ጥረት ያደርጋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
"በአማራ እና በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች መካከል የሚፈጠሩ ግጭቶችን በዘላቂነት ለመቅረፍ ህዝብን ለግጭት የሚያሰልፉ አመራሮችን መለየትና በግልጽ መታገል ያስፈልጋል።" (የቤኒሻንጉል ጉሙዝ እና የአማራ ክልሎች የትብብር ሰነድ ሲፈራረሙ ከተናገሩት የተወሰደ)

@tsegabwolde @tikvahethiopia
e903df39-1035-44e8-b13d-4397366f8960_32k.mp3.crdownload
5.1 MB
ፌክ ኒውስ - የፈጠራ ወሬ፡- ምንጩ፣ መገለጫው፣ መዘዙ፣ ማርከሻው...
ፌክ ኒውስ - የፈጠራ ወሬ፡- ምንጩ፣ መገለጫው፣ መዘዙ፣ ማርከሻው...

የፈጠራ ወሬ ወይም FAKE NEWS አንባቢን ወይም አድማጭን ለማታለል ወይም ትክክለኛ መረጃ እንዳያገኝ ሆን ተብሎ የሚሠራጭ አሳሳችና የሃሰት ዜና ነው።

FAKE NEWS ወይም የፈጠራ ወሬ በተለይ አሁን አሁን ብዙ አድማጭና አንባቢ ከሚታወቁ የዜና ማሠራጫ ጣቢያዎች ይልቅ ከተለያዩ ማኅበራዊ መገናኛዎች ዜና በሚፈልግበት፣ በሚቃርምበትና ሃሣቡንም በሚያንሸራሽርበት ዘመን አደጋው ከፍተኛ ሆኗል።

FAKE NEWS ወይም የፈጠራ ወሬ በማኅበረሰብ ውስጥ መተማመንን ያሳጣል፤ መንግሥትና ሕዝብን፣ ሕዝብን ከሕዝብ ያጋጫል። በFAKE NEWS ወይም በፈጠራ ወሬ ሥርጭት ላይ ጥናት ያደረጉ ማርከሻውንም የሚመክሩ ባለሙያ አቶ ዳኛቸው ተሾመ በዚህ ጉዳይ ለተጠየቁ ጥያቄዎች መልስ ሰጥተዋል።

አቶ ዳኛቸው ተሾመ ሎስ አንጀለስ - ካሊፎርኒያ የሚኖሩ ላለፉት ሰላሣ ዓመታት በትምህርት፣ በምርምርና በሥራም ከኮምፕዩተር ሳይንስ ጋር ያሉ ሰው ናቸው። በዳታ ቤዝ ዲዛይንና አርክቴክቸር ላይ ሠርተዋል። የሁለተኛ ዲግሪያቸውን ምርምርና ፅሁፍም የሠሩት ድምፅን በመፈተሽና ለይቶ በማወቅ ክህሎት ላይ መሆኑን ይናገራሉ። ከዚያ በተለይ ግን አቶ ዳኛቸው እራሴን ማሳወቅ የምፈልገው “ሕይወቱን ለሰው ልጅ መብት መከበር እንደሰጠ ሰው ነው” ይላሉ።

የጄነራል አሳምነው ፅጌና የአማራ ክልል መገናኛ ብዙኃን ኃላፊ የመጨረሻ የስልክ ምልልስ የድምፅ ቅጂም ዩናይትድ ስቴትስ በሚገኝ ዲጂታል አሻራ መርማሪ ቡድን አስመርምረው ያገኙትን ውጤትም ያካፍላሉ።

ይቀጥላል👇
ይህ የዲጂታል ፎረንሲክ ኤክስፐርትስ - የድርጅቱ ስም ነው - /ዲጂታል አሻራ መርማሪ ባለሙያዎች/ ሙያዊ አስተያየት ነው። ሪፖርተሩና ሟቹ /አሁን “ተናጋሪው” የሚባሉት/ የተቀረፁት በአንድ ጊዜ /በተመሣሣይ ጊዜ ወይም አንድ ላይ/ ነው፤ ወይም /የሁለቱም ድምፅ/ እንደገና ተቀርፆም ከሆነ የተቀረፀው በአንድ ጊዜ /ወይም አንድ ላይ/ ሊሆን ይችላል።

ያልተቋረጠ /ወይም የተያያዘና ተከታታይ/ ኢ.ኤን.ኤፍ. - የእንግሊዝኛ አባባል ምኅፃር ነው - የኤሌክትሪክ ትስስር /ኔትወርክ/ ሞገድ አለ። የድምፁ ሂደት የተሰባበረ አይደለም፤ ይህ ማለት ለእኛ በተላከልን የተቀረፀ ድምፅ ላይ ሪፖርተሩና ተናጋሪው የተቀረፁት በአንድ ጊዜ /በተመሣሣይ ጊዜ ወይም በአንድ ላይ/ መሆኑን ያረጋግጣል። በሌላ በኩል ደግሞ የኤሌክትሪክ ትስስር ሞገዱ /ኢ.ኤን.ኤፍ/ እንዳይቆራረጥ ለማድረግ ሪፖርተሩ መጠይቆቹን ተገቢ ጊዜያቸውን እየጠበቀ የተናጋሪውን ቀድሞ የተቀረፀ ድምፅ እያጫወተ ቀርፆ ሊሆንም ይችላል። የሪፖርተሩ ድምፅ ከተናጋሪው ድምፅ ጋር እየተቆራረጠ አልተቀጣጠለም።

ይቀጥላል👇
ይህ የዲጂታል ፎረንሲክ ኤክስፐርትስ - የድርጅቱ ስም ነው - /ዲጂታል አሻራ መርማሪ ባለሙያዎች/ ሙያዊ አስተያየት ነው። ምንጩ ላይ ለማስተካከል ወይም ለመቀማመር ተብሎ በእጅ የተከናወነ ሥራ የለም። አንዱን ድምፅ በሌላኛው ላይ ማስኬድን፣ ወጥነት የሌላቸው የድምፅ ውጣ ውረድ ዓይነቶችን፣ ቆርጦ መቀጠልን ወይም መሰል ለማጭበርበር ተብሎ የተፈፀመ የአርትኦት ሥራ የለበትም።

ይቀጥላል👇
በመጨረሻም ሪፖርተሩ ያወጣው የተቀረፀ ድምፅና የቀረቡት ሁለት ናሙናዎች ተመሣሣይ /ወይም አንድ/ መሆናቸውን የዲጂታል ፎረንሲክ ኤክስፐርትስ - የድርጅቱ ስም ነው - /ዲጂታል አሻራ መርማሪ ባለሙያዎች/ ሙያዊ አስተያየት ያረጋግጣል። የተቀረፀውን ድምፅ አሻራ የያዘውን ድምፅ በጊዜ ውስጥ የሚያሳየውን ሞገድ ሂደት የሚያመላክቱ ምሥሎች /ስፔክቶግራምስ/ በተለይ የተከበቡትን ሞገዶች ይመልከቱ። ከተናጋሪው ድምፅ ጋር የተቀላቀሉ ሌሎች የጀርባ የድምፅ ሞገዶች ከጊዜ ወደ ጊዜ አነስተኛ ለውጦችን ቢያሳዩም ዋናዎቹ ነጥቦች፣ እንዲሁም ቁልፍ በሆኑት ሞገዶች መካከል ያሉት ክፍተቶች ግን አሉ።

Via VOAአማርኛ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ሱዳን

የሱዳን ተቃዋሚ ሃይሎች አምስት ሲቪል የሉአላዊ ምክር ቤት አባላትን መምረጣቸው ተገለፀ። በሱዳን ተቃዋሚዎች ጥምረት የመረጧቸው የኡአላዊ ምክር ቤቱ አባላቱ በዛሬው እለት ቃለ መሃላ ይፈጽማሉ ተብሎ እንደሚጠበቅም ተነግሯል። ከወታዳራዊ ሽግግር ምክር ቤት፤ መሪውን አብደል ፈታህ አልቡራን፣ ምክትላቸውን ሞሃመድ ሃማዳን ዳጋሎ እና የወታዳራዊ ሽግግር ምክር ቤት ቃል አቀባይ ሌተናል ጀኔራል ያሰር አል አታን ይጨምራል ነው የተባለው፡፡

Via #CGTN/#FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#FAKENEWS

የፈጠራ ወሬ ወይም FAKE NEWS አንባቢን ወይም አድማጭን ለማታለል ወይም ትክክለኛ መረጃ እንዳያገኝ ሆን ተብሎ የሚሠራጭ አሳሳችና የሃሰት ዜና ነው።

FAKE NEWS ወይም የፈጠራ ወሬ በተለይ አሁን አሁን ብዙ አድማጭና አንባቢ ከሚታወቁ የዜና ማሠራጫ ጣቢያዎች ይልቅ ከተለያዩ ማኅበራዊ መገናኛዎች ዜና በሚፈልግበት፣ በሚቃርምበትና ሃሣቡንም በሚያንሸራሽርበት ዘመን አደጋው ከፍተኛ ሆኗል።

FAKE NEWS ወይም የፈጠራ ወሬ በማኅበረሰብ ውስጥ መተማመንን ያሳጣል፤ መንግሥትና ሕዝብን፣ ሕዝብን ከሕዝብ ያጋጫል።

Via #VOA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በእነ ብርጋዴየር ጄኔራል ተፈራ ማሞ ክስ መመስረቻ ላይ ውሳኔ ለመስጠት ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጠ!

ከሰኔ 15ቱ የባሕር ዳር ጥቃት ጋር በተያያዘ በቁጥጥር ስር ያሉትን የእነ ብርጋዴየር ጄኔራል ተፈራ ማሞን ጉዳይ እየተመለከተ ያለው የባህርዳር እና አካባቢው ፍርድ ቤት በተጠርጣሪዎች ላይ ክስ ለመመስረት ወይም ተጨማሪ የጊዜ ቀጠሮ መስጠት የሚያስችል ውሳኔ ለመስጠት ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጠ። ፍርድ ቤቱ ውሳኔውን ከሁለት ቀናት በኋላ ለመስጠት ቀጠሮ ይዟል።

ከባሕሩ ዳሩ ጥቃት ጋር በተያያዘ በሶስት የተለያዩ መዝገቦች የተካተቱ ተጠርጣሪዎች ብዛት 61 ናቸው። በተጠርጣሪዎቹ ላይ ሲቀርብ የቆየውን የምርመራ የጊዜ ቀጠሮዎችን ሲፈቅድ የቆየው የባሕር ዳር ወረዳ ፍርድ ቤት ከሁለት ሳምንት በፊት ባስቻለው ችሎት የ15 ቀናት የክስ መመስረቻ ቀጠሮ ሰጥቶ ነበር። ፍርድ ቤቱ “በተጠርጣሪዎች ላይ የቀረበው የሰው እና የሰነድ ማስረጃ ለክስ በቂ ነው” በማለት ነበር ከዚህ በኋላ የምርመራ ጊዜ እንደማይፈቅድ በማስታወቅ መዝገቡን የዘጋው።

ጉዳዩን የያዘው መርማሪ ቡድን ግን “ምርመራዬን አላጠናቀቅሁም” በማለት ለባሕር ዳር እና አካባቢው ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቤት ብሏል። የተጠርጣሪ ጠበቆች “የጊዜ ቀጠሮ ይግባኝ የማይባልበት አሰራር ስለሌለው ፍርድ ቤቱ የመርማሪ ቡድኑን ጥያቄ ውድቅ ሊያደርገው ይገባል” ሲል ተቃውመዋል። ዛሬ ጉዳዩን ሲያከራክር ያረፈደው የባሕር ዳር እና አካባቢው ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሁለቱንም ወገኖች ክርክር መርምሮ ውሳኔ ለመስጠት ለነሐሴ 16 ቀን 2011ዓ. ም. ከሰዓት በኋላ ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቶ የዕለቱን የችሎት ውሎ ቋጭቷል።

Via #DW
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በመሬት ናዳ የሰው ህይወት አለፈ!

በወላይታ ሶዶ ከተማ የተከሰተው ድንገተኛ የመሬት ናዳ የእናትና ልጅ ሕይወት መጥፋቱን ፖሊስ አስታወቀ። የከተማዋ ፖሊስ አዛዥ ኢንስፔክተር ወጋየሁ ዳና እንደገለጹት አደጋው የደረሰው እናትና  ልጅ ከምንጭ ውሃ ለመቅዳት በሄዱበት በተከሰተ ናዳ ሕይወታቸው አልፏል።

አደጋው የተከሰተው ከጠዋቱ አንድ  ሰዓት ገደማ በከተማው ድል በትግል ቀበሌ ሆርባቢቾ መንደር እንደነበርም አስረድተዋል። የአደጋው ተጎጂዎች ያሰሙትን ጥሪ ተከትሎ ፖሊስና የአካባቢው ማህበረሰብ ሟቾችን ለማትረፍ ጥረት አድርጎ እንደነበር ገልጸዋል። የሟቾቹ አስከሬን ለቤተሰቦቻቸው መሰጠቱንም አዛዡ ተናግረዋል።

ማህበረሰቡ በተለይም ከፍተኛ ዝናብ የሚጥልበትን ወቅት በመለየት ጥንቃቄ እንዲያደርግ ኢንስፔክተር ወጋየሁ አሳስበዋል። በወላይታ ዞን ኦፋና ኪንዶ ኮይሻ ወረዳዎች ሰሞኑን በተከሰቱ አደጋዎች በሕይወትና በንብረት ላይ ጉዳት አድርሷል።

ምንጭ፦ ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጥቁር ለሊት!
ሞጣ ሁለት የቁርጥ ቀን ልጆቿን አጣች!

በሞጣ ከተማ አስተዳደር 01 ቀበሌ ውስጥ ነው አቶ መለሰ ማናየ እና አቶ አዱኛ አስማማው እንደተለመደው የሞጣን ሰላምና ጸጥታ ለመጠበቅ ወጥተው ነበር፡፡ ግን አልተመለሱም ከምሽቱ 4፡00 ሰዓት ሲሆን አቶ እንደግ እንየው የተባለ ህገ ወጥ መሳሪያ አዟዟሪን አገኙት ቁም ሲሉት መቆም አልቻለም፡፡ መሳሪያ መያዛቸውን ያረጋገጠው ገዳይ እንደገና እንየው ሁለቱንም ጸጥታ ስራ ላይ ያሉ ጓዶች በያዘው ሽጉጥ አውቶማቲክ በመተኮስ መታቸው፡፡ ሞቾችም ከወደቁ በኋላ ባደረጉት ተኩስ ገዳይ እንደገና እንየውን ገደሉት፡፡ ሶስት አስከሬን አንድ ቦታ ላይ በተመሳሳይ ሰዓት ተነሳ፡፡ የአቶ መለሰና የአቶ አዱኛ የቀብር ስነስርዓታቸው የከተማው አመራሮች የፖሊስ አባላት የሚሊሻ አባላትና ተክልል የተመደቡ ልዩ ሀይሎች እንዲሁም ወዳጅ ቤተሰቦቻቸው ባሉበት በሞጣ ደብረ ገነት ቅዱስ ጊወርጊስ ቤተ ክርስቲያን ከቀኑ6፡30 ላይ ተፈጽሟል፡፡ ለሁለቱም የሚሊሻ አባሎቻችን ለከፈሉት መስዋትነት እግዚ አብሔር ነፍሳቸውን በአጸደ ገነት ያስቀምጥልን እያልን ለቤተሰቦቻቸውና ለቅርብ ጓዶቻቸው መጽናናትን ተመኘን፡፡

ሞጣ ከተማ ኮሚኒኬሽን ቢሮ

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የጎንደር ዩንቨርሲቲ በባዮ ቴክኖሎጂ መስክ በርካታ የምርምር ሥራዎችን ላበረከቱት ለዶክተር ሳሙኤል ሳህሌ የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ሰጠ፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ቃና ቴሌቪዥን ተቀጣ!

የንግድ ውድድርና የሸማቾች ጥበቃ ባለስልጣን አስተዳደራዊ ችሎት ቃና ቴሌሌቪዥን አሳሳች የጥርስ ሳሙና ማስታወቂያ አስተላልፏል በሚል ከዓመታዊ ገቢው ላይ አምስት በመቶውን እንዲከፍል ሐምሌ 12/2011 ቅጣት ጣለበት።

የብሮድካስት ባለስልጣን ‹‹ሌሎች የጥርስ ሳሙናዎች በቂ አይደሉም፤ ለዚህም ነው ምርጫዬ ዳቦር ኸርባል የሆነው›› በሚል አረፍተ ነገር እናት እና ልጅ የሚነጋገሩበት ማስታወቂያ በጥናት ያልተረጋገጠ እና ለሌሎቹ ተወዳዳሪዎችም ፍትሃዊ ያልሆነ ነው በማለት አቤቱታ ማስገባቱን ተከትሎ ግንቦት 12/2011 በባለስልጣኑ አቃቤ ህጎች ክስ ተመስርቶበት ነበር። ባለስለጣኑ በማስታወቂያው ላይ ሙያዊ ጥናት በማካሄድ እና ማስታወቂያውን በማስረጃነት በማቅረብ አስረድቷል።

ከቃና ቴሌቪዥን ባሻገር የዳቦር ኸርባል የጥርስ ሳሙና አስመጪ ድርጅት ባለቤት አብዱራዛቅ ታከለ ፍትሃዊ ያልሆነ ማስታወቂያ አሰርተዋል በሚል በተመሳሳይ ከአመታዊ ገቢያቸው ላይ የአምስት በመቶ ቅጣት ተጥሎባቸዋል። ማስታወቂያውን ያዘጋጀው ቢ ሚዲያ እና የማስታወቂያ ድርጅትም በተመሳሳይ ከዓመታዊ ገቢው ላይ የአምስት በመቶ ቅጣት እንደተጣለበት የባለስልጣኑ የውሳኔ መዝገብ ያስረዳል። የቃና ቴሌቪዥን የህዝብ ግንኙነት ኀላፊ ኀይሉ ተክለ ሃይማኖት ለባለስልጣኑ ይግባኝ ሰሚ ችሎት ይግባኝ ማለታቸውን እና ውሳኔው ላይም ምንም አይነት አስተያየት መስጠት እንደማይችሉ ተናግረዋል።

Via አዲስ ማለዳ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#መተማ

የመከላከያ ሠራዊት ንብረት ናቸው የተባሉና በመተማ ዮሐንስ በኩል ጭነት ይዘው ወደ ሱዳን ሊሻገሩ ሲሉ እንዲቆሙ በተደረጉ አምስት ከባድ ተሽከርካሪዎች ላይ ምርመራ እየተደረገ መሆኑን የአካባቢው ፖሊስ ለቢቢሲ ገለጸ።

ትናንት ከሰዓት ከዘጠኝ ሰዓት በኋላ አምስት የመከላከያ ሠራዊት ከባድ ተሽከርካሪዎች ወደ ሱዳን ለመሻገር ሲሞክሩ መተማ ዮሐንስ ላይ በአካባቢው ማኅበረሰብ ታግደው እንዳያልፉ መደረጋቸውን በስፋት እያነጋገረ ይገኛል።

ከስፍራው የሚወጡ መረጃዎችና ፎቶግራፎች እንደሚጠቁሙት ጭነት የያዙት ከባድ ተሽከርካሪዎች ጥቂት በማይባሉ ሰዎች ተከበው መንገድ ዳር እንደቆሙና የአካባቢው ባለስልጣናትም ስለጭነቱ ህጋዊነት ለማወቅ የማጣራት ጥረት እያደረጉ መሆናቸውን ያመለክታሉ።

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/Metema-08-19
የዘጠኙ ተጠርጣሪዎች ዋስትና ታገደ!

የደቡብ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በሀዋሳ ከተማና በሲዳማ ዞን የተለያዩ አካባቢዎች ተከስተው የነበሩ ሁከቶችን አስተባብረዋል ለተባሉ ዘጠኝ ተጠርጣሪዎች የስር ፍርድ ቤት የፈቀደውን ዋስትና አገደ። ፍርድ ቤቱ የእግድ ትዕዛዙን የሰጠው ፖሊስ ዋስትናውን በመቃወም ያቀረበውን የይግባኝ አቤቱታ በመቀበል ነው።

በእነ ታሪኩ ለማ መዝገብ የተጠረጠሩ ዘጠኝ ሰዎችን የጊዜ ቀጠሮ ጉዳይ ሲመለከት የቆየው የሀዋሳ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ለተጠርጣሪዎች የዋስትና መብት የፈቀደው ባለፈው አርብ ነሐሴ 10 በዋለው ችሎት ነው። ፍርድ ቤቱ እያንዳንዳቸው ተጠርጥሪዎች የ50 ሺህ ብር ዋስትና በማቅረብ ጉዳያቸውን በውጭ ሆነው እንዲከታተሉ ወስኖ ነበር።

በተጠርጣሪዎች ላይ ምርመራ በማካሄድ ላይ የሚገኘው ፖሊስ አርብ ዕለት ለደቡብ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት አቤቱታ በማስገባቱ ተጠርጣሪዎቹ ሳይፈቱ ቀርተዋል። አቤቱታውን ዛሬ የተመለከተው የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ለተጠርጣሪዎቹ በተፈቀደላቸው ዋስትና ላይ የእግድ ትዕዛዙን አስተላልፏል።

ፍርድ ቤቱ ግለሰቦቹ የተጠረጠሩበት ወንጀል የዋስትና መብትን የሚፈቅድ ወይም የሚከለክል መሆኑን ለማከራከር እና ለፖሊስ የተሰጠው የምርመራ ጊዜ በቂነቱን በመመርመር ብይን ለመስጠት ለነሐሴ 24 ቀን 2011 ዓ.ም ቀጠሮ ሰጥቷል። በሀዋሳ ከተማ እና በሲዳማ ዞን ተከስተው ከነበሩ ሁከቶች ጋር በተያያዘ በቁጥጥር ስር ከዋሉት ተጠርጣሪዎች መካከል የሲዳማ ሚዲያ ኔትዎርክ ዋና ስራ አስኪያጅ ጌታሁን ደጉዬ ፣ ምክትላቸው ታሪኩ ለማ እና የእዚሁ ጣቢያ የቦርድ አባል የሆኑት በላይ ባልጉዳ ይገኙበታል።

Via #DW
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በአዲስ አበባ አማራ ወጣት ማህበር አዘጋጅነት የተሰናዳው የቡሄ፣ የሻደይ፣ አሸንድዬ እና የሶለን በዓል በጃን ሜዳ እየተከበረ ይገኛል።

Via Henok View
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"ዛሬ በሁሩታ ከተማና ባካባቢዉ ካሉ ቀበሌዎች ጋር የቡሄ በአልን #በጅራፍ ግርፍ በዚህ መልኩ አክብረናል።" መክብብ ከሁሩታ

@tikvahethiopia @tsegabwolde