TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.3K photos
1.47K videos
209 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
አሳዛኝ ዜና‼️

በወረታ ከተማ የአደጋ መከላከያ እህል ክምችት መካዝን አካባባቢ በደረሰ #የትራፊክ_አደጋ የሰው ህይወት አለፈ።

በትላንትናው ዕለት ከጎንደር ወደ ባ/ዳር ሲጓዝ የነበረ የሰሌዳ ቁጥር ET 78608 የሆነ ዳንጎቴ የከባድ ጭነት መኪና መንገዱን በመሳት ከወረታ ወደ ወርቅ ሜዳ ሲጓዝ ከነበረ የሰሌዳ ቁጥሩ 23141 ከሆነ ባጃጅ ጋር #በመጋጨቱ ከባጃጁ ውስጥ ሆነው ሲጓዙ ከነበሩት 5 ተሳፋሪዎች መካከል 2ቱ ወዲያውኑ ህይወታቸው አልፏል።

በአደጋው 1 ሰው ከባድ ጉዳት የደረሰበት መሆኑንና ወዲያዉኑ ወደ ፈለገ ህይወት ሆስፒታል በአንቡላንስ መላኩንና 2ቱ ደግሞ ቀላል ጉዳት ደርሶባቸው በወረታ ከተማ ጤና ጣቢያ እየተረዱ መሆናቸውን የወረታ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽ/ቤት ከስፍራው መዘገቡን የጽ/ቤቱ የህዝብና ሚዲያ ግንኙነት የለውጥ ቡድን መሪ አቶ ኃይሌ ብርሃኔ አስታውቀዋል።

ምንጭ፦Woreta city communication affairs(Mulusew)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አሳዛ ኝ ዜና‼️

በምስራቅ ወለጋ ዞን ጊዳ አያና በህዝብ ማመላለሻ አውቶብስ ላይ በደረሰ #የትራፊክ_አደጋ የ16 ሰዎች ህይወት ማለፉ ተገለፀ።

በኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን የትራፊክ ቁጥጥር ደህንነት የሥራ ሂደት ከፍተኛ ባለሙያ ኮማንደር ንጉሴ ግርማ ለfbc እንደተናገሩት፥ አደጋው በትናነትናው እለት ነው የህዝብ ማመላለሻ ኤፍ.ኤስ.አር ተሽከርካሪ ተገልብጦ የደረሰው።

የህዝብ ማመላለሻ አውቶብሱ ላይ በደረሰው የመገልበጥ አደጋም የ16 ሰዎች ህይወት ወዲያውኑ ሲያልፍ 10 ሰዎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት እንዲሁም 5 ሰዎች ላይ ደግሞ ቀላል ጉዳት መድረሱንም ኮማንደር ንጉሴ አስታውቀዋል።

ምንጭ:- fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
‹‹ከከሰልና #እንጨት ጋር አብረን እንድንጓዝ ተገደናል፡፡›› ነዋሪዎች
.
.
በኦሮሞ ብሄረሰብ አስተዳደር ከከሚሴ በደዌ ሃረዋ በሚወስደዉ መንገድ ነዋሪዎች በትራንስፖርት ችግር #እንግልት እየደረሰባቸዉ ነዉ፡፡ የሚመደቡ የህዝብ ማመላለሻ አዉቶብሶች በቂ ባለመሆናቸዉ በአንድ አዉቶብስ ከ100 እስከ 120 ሰዎች እንደሚጓጓዙ የአካባቢዉ ነዋሪዎች ተናግረዋል።

የአካባቢዉ ህብረተሰብ እንደ አማራጭ #የጭነት መኪኖችን ለመጓጓዣነት እየተጠቀመባቸዉ ነዉ፡፡ የአካባቢዉ የትራንስፖርት ችግር ነዋሪዎችን በአይሱዙ መኪኖች ከከሰልና እንጨት ጋር አብረዉ እንዲጓዙ አስገድዷቸዋል፡፡ ለትራፊክ አደጋ #እያጋለጣቸዉ መሆኑን ነዋሪዎቹ ተናግረዋል፡፡

ለአብነት በቅርቡ በደረሰ #የትራፊክ_አደጋ የ12 ሰዎች ህይወት ማለፉን ተሰምቷል፡፡ የደዌ ሃረዋ ትራፊከ ፖሊስ ምክትል ሳጅን መሃመድ ጀማል ህብረተሰቡ የሚያስፈልገዉን የትራንስፖርት አገልግሎት እያገኘ አለመሆኑ ይታወቃል በተደጋጋሚ ትርፍ የሚጭኑትን አሽከርካሪዎች እየቀጣን ነዉ፣ ሆኖም መፍትሄ አልመጣም ብለዋል፡፡ የኦሮሞ ብሄረሰብ አስተዳደር ተቀዳሚ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አህመድ ሃሰን በብሄረሰብ አስተዳደሩ የሚታየዉን የትራንስፖርት ችግር ለመፍታት ግብረ ሃይል ተቋቁሞ እንቅስቃሴ መጀመሩን ገልፀዋል፡፡

ምንጭ፦ አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አሳዛኝ ዜና‼️

በኦሮሚያ ክልል በቦረና ዞን #ያአበሎ_ወረዳ በደረሰ #የትራፊክ_አደጋ ከ15 በላይ ሰዎች ህይወት ማለፉ ተገለፀ።

የተሽከርካሪ አደጋው ያጋጠመው ከኦሮሚያ ክልል ቦረና ዞን ያአበሎ ከተማ ወደ ደቡብ ክልል #ኮንሶ ከተማ #ኮንትሮባንድ_ጭኖ በፍጥነት ሲጓዝ የነበረ ተሽርካሪ ከተቃራኒ አቅጣጫ ከሚመጣ ከባድ የጭነት ተሽከርካሪ ጋር በመጋጨቱ ነው።

በያአበሎ ወረዳ ኛሮ ቀበሌ ኤላ ዲማ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በደረሰው የትራፊክ አደጋም ከ15 በላይ ሰዎች ህይወት ማለፉን ከቦረና ዞን የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት የተገኘው መረጃ ያመለክተታል።

ምንጭ፦ ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETH ማጠቃለያ🗞የካቲት 12/2011 ዓ.ም.

የኢትዮጵያ ሰማዕታት ቀን 82ኛ ዓመት የመታሰቢያ ስነ ስርዓት በዛሬው እለት ተካሂዷል። መታሰቢያ ስነ ስርዓቱ በተለይ 6 ኪሎ በሚገኘው የኢትዮጵያ ሰማእታት አደባባይ ከማለዳው ጀምሮ በተለያዩ ስነ ስርዓቶች ነው የተካሄደው።
.
.
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከጣልያኑ ትጥቅ አምራች ኩባንያ ኤሬአ ጋር የነበረውን ስምምነት ቀይሮ ከእንግሊዙ አምብሮ ኩባንያ ጋር የአራት አመት የትጥቅ ልብስ ማቅረብ ስምምነት ተፈራርሟል።
.
.
በአማራ ክልል የተፈናቀሉ ወገኖችን ለማቋቋም የክልሉ መንግስት ያደረገውን ጥሪ ተከትሎ #ጥረት_ኮርፖሬሽን የ10 ሚሊዮን ብር የመጀመሪያ ድጋፍ ማድረጉን ገልጿል።
.
.
ግሎባል አልያንስ ከምዕራብና ማዕከላዊ ጎንደር #ለተፈናቀሉ 46ሺ ለሚሆኑ ዜጎች 20ሺ የአሜሪካን ዶላር ወይንም በኢትዮጵያ 6 መቶ ሺ ብር #መለገሱን አስታውቋል።
.
.
በፌደራል ስርዓቱ ላይ ከማንም ጋር #ለድርድር እንደማይቀመጥ የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኦዲፒ) አስታውቋል። ፓርቲው በትናነትናው እለት ባወጣው መግለጫው፥ ኦዲፒ በአጀንዳነት ይዞ ከሚታገልባቸው ጉዳዮች ውስጥ ዋነኛው የፌደራል ስርዓቱ ነው ብሏል።
.
.
በኦሮሚያ ክልል በቦረና ዞን #ያአበሎ_ወረዳ በደረሰ #የትራፊክ_አደጋ ከ15 በላይ ሰዎች ህይወት ማለፉ ተገልጿል።
.
.
“ጉዞ ሉሲ ለሰላምና ለፍቅር” የሽኝት መርሃ ግብር ከነገ በስቲያ በይፋ እንደሚካሄድ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አስታውቋል።
.
.
ከነገ በስቲያ/ሀሙስ የካቲት 14/2011 ዓ.ም. የሲዳማ ሪፈረንደም ሰልፍ አስተባባሪ ኮሚቴ በሀዋሳ ከተማ የጠራው #ሰላማዊ_ሰልፍ በመንግስት ፍቃድ አግኝቷል።
.
.
ጥቅምት 4/2011 ዓ/ም ድምፃዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን (#ቴዲ_አፍሮ) በሚሊኒየም አዳራሽ ያቀረበው የሙዚቃ ዝግጅት ደረጃውን በጠበቀ የድምፅ እና የምስል ጥራት #በዲቪዲ የፊታችን ቅዳሜ የካቲት 16 ለገበያ ይቀርባል ተብሏል።
.
.
#የኤርትራ ፐብሊክ ዲፕሎማሲና የባህል ልኡክ አባላት #ከሀዋሳ_ከተማ ነዋሪዎች ጋር #ተወያይተዋል
.
.
ድሬዳዋ ውስጥ በዓመት 3 ነጥብ 5 ሚሊዮን ቶን ማዳበሪያ የሚያመርት ፋብሪካ #ሊገነባ መሆኑን የኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ተገልጿል።
.
.
#ቂሊንጦ_ማረሚያ_ቤት ላይ በደረሰው ቃጠሎ በተነሳው ረብሻ ምክንያት የሰብአዊ መብት ጥሰት ፈፅመዋል በሚል የተጠረጠሩ የማረሚያ ቤት የፖሊስ አባላት ላይ ክስ ተመስርቷል።
.
.
በኢፌዲሪ ጠቅላይ አቃቤ ህግ የሁለተኛ ዙር የ100 ቀን ዕቅድ ዝግጅት አጠናቆ ወደ ስራ መግባቱን የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተርሩ አቶ #ዝናቡ_ቱኑ አስታውቀዋል።
.
.
የሱማሊያ ጫት ነጋዴዎች ከኬንያ ጫት ማስገባታቸውን ትተው #የኢትዮጵያን_ጫት ለመግዛት መወሰናቸውን የሀገሪቱ መገናኛ ብዙኻን ዘግበዋል፡፡
.
.
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር #ወርቅነህ_ገበየሁ በኢትዮጵያ የእንግሊዝ አምባደሳደር ዶ/ር #አላስቴይር_ዲቪድ ማክፌይል በዛሬው ዕለት የካቲት 12 ቀን 2011 ዓ.ም በጽ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።
.
.
በምዕራብ ወለጋ ዞን በነበረው #አለመረጋጋት የተዘረፉ የጦር መሣሪያዎችና ንብረቶች #ተመለሱ። በዞኑ ሁሉም የመንግሥት መዋቅሮችና አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ወደ መደበኛ ሥራቸው መመለሳቸውም ተገልጿል።
.
.
የለገጣፎ ለገዳዲ ከተማ አስተዳደር በህገወጥ መንገድ ተገንብተዋል ያላቸውን መኖሪያቤቶች ማፍረስ ጀምሯል።
.
.
በምዕራብ ወለጋ ዞን የኦነግ አባላት ህዝቡን #እየተቀላቀሉ ሲሆን፣ በዞኑ፣ መነ ሲቡ ወረዳ አቀባበል እየተደረገላቸው ይገኛል።
.
.
በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ህዝባዊ ተሳትፎ ብሄራዊ አስተባባሪ ምክር ቤት ጽህፈት ቤት እና በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በጋራ የተዘጋጀው የእግር ኳስ ውድድር ከየካቲት 22 እስከ 24 ቀን 2011 ዓ.ም በአዲስ አበባ ይካሄዳል።

ምንጭ፦ ኢዜአ፣ ኢ.ፕ.ድ፣ fbc፣ etv፣ ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት፣ wazemaradio፣ የጀርመን ራድዮ

@tsegabwolde @tikvahethiopia
አዲስ አበባ🔝

ከላይ በፎቶው የምትመለከቱት አዲስ አበባ #ካዲስኮ_አካባቢ እየተሰራ ያለ ግንባታ ነው። የህንፃ ግንባታው #የእግረኛ_መንገድ_እንዲዘጋ ምክንያት ሆኗል፤ የሚመለከተው አካል ሊደርስ የሚችለውን #የትራፊክ_አደጋ ከግንዛቤ በማስገባት የእርምት እርምጃ ቢወስድ መልካም ነው እንላለን።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
አሳዛኝ ዜና‼️

በኦሮሚያ ክልል በምስራቅ ወለጋ ዞን በደረሰ #የትራፊክ_አደጋ የ11 ሰዎች ህይወት ማለፉ ተገለፀ።

የትራፊክ አደጋው በትናንትናው እለት የደረሰ መሆኑን ከምስራቅ ወለጋ ዞን የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

#ከነቀምቴ ከተማ ወደ #ሲቡ_ስሬ ወረዳ 22 ሰዎችን አሳፍሮ ሲጓዝ የነበረ ሚኒባስ ተሽከርካሪ ጪንጊ በተባለች ከተማ አቅራቢያ በመገልበጡ ነው አደጋው የደረሰው።

በትራፊክ አደጋውም በሚኒባስ ተሽከርካሪው ተሳፍረው ሲጓዙ ከነበሩ 22 ሰዎች ውስጥ የ11 ሰዎች ህይወት ማለፉ ነው የተገለፀው።

ምንጭ፦ Fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የትራፊክ አደጋ...

#አርባምንጭ

በአርባምንጭ ከተማ #በዛሬው_ዕለት በደረሰ #የትራፊክ_አደጋ የሰው ህይወት ማለፉ ተሰምቷል።

Via Gamo Zone Administration public Relation office

•ወገኖቼ መነጋገር አለብን! እንደወጣን እየቀረን ነው! በየቦታው በየከተማው በትራፊክ አደጋ ብዙ ዜጎቻችን እያለቁ ነው።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አሳዛኝ ዜና‼️

በደቡብ ክልል ሲዳማ ዞን ጊርኛአዶ ወረዳ በደረሰ #የትራፊክ_አደጋ የ13 ሰዎች ሕይወት አለፈ፡፡ የ13 ሰዎችን ህይወትን ለቀጠፈው አደጋ መንስኤም ሰራተኞችን ጭኖ ወደ ጫት ማሳ በመጓዝ ላይ የነበር የጭነት አይሱዚ በመገልበጡ እንደሆነ ተገልጿል፡፡

በዚሁ አደጋ አራት ሰዎች ላይ ከፍተኛ የአካል ጉዳት የደረሰ ሲሆን÷ በቦና ሆስፒታል ክትትል እየተደራገላቸው ይገኛል፡፡

የሲዳማ ዞን ፓሊስ መምሪያ የትራፊክ አደጋ መቆጣጠር የስራ ሂደት ባለቤት ኢንስፔክተር ሀኃይሉ ታፈሰ እንደገለጹት÷ ተሽካርካሪውን ረዳቱ ይዞት የነበርና ከፍጥነት በላይ ሲያሸከረክር አደጋው ደርሷል፡፡ ረዳቱ መንጃ ፈቃድ እንዳልነበረውም ነው ኢንስፔክተር ሀኃይሉ የገለጹት፡፡

Via #FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia