TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.7K photos
1.49K videos
211 files
4.06K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ወላይታ ዞን ፖሊስ‼️

የህብረተሰቡን ሰላምና ፀጥታን #ለማስከበር ከመቼውም ጊዜ #በተጠናከረ ሁኔታ እየሠራ መሆኑን የወላይታ ዞን ፖሊስ መምሪያ አስታውቋል፡፡

የወላይታ ዞን ፖሊስ መምሪያ ኃላፊ ምክትል ኮማንደር #ኤፌሶን¥ላካይቶ እንደገለጹት በዞኑ የፀጥታ ሁኔታ ለማረጋገጥ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሠራ ነው፡፡

ባለፉት ሶስት ወራት በተለያዩ የስርቆትና ንጥቂያ ወንጀል የተጠረጠሩና እጅ ከፍንጅ የተያዙ በቁጥር 50 የሚሆኑ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተካሄደባቸው ይገኛል ብለዋል።

በዞኑ ዜጎች በሰላም ወጥተው በሰላም እንዲገቡ ለማድረግና የህግ የበላይነት እንዲከበር ለማስቻል መምሪያው ከህብረተሰቡ ጋር በመቀናጀት ሰፊ ሥራ እያከናወነ ይገኛል፡፡

ሀገሪቱ በለውጥ ጎዳና ላይ ከመሆኗ ጋር ተያይዞ ለውጡን የማይቀበሉ አንዳንድ አካላት በሚፈጥሩት የፀጥታ መደፍረስ የተለያዩ የስርቆትና ንጥቂያ ወንጀሎች እየተበራከቱ በመሆናቸው ችግሮችን ለመቅረፍ የፀጥታ አካላትን ያሳተፈ ጊዜያዊ ግብረ ኃይል መቋቋሙንም ተናግረዋል፡፡

በዞኑ የሚፈጸሙ #የስርቆትና #የንጥቂያ ወንጀል #በዘላቂነት ለመከላከል በየደረጃው የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎችን የማወያየትና በወንጀሉ የተጠረጠሩ ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር የማዋል ሥራዎች እየተከናወኑ ይገኛሉ ብለዋል፡፡

በጉኑኖ ከተማ አስተዳደር በህገ ወጥ መንገድ ሌሊት ባለሁለት እግር ሞተር ብስክለት አሽከርካሪዎችን ለመቆጣጠር ፖሊስ ያደረገውን ጥረት ጥቂት የሞተር ብስክለት አሽከርካሪዎች ‹‹እኛን መቆጣጠር አትችሉም›› በማለት ሁከት ፈጥረው እንደነበር አስታውሰዋል፡፡

ከዚህ ጋር በተያያዘ የተፈጠረውን ሁከት ፖሊስ ከከተማው ህብረተሰብ ጋር በመቀናጀት #በቁጥጥር ስር ለማዋል መቻሉን ኃላፊው ገልፀዋል፡፡

በከተማው ሁከት የፈጠሩ፣ የተሳታፉና የመሩ በቁጥር 30 የሚሆኑ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለው ህጋዊ የምርመራ ሂደት መጀመሩን ጠቁመዋል፡፡

በሶዶ ከተማ አራዳ ክፍለ ከተማ በቡድን ተደራጅተው #በስርቆት ወንጀል የተሰማሩ 9 ግለሰቦች ለህግ ቀርበው ተገቢ ውሳኔ እንዲያገኙ የተደረገ ሲሆን በዋዱ አከባቢም በተመሳሳይ ወንጀል ተሰማርተው የነበሩ 9 ተጠርጣሪዎች በህግ ቁጥጥር ስር ውለው ምርመራው #መጠናቀቁን ተናግረዋል፡፡

በተለይ የባለሁለት እግር ሞተር ብስክለት አሽከርካሪዎች ከምሽቱ 12 ሰዓት በኋላ ማሽከርከር እንደሌለባቸው ያሳሰቡት ምክትል ኮማንደር ኤፌሶን ሌሊት ማሽከርከር ለተለያዩ አደጋዎች የሚያጋልጥ በመሆኑ ህብረተሰቡ ተገቢ ጥንቃቄ ማድረግ አለባቸው ብለዋል፡፡

በየአካባቢው ህብረተሰቡ ከወትሮው የተለየ የፀጥታ ችግር ሲያጋጥም ለዞኑ ፖሊስ በ046-551-21-26፣ ለሶዶ ከተማ ፖሊስ 046-551-01-46፣ ለሶዶ ዙሪያ ወረዳ ፖሊስ 046-551-00-22 የስልክ ቁጥሮችን በመጠቀም ጥቆማ መስጠት እንደሚችሉ ገልጸዋል፡፡

ምንጭ፦Wolaita ZONE Culture,tourisim and Governmental Communication Affairs Office
@tsegabwolde @tikvahethiopia