TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.8K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ፎቶ👆ዛሬ ጥዋት የተከሰከሰው ሂሊኮፕተር የወደቀው በመኖሪያ ቤት ላይ ሲሆን፤ የተከሰከሰበት ምክንያትም የሞተር መጥፋት እንደሆነ ነው የታወቀው።

#reporter
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ኢትዮ ቴሌኮም ሃብቱን በውጭ ኩባንያ እያስመረመረ መሆኑን ሪፖርተር አስነብቧል፡፡ መርማሪው የእንግሊዙ ፕራይስ ወተር ሃውስ ኩፐር የተባለው ኩባንያ ነው፡፡ ኩባንያው ካሁን በፊት የኢትዮ ቴሌኮምን የፋይናንስ አስተዳደርና የሒሳብ አያያዝ ሥርዓት አደራጅቷል፡፡ ጥናቱ እስከ 6 ወራት ሊፈጅ ይችላል፡፡ የሃብት ግምቱ ሲጠናቀቅ ዲሊዮት የተባለ የእንግሊዝ ኩባንያና ኧርነስት ኤንድ ያንግ የተባለ የአሜሪካ ኩባንያ ደሞ ኢትዮ ቴሌኮም በሙሉ ወይም በከፊል ወደ ግል ባለሃብቶች ሲዘዋወር የአክሲዮን አወቃቀርና ሽያጭን በተመለከተ እንዲያማክሩ ተቀጥረዋል፡፡ የአማካሪ ኩባንዎችን ወጭ ዐለም ባንክና ለጋሽ ሀገራት ይሸፍናሉ፡፡ አጠቃላይ ሂደቱ የሚመራበት ረቂቅ ሕግ ገና በፓርላማ አልጸደቀም፡፡

Via #reporter
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ብ/ጄኔራል ተፈራ ማሞ በቁጥጥር ስር ውለዋል...

የአማራ ክልል ልዩ የፖሊስ ኃይል ዋና አዛዥ ብርጋዴር ጄኔራል ተፈራ ማሞን ጨምሮ፣ አራት የክልሉ አመራሮች መታሰራቸውን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል፡፡

Via #reporter
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከፍተኛ ውዝግብ ያስነሱት የ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች #ለዕድለኞች መተላለፍ ጀመሩ፦
.
.
የካቲት 27 ቀን 2011 ዓ.ም. በኢንተርኮንቲኔንታል ሆቴል የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስትር በነበሩት አቶ ጃንጥራር ዓባይና በአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማ (ኢንጂነር) በይፋ ዕጣ ከወጣበት በኋላ፣ ከፍተኛ ውዝግብ ፈጥሮ የነበረው የ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤት ዕጣ ለወጣላቸው ዕድለኞች ማስተላለፍ ተጀመረ፡፡

ከ18 ሺሕ በላይ በሚሆኑ የ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ ከወጣ በኋላ፣ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር በገቡት ውል ምክንያት በወቅቱ እንደ ቤቱ ስፋት ተተምኖ የነበረውን ክፍያ ሙሉ በሙሉ (መቶ በመቶ) የፈጸሙ በርካታ ሰዎች የዕጣውን መውጣት ተቃውመው ነበር፡፡ ተቃውሟቸው ‹‹ለምን ዕጣው ወጣ?›› በሚል ሳይሆን፣ ከንቲባው የቤት ግንባታ ፕሮግራም ዓላማና መመርያ ከ40 በመቶ በላይ የተገመተውን ዋጋ የቆጠበ በሙሉ በሚወጣው የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ ውስጥ መካተት አለበት ብለው ዕጣው በመውጣቱ ነበር፡፡

በመሆኑም መቶ በመቶ ክፍያ የፈጸሙት በርካታ ሰዎች ተሰባስበው ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት ወስደውት ነበር፡፡ ከ200 በላይ የሚሆኑ የ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች መቶ በመቶ ከፋዮች፣ በተለያዩ መዝገቦች የዳኝነት በመክፈል በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ፍትሐ ብሔር ችሎት ክስ መሥርተው ነበር፡፡

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴርንና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቁጠባ ቤቶች ልማት ኢንተርፕራይዝን የከሰሱት ግለሰቦቹ፣ ባንኩ ውል በመፈጸም ሚኒስቴሩ ያወጣውን መመርያ ባለማስፈጸሙና ኢንተርፕራይዙ ደግሞ ሕግ ተላልፎ ዕጣ በማውጣቱ፣ በአንድ ላይ በመክሰሳቸው ፍርድ ቤቱ ዕጣ የወጣባቸውና ዕጣ ያልወጣባቸውም የ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ለዕድለኞች እንዳይተላለፉ ዕግድ ጥሎ ነበር፡፡

ፍርድ ቤቱ የቀረበለትን ክስ ከመረመረ በኋላ በሰጠው ትዕዛዝ፣ በተለይ መጀመርያ ክስ ባቀረቡት 98 ሰዎች የተመዘገቡት የቤት ዓይነት ከየሳይቱ ታግዶ እንዲቆይ በማለት፣ የቀሪዎቹን የ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕግድ አንስቷል፡፡

ሌሎችም አመልካቾች በተመሳሳይ ሁኔታ ክስ መሥርተው ጉዳያቸው እየታየ ቢሆንም፣ ዕግዳቸው የተነሳላቸው የጋራ መኖሪያ ቤቶች ለዕድለኞች ከሰኔ 14 ቀን 2011 ዓ.ም. ጀምሮ ውል የሚዋዋሉበት ፕሮግራም በየክፍላተ ከተሞቹ ወጥቶላቸው በመዋዋል ላይ ይገኛሉ፡፡

አስተዳደሩ 32,653 የ20/80 የጋራ መኖሪያ ቤቶችን ዕጣ ያወጣ ቢሆንም፣ ለዕድለኞቹ መቼ እንደሚተላለፉ ያለው ነገር የለም፡፡   

Via #reporter
🗞ቀን ሰኔ 26/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
20/80 የጋራ መኖሪያ ቤት...

የአ/አ ከተማ አስተዳደር 32,653 የ20/80 የጋራ መኖሪያ ቤቶችን ዕጣ ያወጣ ቢሆንም፣ ለዕድለኞቹ መቼ እንደሚተላለፉ እስካሁን ያለው ነገር የለም፡፡   

Via #reporter
🗞ቀን ሰኔ 26/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊና የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል አቶ ክርስቲያን ታደለ፣ ታስረው ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ቀጠሮ ተጠየቀባቸው፡፡

አቶ ክርስቲያን በቁጥጥር ሥር የዋሉት ሐምሌ 4 ቀን 2011 ዓ.ም. ነው፡፡ በፌዴራል ፖሊስ ታስረው የሚገኙ የአብን አመራሮች፣ አባላትና ደጋፊዎችን ፒያሳ አካባቢ በሚገኘው የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን እስር ቤት ጠይቀው ሲመለሱ መሆኑን የአብን ሊቀመንበር ደሳለኝ ጫኔ (ዶ/ር) ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡ አመራሮቻቸውና አባሎቻቸው የታሰሩት በቀዝቃዛ ቦታ፣ የፀሐይ ብርሃን በማያገኙበትና ቤተሰብ ሊጠይቃቸው በማይችል ሁኔታ በመሆኑ እንዲሻሻልላቸው ከፖሊስ ኃላፊዎች ጋር ተወያይተው ሲወጡ፣ መውጫ በር ላይ አቶ ክርስቲያንን እንደያዟቸው ሊቀመንበሩ ተናግረዋል፡፡

በቁጥጥር ሥር ያዋላቸው መርማሪ ፖሊስ በነጋታው ሐምሌ 5 ቀን 2011 ዓ.ም. በፌዴራል የመጀመርያ ደረጃ ፍርድ ቤት ልደታ፣ ምድብ ወንጀል ችሎት እንዳቀረባቸውም አስረድተዋል፡፡

መርማሪ ፖሊስ ለምን አቶ ክርስቲያንን በቁጥጥር ሥር እንዳዋላቸውና እንዳሰራቸው ተጠይቆ በሰጠው ምላሽ፣ ተጠርጣሪው ወጣቶችን መሣሪያ እንደሚያስታጥቁና እንደሚያደራጁ በማስረዳት ለተጨማሪ ምርመራ 14 ቀናት መጠየቁም ታውቋል፡፡

ተጠርጣሪው አቶ ክርስቲያንም ወጣቶችን መመልመልና ማደራጀት ሥራቸው መሆኑንና ከእስርም ሲለቀቁ የሚቀጥሉት ሥራቸው እንደሆነ ተናግረው፣ መሣሪያ ያስታጥቃሉ ስለተባለው ግን ፖሊስ ማስረጃ ካለው እንዲያቀርብ ጠይቀዋል፡፡

ፍርድ ቤቱም የግራ ቀኙን ክርክር ሰምቶ ፖሊስ ምርመራውን እንዲያጠናቅቅ የሰባት ቀናት ተጨማሪ ጊዜ በመፍቀድ፣ ለሐምሌ 11 ቀን 2011 ዓ.ም. ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡

Via #Reporter
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#አብዛን_ንግድ

20 ሺ ሠራተኞችን #ለመቅጠር ገንዘብ እያስከፈለ በመመዝገብ ላይ የነበረው ግለሰብ ከእነ ጓደኞቹ ታስሮ ፍርድ ቤት ቀርቧል። አብዛን የተሰኘ የንግድ ሥራ ድርጅት ባለቤት መሆኑ የተገለጸ ግለሰብ 20 ሺሕ ሠራተኞችን ለመቅጠር በነፍስ ወከፍ 2,477 ብር በማስከፈል፣ በርካታ ወጣቶችን በመመዝገብ ላይ እያለ ከጓደኞቹ ጋር በቁጥጥር ሥር ውሎ ታሰረ፡፡ግለሰቡ አቶ አብርሃም ዘሪሁን የሚባል ሲሆን፣ የሥራ ማስታወቂያውን በቃና ቴሌቪዥንና በሌሎች ሚዲያዎች በማስተዋወቅ፣ ከሐምሌ 1 እስከ 18 ቀን 2011 ዓ.ም. ድረስ እያንዳንዱ ተመዘጋቢ የ2,477 ብር ሲፒኦ አሠርቶ እንዲመዘገብ ጥሪ ማድረጉ ታውቋል፡፡
.
.
ተጠርጣሪዎቹ ሐሰተኛ ሰነድ በመጠቀምና በተለይ የ2011 ዓ.ም. ተመራቂ ወጣቶችን በማማለል ከሦስት ሺሕ ብር በላይ ደመወዝ እንደሚከፍል፣ #ሐሰተኛ ማስታወቂያ በማስነገር ከእያንዳንዱ ተመዝጋቢ 2,744 ብር መቀበላቸውን ፖሊስ ገልጿል፡፡ ስለማስታወቂያውና ስለሥራው የተጠራጠረው ፖሊስ ከአሥር ተመዝጋቢዎች ጋር ባደረገው ቃለ መጠይቅ ጥርጣሬውን ይበልጥ ስላጎላው፣ ግለሰቦቹን ሐምሌ 13 ቀን 2011 ዓ.ም. በቁጥጥር ሥር አውሎ እየመረመረ መሆኑንና ለተጨማሪ ምርመራ 14 ቀናት እንዲፈቀድለት ጠይቋል፡፡

ተጨማሪ የንብቡ👇
https://telegra.ph/ABZAN-07-24

Via #reporter
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ትረስት ፈንድ በውጭ አገር ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በዕርዳታ ያሰባሰበውን 116 ሚሊዮን ብር (አራት ሚሊዮን ዶላር)፣ በኢትዮጵያ ለሚካሄዱ ማኅበራዊና ኢኮኖሚዊ ችግሮች ለሚፈቱ ፕሮጀክቶች እንደመደበ አስታውቋል፡፡

Via #reporter
@tsegabwolde @tikvahethiopia
‹‹ኃይሌ የለመደብህ #ወርቅ እንጂ ብር አይደለም›› ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ
.
.
የሻለቃ ኃይሌ ገብረ ሥላሴ ኩባንያ የሆነው ማራቶን ሞተርስ ከቀረጥ የ155 ሚሊዮን ብር ገቢ በማስገኘት ሐምሌ 20 ቀን 2011 ዓ.ም. የግብር ከፋዮች የማበረታቻ ዕውቅና ሽልማት የብር ደረጃ ተሸላሚ መሆን ችሏል። በወቅቱ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ‹‹ኃይሌ የለመደብህ ወርቅ እንጂ ብር አይደለም›› በማለት በቀልድ መድረኩን አዋዝተውት ነበር፡፡ 

Via #reporter
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ዐቃቤ ሕግ በቀድሞው የብሄራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ሃላፊ ደርበው ደመላሽና ሌሎች ተከሳሽ ሠራተኞች ላይ ምስክር ማሰማት መጀመሩን ሪፖርተር አስነብቧል፡፡ ፖሊስ ምስክሮቹን በአድራሻቸው ማግኘት ስላልቻልኩ፣ በስልካቸው እንድጠራ ተለዋጭ ቀጠሮ ይሰጠኝ ብሏል፡፡ በአካል የቀረቡት ምስክሮች 5 ሲሆኑ፣ በደኅንነቱ ሃላፊ ደርበው ላይ የመጀመሪያው ምስክር ቃል ተሰምቷል፡፡

በደኅንነቶች ታፍኜ ስለ “ድምጻችን ይሰማ” በግድ በፌስቡክ እንድጻጻፍ ተደርጌያለሁ፣ ድብደባ ተፈጽሞብኛል፤ ደርበው ትዕዛዝ ባይሰጡም በአካል በዝምታ ይከታተሉ ነበር በማለት ምስክርነቱን ሰጥቷል፡፡ ደርበው የገራፊዎቹ አለቃ መሆናቸውን እንዴት እንዳወቀ ዳኛው ሲጠይቁትም ከሁኔታቸው ገምቼ ነው ብሏል፡፡ ተከሳሹ በበኩላቸው ምስክሩ ደመወዝ ተከፋይ የሆነ፣ የደኅንነት ተቋሙ ወኪላችን ነበር፤ ስለመታሰሩ የማውቀው ነገር የለም ሲሉ ተከላክለዋል፡፡

Via #reporter/#wazemaradio
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ኢትዮጵያ ?

•እስከ መጋቢት 2011 ዓ.ም. ድረስ ያለው የአገሪቱ አጠቃላይ የውጭና የአገር ውስጥ ብድሮች ዕዳ 1.5 ትሪሊዮን ብር ደርሷል

•የኢትዮጵያ አየር መንገድና የኢትዮ ቴሌኮም የውጭ ብድር ዕዳ 111.9 ቢሊዮን ብር ነው።

•የሌሎቹ የልማት ድርጅቶች የውጭና የአገር ውስጥ አጠቃላይ የብድር ዕዳ 594 ቢሊዮን ብር ደርሷል።

•ማዕከላዊ መንግሥትና የልማት ድርጅቶች ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ተበድረው ያልመለሱት ዕዳ 412.5 ቢሊዮን ብር ደርሷል።

•መንግሥት ከንግድ ባንክ የወሰደውን ብድር መመለስ ባለመቻሉ በየዓመቱ እስከ 25 ቢሊዮን ብር ወለድ እየከፈለ ነው።

Via #REPORTER
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አቶ ሚሊዮን ማቴዎስ ከርዕሰ መስተዳድርነታቸው ተነስተው፣ በሚኒስትር ማዕረግ የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢሕአዴግ) ምክር ቤት ጽሕፈት ቤት የዴሞክራሲ ማዕከል ምክትል ዋና አስተባባሪ ሆነው እንደሚሾሙ ተሰምቷል። #Reporter

@tsegabwolde @tikvahethiopia
animation.gif
345 KB
እንደ አማዞን ደን እሳት ያልተጮኸለት የአንጎላና ኮንጎ የደን እሳት!

ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙኃን ብዙውን ትኩረት የሰጡት በብራዚል ለሚገኘው የአማዞን ደን ሰደድ እሳት ቢሆንም፣ በአማዞን የተከሰተው ሰደድ እሳት በአንጎላም ሆነ በዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ከተከሰተው የደን ሰደድ እሳት እንደማይበልጥ የናሳ መረጃ አመልክቷል፡፡

አልጀዚራና ቢቢሲ እንደዘገቡትም፣ በማዕከላዊ አፍሪካ በሚገኙት በሁለቱ አገሮች ደኖች የተከሰተው እሳት በአማዞን ከተከሰተው በሦስት እጥፍ ያየለ ነው፡፡

በቅርቡ በአማዞንም ሆነ በማዕከላዊ አፍሪካ ደኖች ላይ የተነሳው ሰደድ እሳት መጠን ሲታይ ከአንጎላና ከኮንጎ በመቀጠል የብራዚሉ አማዞን በሦስተኛ ደረጃ ሲገኝ ከብራዚል በመለጠቅ የዛምቢያ የደን ሰደድ እሳት አራተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል፡፡ የብራዚል ጎረቤት ቦሊቪያ ደግሞ ስድስተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡ የፖለቲካ ሚዛኑ ያደላውና የመገናኛ ብዙኃንን የላቀ ዘገባ ያገኘው ግን የአማዞኑ ነው፡፡

ከትላንት በስቲያ የተለቀቀውና መረጃው ከመለቀቁ በፊት በነበሩ 48 ሰዓታት ውስጥ የተከሰተውን ሰደድ እሳት አስመልክቶ ሁለት ሳተላይቶችን በመጠቀም የምድር የአየር ንብረት መረጃን የሚለቀው ሞዲስ (ኤምኦዲአይኤስ) እንዳስታወቀው፣ በአንጎላ 6,902፣ በዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ከንጎ 3,395 እንዲሁም በብራዚል 2,127 ሥፍራዎች ላይ የደን እሳቶች ተከስተዋል፡፡

በማዕከላዊ አፍሪካ ደን የተከሰተው ሰደድ እሳት፣ በብራዚል አማዞን ቀይ መቀነስ ሠርቶ እንደሚንቦገቦገው እሳት ሁሉ ከጋቦን አንጎላ ድረስ ቀይ ሰንሰለት ሠርቶ ይታያል ሲል የናሳ ሳተላይት ምስልን ጠቅሶ ፍራንስ 24 ዘግቧል፡፡

Via #Reporter
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት አካል ከሚሆኑት 16 የኃይል ማመንጫ ጀኔሬተሮች መካከል አምስቱ ጀኔሬተሮች፣ የግድቡ ግንባታ ተጠናቆ የሚፈለገው ውኃ ከተሞላ በኋላ እንዲገጠሙ ተወሰነ፡፡

ከፍተኛ ሀብት የሚወጣባቸው እነዚህ ውስን ጀኔሬተሮች ግድቡ ሙሉ በሙሉ በውኃ ሳይሞላ ኃይል ማመንጨት እንደማይችሉ እየታወቀ እንዲደረደሩ ማድረግ ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ የሌለው፣ ይልቁንም ለእነዚህ ጀኔሬተሮች የሚወጣውን ሀብት ለሌላ ፍላጎት በማዋል ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ማስገኘት የውሳኔው ምክንያትነት እንደሆነ ለመረዳት ተችሏል፡፡

ሪፖርተር ጋዜጣ ከታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ክፍሌ ሆሮ (ኢንጂነር) አገኘሁት ባለው መረጃ እንዳመለከተው፣ የኃይል ማመንጫ ግድቡ ቀሪ ግንባታ በሦስት ምዕራፎች ተከፍሎ እንዲከናወን የፕሮጀክት ጽሕፈት ቤቱ ያቀረበውን የውሳኔ ሐሳብ መንግሥት ተቀብሎ እንዳፀደቀውና ግንባታውም በዚሁ በተከለሰ የግንባታ መርሐ ግብር መሠረት መከናወን ተጀምሯል፡፡

ተጨማሪ የንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-09-01

Via #Reporter
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ዋና መሥሪያ ቤቱ በእንግሊዝ የሆነው ግሎባል ብራንድስ መጽሔት፣ ካሊብራ ሆስፒታሊቲና ቢዝነስ ኩባንያ በኢትዮጵያ የሆቴል ኢንቨስትመንት እንዲስፋፋ ላበረከተው አስተዋጽኦ ዕውቅና ሰጠ። በቅርቡ በለንደን በተካሄደ ሥነ ሥርዓትም የካሊብራ አማካሪዎች ሽልማቱን ተቀብሏል።

Via #reporter
@tsegabwolde @tikvahethiopia
https://unitypark.et/

መስከረም 30 ቀን 2012 ዓ.ም. ለጉብኝት ክፍት የሚሆነው የታላቁ ቤተ መንግሥት <<አንድነት ፓርክ>> ድረ ገጽ ይፋ ሆነ፡፡ ጎብኚዎች ስለ ፓርኩ ገጽታና ስለሚጎበኙ ስፍራዎች መረጃ ከድረ ገጹ ማግኘት የሚችሉ ሲሆን፣ የመጎብኛ ቀንና ሰዓት በመጥቀስ ትኬት መቁረጥም ያስችላል። ለፓርኩ ጉብኝት በተንቀሳቃሽ ስልክ ክፍያ ለመፈጸም የሚያስችል አሠራር በኢትዮ ቴሌኮም አማካይነት ተዘርገቷል።

https://unitypark.et/

#REPORTER
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በደኅንነት ሠራተኞች ላይ “የፖሊግራፍ” ምርመራ ቴክኖሎጂ ጥቅም ላይ ሊውል ነው!

•ለደኅንነት ተቋሙ የሚሾም ሰው ከአምስት ዓመት በፊት የፖለቲካ ድርጅት አባል ያልነበረ መሆን ይኖርበታል።

•የመረጃ መረብ ደኅንነትና የፋይናንስ ደኅንነት ማዕከልን ለማፍረስ ታቅዷል።

በብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት የሚቀጠሩም ሆነ የሚመደቡ ሠራተኞች በተቋም ላይ የደኅንነት ሥጋት ወይም አደጋ አለማስከተላቸው ሲታመነበት ብቻ፣ እንዲቀጠሩ ወይም እንዲመደቡ የሚያስገድድና ይህንንም ተግባራዊ ለማድረግ “በፖሊግራፍ” ቴክኖሎጂ የተደገፈ ምርመራ ሊደረግባቸው እንደሚችል ተገለጸ፡፡

ሪፖርተር ጋዜጣ በብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ላይ የተጀመረውን ሪፎርም አስመልክቶ ከታማኝ ምንጮች አገኘሁት ባለው መረጃ እንደሚያመለክተው፣ ሪፎርሙ ተጠናቆ ተግባራዊ መደረግ ሲጀምር በተቋሙ የሚቀጠሩም ሆነ የሚመደቡ ሠራተኞች ላይ ጥብቅ የደኅንነት ማጣራት ይደረጋል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-10-20-3

#REPORTER
@tsegabwolde @tikvahethiopia
" የሀብት ምዝገባ መረጃው ለህዝብ ክፍት ይደረግ "

የኢትዮጵያ ሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም የፌዴራል ሥነ ምግባርና የፀረ ሙስና ኮሚሽን #በተሿሚዎች#በተመራጮች ወይም #በመንግሥት_ሠራተኞች ላይ እያከናወነ ያለው የሀብት ምዝገባ መረጃ ለሕዝብ ይፋ እንዲያደርግ ጠይቋል።

በ2002 ዓ/ም በወጣው የሀብት ማሳወቂያና ምዝገባ አዋጅ ቁጥር 668/2002 ድንጋጌ መሠረት፦
👉 የአገሪቱ ፕሬዚዳንት፣
👉 ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣
👉 ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣
👉 ሚኒስትሮች፣
👉 ሚኒስትር ዴኤታዎች፣
👉 ኮሚሽነሮች፣
👉 ምክትል ኮሚሽነሮች፣
👉 ዋና ዳይሬክተሮች፣
👉 ምክትል ዋና ዳይሬክተሮች፣ እንዲሁም #ሌሎች የመንግሥት ሠራተኞች ሀብታቸውን እንዲያስመዘግቡ #ግዴታ ጥሎባቸዋል፡፡

የኢትዮጵያ ሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም ባወጣው መግለጫ፣ ግለሰቦቹ ለኮሚሽኑ ያስመዘገቡትን ሀብት መረጃ በሚስጥር መያዝና ለሕዝብ ይፋ አለማድረግ ከአዋጁ ጋር  የሚፃረር ድርጊት እንደሆነ አስረድቷል፡፡

በተለይም በመንግሥት ተቋማት የሚገኙ የሥነ ምግባር መከታተያ የሥራ ክፍሎች በየተቋማቸው ያለውን የሀብት ምዝገባ መረጃን ለማንኛውም መረጃ ጠያቂ እንዲሰጡ አለማድረግ፣ ወይም ምቹ ሁኔታ አለመፍጠር የሕገ መንግሥቱን የግልጽነትና ተጠያቂነት ድንጋጌንና የሀብት ማስመዝገቢያና ማሳወቂያ አዋጅ ቁጥር 668/2002 ጽንሰ ሐሳብና መሠረታዊ ዓላማን ግምት ውስጥ ያላስገባ መሆኑን አስታውቋል፡፡

መረጃ ያለመስጠት ድርጊት ለተጀመረው የሙስና ትግል ምንም ዓይነት አበርክቶ የሌለው በመሆኑ የሀብት ምዝገባ መረጃ ለሕዝብ ክፍት እንዲሆን የዕርምት ዕርምጃ እንዲወስድ ተቋሙ ጠይቋል፡፡

(የኢ/ሕ/ዕ/ጠ/ተቋም ወቅታዊና ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ የሰጠው መግለጫ ከላይ ተይይዟል)

#Reporter
#EthiopiaInstitutionoftheOmbudsman

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ATTENTION

" ለሕዝቡ አስቸኳይ ዕርዳታ ካልደረሰለት አደጋው ከአሁኑ ሊብስ ይችላል "

በሶማሌ ክልል ዳዋ ዞን አስተዳደር ምክትል አስተዳዳሪ አቶ መሐመድ ሀቢቻ ለሪፖርተር የሰጡት ቃል ፦

" ሕዝቡ የሚኖረው በከብቶቹ ላይ ተመሥርቶ ነው፡፡ ድርቁ እስከ መቼ እንደሚቀጥል አይታወቅም፡፡

ለሕዝቡ አስቸኳይ ዕርዳታ ካልደረሰለት አደጋው ከአሁኑ ሊብስ ይችላል።

የሞተውን የእንስሳት ሀብት ቁጥር ገና እየተጠና ነው፤ በሰዎች ላይ የደረሰውንም ጉዳት እየተገመገመ ነው።

ስለጉዳቱ የተጣራ አኃዝ ባይኖረንም በምግብ እጥረት ችግር ወደ ሆስፒታል የገቡ ሰዎች መረጃ አለን። "

NB. አምና በሶማሌ ክልል ካሉ 11 ዞኖች በአሥሩ ከባድ የድርቅ አደጋ ደርሶ #ከአንድ_ሚሊዮን ያላነሱ እንስሳትን ገድሏል። የዳዋ ዞን ገና ከዚህ አደጋ ያላገገመ ሲሆን ዘንድሮም ከባድ አደጋ ገጥሞታል።

Credit : #Reporter

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Ethiopia " ሌሎች ተዋናዮች የአፍሪካ ቀንድ ክልልን ለማተራመስ እርምጃ ሲወስዱ በዝምታ አንመለከትም " - ኢትዮጵያ @tikvahethiopia
#Ethiopia🇪🇹

" #ኢትዮጵያ ሶማሊያ እንደ አገር ትቆም ዘንድ ብዙ መስዋዕትነትን ከፍላለች፡፡ ብዙ ሺሕ የሚቆጣጠሩ ወንዶችና ሴቶች መስዕዋት አድርገናል ገብረናል፡፡

የቆጠብነው ነገር የለም ሕይወት ሰጥተናል፣ ደም ሰጥተናል፣ ላብ ሰጥተናል፣ ጉልበት ሰጥተናል፡፡ ነገር ግን በሶማሊያ በኩል ይህንን አስተዋጽኦ ከቁብ ላለመቁጠርና ውለታ ለማስቀረት የሚደረግ መግለጫ መስማት እንደ ኢትዮጵያዊ ይኮሰኩሳል።

እንደ አፍሪካዊና ሰላም ወዳድ እንደሆነው የሶማሊያ ሕዝብ ደግሞ ያማል።

በሶማሊያ በኩል የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ያደረገውን ተጋድሎ በማንኳሰስ፣ የወሬያቸውና የንግግራቸው ሁሉ ማዋዣ ብቻ ሳይሆን ማዕከል እያደረጉት ነው ፤ ይህ ነውር ነው !!

ኢትዮጵያ ለዘመናት ያደረገችውን አስተዋጽኦ እና የከፈለችውን ዋጋ በማጣጣል፣ የኢትዮጵያን ጥቅም የሚፃረሩ ኃይሎችን ሶማሊያ መጋበዟን ልታቆም ይገባል።

ኢትዮጵያ የደኅንነት ሥጋት የሚፈጥርባትን አካል ዝም ብላ አትመለከትም። " - አምባሳደር ታዬ አጽቀ ሥላሴ (የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር)

#Ethiopia #Reporter
@tikvahethiopia