TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.8K photos
1.49K videos
211 files
4.06K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የታገቱ ተማሪዎችን አስመልክቶ የሶሻል ሚዲያው ንቅናቄ!

የሶሻል ሚዲያ ንቅናቄዎች ምን ይመስላሉ ብለን ቃኝተን ነበር ከደምቢዶሎ ዩኒቨርሲቲ የተጠለፉ ተማሪዎችን አስመልክቶ በርካታ ሰዎች እነዚህን ፎቶዎች ተጠቅመው መንግስት እውነታውን እንዲገልጽ ሲጠይቁ አስተውለናል፡፡ አብዛኞቹ ልጄን መልሱልኝ የሚሉና #Bringbackourstudents የሚሉ ናቸው፡፡

#Facebook
#Tiwtter
#instagram

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
#BringBackOurStudents

የኢትዮጵያ መንግስት በታገቱት ተማሪዎች ዙሪያ በቂና ዝርዝር መረጃ ለተማሪዎቹ ወላጆችና ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ እንዲሰጥ፣ ተማሪዎቹ በምን አይነት ሁኔታ ላይ እንዳሉ እንዲገለፅ በማህበራዊ ሚዲያ ዘመቻ እየተካሄደ ይገኛል፤ ዘመቻው በመንግስት ላይ ጫና በማሳደር የተማሪዎቹን ሁኔታ እንዲያሳውቅ እንዲሁም ዓለም አቀፍ ሚዳያዎች ስለታገቱት ተማሪዎች ድምፅ እንዲሆኑ ለማድረግ ያለመ ነው።

ከወር በላይ ታግተው የሚገኙ ተማሪዎች የት እንዳሉ አይታወቅም ፤ የመንግስት ኃላፊዎች በየጊዜው በየሚዲያው እየወጡ የሚሰጧቸው መረጃዎችም እርስ በእርሳቸው የማይጣጣሙ ናቸው። የተማሪዎቹ ደህንነት ያሰጋቸው እና ያስጨነቃቸው በርካታ የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች መንግስት እውነቱን እንዲያወጣ ጫና እያሳደሩ ይገኛሉ።

PHOTO : Yanchi Movement
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia