TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.7K photos
1.44K videos
207 files
3.98K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
🇪🇹 #NationalDialogue 🇪🇹

የመጅሊሱ ቅሬታ ምንድነው ?

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት ህዝበ ሙስሊሙ ሀገራዊ ምክክሩን እጅግ እንደሚደግፈው ነገር ግን ከምክክሩ ተሳታፊዎች ጋር በተያያዘ ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽ እንዳልተሰጠው በዚህም ምክንያት ቅሬታ እንዳደረበት ገልጿል።

ም/ቤቱ ያደረበት ቅሬታ " በምክክሩ ላይ የሙስሊሞች ውክልና አነስተኛ ነው ፤ ይህ ደግሞ በምክክር ውጤቱ ላይ ተጽእኖ እንዳያሳድር ስጋት አለኝ " የሚል ነው።

" #ከወረዳ እስከ #ክልል ድረስ የሚሳተፉት ተወካይ ሙስሊሞች ቁጥር እጅግ አነስተኛ ነው " የሚለው ም/ቤቱ ፥ " እንደ ሙስሊም በጋራ ሀገራዊ አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ መግባባት ላይ ለመድረስ በቂ ተወካዮች አልተወከሉም " ብሏል።

የምክር ቤቱ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ከማል ሀሩን ምን አሉ ? (ለሃሩን ሚዲያ)

- ሙስሊሙ ከምንም በላይ ምክክሩን ይፈልገዋል።

- ሙስሊሙ የቆዩ ችግሮች ስላሉበት ይሄን ምክክር እንዲሳካ በጣም ከሚደግፉት ማህበረሰብ ክፍሎች ዋነኛው ነው።

- ከሌሎች እምነቶች ሲነጻጸር ሙስሊሙ ማህበረሰብ ለዚህ ምክክር ያለው ድጋፍ ፈጽሞ ሊወዳደር የሚችል አይደለም። ሙስሊሙ ይህንን ምክክር የሚፈልገው ያልተመለሱለት ጥያቄዎቹ እንዲመለሱለት ነው።

- ተወካዮች ከታች ሲመረጡ ሙስሊሙ ማህበረሰብ ተሳታፊ እንዲሆን ያስፈልጋል። ኮሚሽኑም check and balance ማድረግ አለበት ፤ በትክክልም የዚህን ማህበረሰብ ጥያቄዎች የሚያነሱ ተወካዮች ተወክለዋል የሚለውን።

- የተሳታፊዎች ልየታ ከታች ጀምሮ ሲመጣ በትክክል ሁሉም ማህበረሰብ መወከሉን ማረጋገጥ ይገባል። ኮሚሽኑም ከሌሎች እምነቶች ጋር balance የማድረግ ስራ ይጠበቅበታል።

- ተሳትፎ ላይ ቁጥሩ የተዛባ ከሆነ፣ በጣም አነስተኛ ከሆነ ቅሬታ ስለሚያስከትል ጥንቃቄ ያስፈልጋል።

- ኮሚሽኑ አካሄድ የነበረው ሲቪል ማህበራት፣ ሴቶች፣ ወጣቶች፣ መምህራን ፣ አርብቶ አደሮች፣ እድሮች፣ የፍትህ አካላት፣ የመንግሥት ሰራተኞች፣ ፖለቲከኞች የያዘ ነው በሃይማኖት መልክ ግን የቀረበ ነገር የለም። እነዚህ አደረጃጀቶች ምን ያህል ሙስሊሙ ተሳትፎ አለው ? የሚለው ያሳስበናል፤ ስጋትም አድሮብናል።

- የተነሱ ጥያቄዎችን እና ያሉትን ስጋቶች በተደጋጋሚ ለኮሚሽኑ ቀርበው የጋራ ኮሚቴ ጭምር እንዲቋቋም መረጃዎችም እንዲሰጡ ተጠይቆ በተለያየ ምክንያት ሊሳካ አልቻለም።

- ውይይቶች አድርገናል በተደጋጋሚ ፤ በውጤቱ ላይ የሙስሊሙን ተሳትፎ የሚያሳዩ መረጃዎች (ዳታ) ማግኘት አልተቻለንም።

- እንደ አጀንዳ የሙስሊሙ ማህበረሰብ ጥያቄዎች በ9 አጀንዳዎች ተካተው ፣ በ47 ጥያቄ ቀርቦ የካቲት 2 ላይ ለኮሚሽኑ ቀርቧል። መጨረሻ ላይ ኮሚሽኑ ያንን የማስፈጸም ኃላፊት አለበት።

- ታች ያለው የማህበረሰቡ ውክልና በተሻለ ሁኔታ ሁሉ የሃይማኖት ተቋማት ባገናዘበ፣ ሃይማኖት ተቋማትን balanced ባደረገ ሁኔታ መታየት አለበት ቁጥሩ። ለምሳሌ ፦ ከ12 ሺህ ምን ያህል ሙስሊም ተካቷል ፤ ከአዲስ አበባም ከ2500 ተሳታፊ ካለ ምን ያህል ሙስሊም ተሳታፊ ነው ? የሚለው ነው የማህበረሰቡ ጥያቄ።

- እኛ በቂ መረጃዎች የሉንም ለማህበረሰቡ ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት አስቸጋሪ ነው። በአንዳንድ ሁኔታ ስናጣራ በጣም አነስተኛ ቁጥር ያለበት ስለሆነ የተሻለ ውጤት እንዲገኝ ጥያቄ በማያስነሳ መንገድ እንዲሄድ ማድረግ ይገባል።

- የሙስሊሙ ማህበረሰብ ተሳታፊ ቁጥር አነስተኛ ከሆነ የሚቀርበው አጀንዳ ይቀራል ፤ ያ ደግሞ እጅጉን ያሳስበናል።

- በእኛ በኩል አሁንም ምላሽ እየጠበቅን ነው።

#EthiopianMuslims
#HarunMedia
#NationalDialogue

@tikvahethiopia