TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.9K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
37 ሰዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ‼️

ባለፈው #ቅዳሜ በደቡብ ፖሊስና በወላይታ ድቻ እግር ኳስ ክለቦች መካከል ሊካሄድ በነበረው ጨዋታ ላይ #ግጭት እንዲፈጠር በማነሳሳት የተጠረጠሩ 37 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ።

የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ባህል፣ ቱሪዝምና ስፖርት ጉዳዮች መምሪያ ሃላፊ አቶ ደስታ ዳንጊሶ ጉዳዩን አስመልክቶ በዛሬው ዕለት መግለጫ ሰጥተዋል።

ሃላፊው በመግለጫቸው የራሳቸውን ፖለቲካዊ አጀንዳ የሚያራምዱ አካላት በሸረቡት ሴራ በዕለቱ በሰውና በንብረት ላይ ጉዳት መድረሱን ተናግረዋል።

በተፈጠረው ግጭትም በአንዲት ሴት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባት ሆስፒታል እንደምትገኝና 17 ሰዎች ላይ ደግሞ ቀላል ጉዳት መድረሱን ገልፀዋል።

ከዚህ ባለፈም የ10 መኪናዎች መስታወት ሙሉ በሙሉ የተሰባበረ ሲሆን ፥ አንድ ግሮሰሪ ላይም ዘረፋ ተፈጽሟል ነው ያሉት።

ግጭቱ የከፋ ጉዳት ከማድረሱ በፊት የሀዋሳ ከተማ ነዋሪዎችና የፀጥታ አካላት በመቀናጀት ባደረጉት ርብርብ በቁጥጥር ስር ሊውል መቻሉንም አንስተዋል።

ስለሆነም መገናኛ ብዙሃን የተከሰተውን ችግር ከማጋነንና #የተሳሳተ መረጃ ከማሰራጨት #እንዲቆጠቡ አሳስበዋል።

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽንም ከጉዳዩ ጋር ተያይዞ በደቡብ ፖሊስና በወላይታ ድቻ እግር ኳስ ክለቦች መካከል የሚደረገውን ጨዋታ ጨምሮ ሀዋሳ ከተማ ከቅዱስ ጊዮርጊስ እግር ኳስ ክለብ ጋር የሚያደርጉትን ጨዋታ ላልተወሰነ ጊዜ ማራዘሙ ታውቋል።

Via #fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia