TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.1K photos
1.5K videos
211 files
4.09K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ኢ/ር ታከለ ኡማ በከተማዋ ባሉ የተለያዩ ትምህርት ቤቶች በመገኘት የዕድሳት ሂደቱ ያለበትን ደረጃ ተመልክተዋል፡፡ ቦሌ መሠናዶ ፣ ኮከበ ጽበሃ እና ጥቁር አንበሳ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በዛሬው ዕለት ምልከታ ከተደረገባቸው ትምህርት ቤቶች ውስጥ ይገኙበታል፡፡

Via MayorOfficeAA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የኢንሳ የቀድሞ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ሌተናል ኮሎኔል ቢኒያም ተወልደ ዋስትና ታገደ!

የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ አንደኛ ወንጀል ችሎት ሐምሌ 29 ቀን 2011 ዓ.ም. በ30,000 ብር ዋስ ከእስር እንዲፈቱ ትዕዛዝ የሰጠ ቢሆንም፣ ከሳሽ ዓቃቤ ሕግ ለይግባኝ ሰሚው ችሎት ይግባኝ አቅርቦ እንዲታገድ አድርጓል፡፡

በከባድ የሙስና ወንጀል ተጠርጥረው #በእስር ላይ የሚገኙት ቀድሞ የኢትዮጵያ የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት ኤጀንሲ (ኢንሳ) ምክትል ዳይሬክተር ሌተና ኮሎኔል ቢኒያም ተወልደ፣ በተመሠረተባቸው ክስ እንዲከላከሉ ብይን ተሰጥቶባቸው ነበር፡፡ የሙስና ወንጀሎች አዋጅ ቁጥር 881/2007፣ አዋጅ ቁጥር 780/2005፣ አዋጅ ቁጥር 591/2007 የወንጀል ሕግ 808 ተላልፈዋል በማለት ዓቃቤ ሕግ እንደ ክሱ በማስረዳቱ በአምስት ክሶች  እንዲከላከሉ ብይን ተሰጥቶ ነበር፡፡

የተጠቀሱባቸው #የሕግ ድንጋጌዎች #ዋስትና እንደማይከለክሉ በማስረዳት ሌተና ኮሎኔል ቢኒያም በጠበቃቸው አማካይነት ፍርድ ቤቱ የዋስትና መብታቸውን እንዲጠብቅላቸው ጠይቀው ነበር፡፡ ዓቃቤ ሕግ በተከሳሹ ላይ የተጠቀሱት ሕጎች ከ15 ዓመታት በላይ ሊያስቀጧቸው እንደሚችሉ በመግለጽ፣ የዋስትና ጥያቄያቸው ውድቅ እንዲደረግ ተከራክሮ ነበር፡፡

ፍርድ ቤቱ የዋስትና ጥያቄው የሕግ ክልከላ ያለበት ነው ወይስ አይደለም የሚለውን መርምሮ፣ የዓቃቤ ሕግን መቃወሚያ ውድቅ በማድረግ በ30,000 ብር ዋስትና እንዲለቀቁና ዓቃቤ ሕግ ይግባኝ የሚል ከሆነ በማለት አሥር ቀናት ለመጠባበቂያ ሰጥቶ ነበር፡፡ ዓቃቤ ሕግም ይግባኙን ለፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት አቅርቦ ‹‹ያስቀርባል›› በመባሉ፣ ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት ትዕዛዝ እስከሚሰጥ ዋስትናው መታገዱ ታውቋል፡፡

Via Reporter
@tsegabwolde @tikvahethiop
#ነቀምቴ አንድነታቸውን አጠናክረው ለአካባቢያቸው ጽዳትና ደህንነት ተግተው እንደሚሰሩ በነቀምቴ ከተማ ነዋሪዎች ተናገሩ። ብሔራዊ የጽዳት ቀን ዛሬ በነቀምቴና ቁኒ ከተሞች ተካሄዷል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
እሁድ እንዴት እያለፈ ነው?

የለኩ ወጣቶች ቀኑን በበጎ ስራ እያሳለፉት እንደሚገኙ ነግረውናል፦

*የለኩ እኔም ለወገኔ የበጎ አድራጎት ማህበር በከተማውና በሸበዲኖ ወረዳ ከሚገኙ 12 ቀበሌዎች ላይ ያሉ እጅግ የተቸገሩ 60 አረጋዊያንን እና ከ 200-500 ሚደርሱ ተማሪዎችን በመርዳት ላይ የሚገኝ ማህበር ሲሆን ለ 2012 ከህዝብ ከሚሠበሠብ ገንዘብ በተጨማሪ የተለያዩ ገቢ ማስገኛዎችን በመንደፍ በእንቅስቃሴ ላይ ይገኛል ዛሬም ቡና ና ሊስትሮ በመጥረግ ላይ እንገኛለን። ስለሆየም ሁላችንም ከተረፈን ሳይሆን ካለን ነገሮች ላይ በማካፈል ከጎናችን እንድትቆሙልን ስንል በትህትና እንጠይቃለን!"

0939467113
0916336699
0985099944

@tsegabwolde @tikvahethiopia
እሁድ እንዴት እያለፈ ነው?

የኢትዮጵያ ቡና ደጋፊዎች ቀኑን ለወገናቸው ደም በመለገስ እያሳለፉ ይገኛሉ። ሶስት ቁጥር ማዞርያ ቶታል አካባቢ የሚገኙ ደጋፊዎች!

"ስንደመር ያምርብናል፤ በደማችን ሰው ይድናል"

ፎቶ📸Buna Gebya
@tsegabwolde @tikvahethiopia
እሁድ እንዴት እያለፈ ነው?

#ባይሽ_ኮልፌ

"እኛ ደግሞ ለ18 አመታት ጫካ ውስጥ ትኖር የነበረችውን እናት የቀበሌ ቤት ተሰጥቷ አድሰንላት ቤት አስገብተናት አብረናት እያሳለፍን ነው"

"ከእንግዲህ ብሞትም አይቆጨኝም!" እማማ አስቴር መንግስቱ

እናታችን ወደ ቤታቸው ሲገቡ በደስታ አልቅሰዋል! በሆነዉ ሁሉ ተገርመዋል። እንዲህም አሉን"ልጄ ዉሀ ላይ እየተኛ ሞራሉ ተነክቶአል። ትምህርቱን እንኳን እንደ #ጏደኞቹ ጠንክሮ #መማር አልቻለም አሁን ግን ቤት አለዉ #ብሞትም አይቆጨኝም። እኛን እንዳስደሰታችሁ ፈጣሪ እናንተን ያስደስትልኝ!" ከዚህ በላይ ደስታ የት አለ? "ኑ ለመልካም ስራ ረፍዶ አያውቅም!!!"

#ባይሽ_ኮልፌ

@tsegabwolde @tikvahethiopia
እሁድ እንዴት እያለፈ ነው?

በወላይታ ዞን ቦዲቲ ከተማ የሚገኙ ወጣቶች እና የከተማ ነዋሪዎች እሁድን ለወገኖቻቸው ደም በመለገስ እያሳለፉ እንደሚገኙ ነግረውናል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሓደ ጥማር ንሓደ ህፃን
አንድ እሽግ ለአንድ ህፃን
One Pack For One Child


ኮኸብ ፅባሕ መተሐጋገዝን መረዳድእን ሰገናት ማሕበር - #መቐለ, #ትግራይ

📞0914271942
📞0914708858

@tsegabwolde @tikvahethiopia
"ወጣቶች የስደትን መራራነት ተረድተው ከስደት መታቀብ አለባቸው"–በሱዳን ተመላሽ ስደተኞች #ETHIOPIA

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ የንግስት እሌኒ መ/መ/ሆስፒታል ድንገተኛ ጉብኝት አደረጉ!

የኢፌዴሪ ሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳዮች ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ ከሌሎች የፌዴራል እና የዞን አመራሮች ጋር በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ስር የሚገኘውን የንግስት እሌኒ መ/መ/ሆስፒታል ድንገተኛ ጉብኝት አደረጉ፡፡ በጉብኝቱ ወቅት ዶ/ር ሐብታሙ አበበ የዩኒቨርስቲው ፕሬዝዳንት እና ዶ/ር አያኖ ሻንቆ በም/ፕሬዝዳንት ማዕረግ የሆስፒታሉ ቺፍ ኤክስኪዩቲቭ ዳይሬክተር እየተጠናቀቁ ያሉ ግንባታዎች ላይ ለድንገቴ ክቡራን እና ክቡራት ጎብኝዎች ገለፃ እና ማብራሪያ ሰጥተዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ማህበረሰብ ተስፋ ሲቆርጥ ምን ይፈጠራል?

"...እንደ ህዝብ ደግሞ ህዝብ ተስፋ ከቆረጠ እሴቶቹን ይጥላል፤ ነገ ለውጥ የለም፤ ምንም ተስፋ የለንም ብሎ ካሰበ፤ ይጋደላል፣ ይሰዳደባል፣ ተስፋ የቆረጠ ሰራዊት ልታይ ትችላለህ ፌስቡክም ላይ ሚዲያም ላይ፤ ህዝብ ተስፋ ከቆረጠ መከባበሩ ይጠፋል፤ ትህትናው ይጠፋል፤ ፍቅሩ ይጠፋል፤ ሚታየው ነገር የለም። ሰውን ስነ ስርዓት ከሚያሲዙትና እሴቶቹን ጠብቆ እንዲኖር ከሚያደርጉት ነገሮች አንዱ ነገ መልካም ይሆናል የሚል #ተስፋ ነው" ዶክተር #ወዳጄነህ_ማሀረነ

#HOPE #TIKVAH/#ተስፋ/

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#FakeTelegramChannel ይህ "ልዩ መረጃ ከኤልያስ ጋር" የሚለው ገፅ ሀሰተኛ ነው። ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት "ልዩ መረጃ" በሚል ምንም አይነት የፌስቡክ ገፅም ሆነ የቴሌግራም ቻናል እንደሌለኝ እወቁልኝ ብሏል። ለቴሌግራም Report እንድታደርጉም ጥሪ እናቀርባለን።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር!

የተማሪዎችን ብቃት፣ ክህሎትና ተግባቦት በማጠናከር አጠቃላይ የትምህርት ጥራትን ለማሻሻል ያስችላሉ ተብሎ የታመነባቸው አዳዲስ የትምህርት ዓይነቶች (ኮርሶች) በሁሉም ዩኒቨርስቲዎች ከመጪው ዓመት ጀምሮ የሚሰጥ መሆኑን የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ። በዚህም መሰረት ቀደም ሲል በሶሰት ዓመት ይጠናቀቅ የነበረው የመጀመሪያ ዲግሪ መደበኛ ትምህርት መርሃ ግብር ወደ አራት ዓመት ከፍ እንዲል ይደረጋል ተብሏል።

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-08-18

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ላለፉት ሁለት ቀናት በአሶሳ ከተማ ሲካሄድ የቆየው የቤኒሻንጉል ጉሙዝ እና የአማራ ክልሎች የጋራ የሰላምና የልማት መድረክ የጋራ የልማትና የሰላም ስምምነት በመፈረም ተጠናቋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ፓስፖርት

ከዚህ ቀደም ፓስፖርት ለማግኘት ይጠየቅ ነበረው የድጋፍ ደብዳቤ ቀርቶ በመታወቂያና በልደት የምስክር ወረቀት መሰጠት መጀመሩን የኢሚግሬሽን፣ ዜግነትና ወሳን ኩነት ኤጀንሲን ገልጿል። ከዚህ በኋላም ፓስፖርት ለመውሰድ ጥያቄ የሚያቀርቡ ግለሰቦች ሕጋዊ መታወቂያና የልደት የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው ተብሏል፡፡

ፓስፖርት በአስቸኳይ ለሚፈልጉ ሰዎችም ከ3 እስከ 5 በሚደርሱ ቀናት ውስጥ ምላሽ እንደሚያገኚ ኤጀንሲው የገለጸ ሲሆን በመደበኛ ጊዜም ሆነ በአስቸኳይ ፓስፖርት ለማደስ እና አዲስ ለመጠየቅ ሕጋዊ መታወቂያና የልደት የምስክር ወረቀት መያዝ እንደሚያስፈልግ ተነግሯል።

ይህ አሰራርም ዜጎች የልደት የምስክር ወረቀት እንዲኖራቸው እንዲሁም ሕገ ወጥ መታወቂያዎችን ለመከላከል የልደት የምስክር ወረቀቱ እንደሚያግዝ ተገልጿል። ከዚህ ቀደም ፓስፖርትን ያለ አሳማኝ የድጋፍ ደብዳቤ መስጠት ተከለከለበት ምክንያት ሕገ ወጥ ስደትን ለመከላከል ሲሆን የውጪ ምንዛሪ እጥረትም ሌላኛው ምክንያት እንደነበር የኤጀንሲው ገልጾ ነበር።

ምንጭ፦ ቢቢሲ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የፀሎት ቀን!

በአገር አቀፍ ደረጃ የዕርቅ መንፈስ እንዲመጣ ለማስቻል ጳጉሜን 1 ቀን 2011 ዓ.ም. ከኢትዮጵያ ሃይማኖቶች ጉባዔ ጋር በመተባበር የፀሎት ቀን ለማድረግ ዝግጅቱን ማጠናቀቁን ብሔራዊ የዕርቀ ሰላም ኮሚሽኑ አስታውቋል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
እኛ እንደ TIKVAH-ETH ቤተሰብ 6710 ላይ መልዕክት በመላክ የልብ ህሙማን ህፃናትን አለንላችሁ እንበላቸው!! በቤተሰባችን ምን ያህል አስተዋፅኦ እናደርጋለን??

የTIKVAH-ETH ቤተሰቦች በትንሹ 20,000 ሆነን 3 መልዕክት ብንልክ 60,000 ብር በአንድ ምሽት አስተዋፆ ማድረግ እንችላለን!!

እኔ ካለኝ ላይ አካፍያለሁ?? እናተስ??

ለአንድ መልዕክት የሚቆርጠው 1 ብር ብቻ ነው!!

@tsegabwolde @tikvahethiopia