TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.3K photos
1.47K videos
209 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የኢንተርኔት አገልግሎት ቢመለስም ቴሌግራም አሁንም እየሰራ እንዳልሆነ ከTIKVAH-ETH ጎብኚ ቁጥር መረዳት ተችሏል። ከሌሎች በተለየ መልኩ የቴሌግራም መቋረጥን በተመለከት እስካሁን ከመንግስት አካል የተባለ ነገር የለም።

ለማንኛውም ቴሌግራም ላስቸገራችሁ የቤተሰባችን አባላት...

https://t.iss.one/proxy?server=russia-dd.proxy.digitalresistance.dog&port=443&secret=ddd41d8cd98f00b204e9800998ecf8427e

እንዲሁም...

√Psiphon
√Opera VPN በስልካችሁ ላይ በመጫን #ቴሌግራም መጠቀም ትችላላችሁ!

@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የ2ተኛው ቀን የ12ኛ ክፍል ፈተና ዛሬ ተሰጥቷል። የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ትላንት የካቲት 29 ቀን 2013 ዓ/ም መጀመሩ ይታወቃል። በዛሬው ዕለት የ2ኛው ቀን ፈተና በመላ ሀገሪቱ ሲሰጥ ውሏል። ከፈተናው ሂደት ጋር በተያያዘ የተለያዩ አስተያየቶች ከተማሪዎች እና ከተማሪ ወላጆች እያደረሱን ይገኛሉ። አንዳንድ ተማሪዎች ስልክ ይዞ የመገኘትም ነገር እንደነበረ ተፈታኞች ለቲክቫህ እያሳወቁ ነው።…
#Telegram

ቴሌግራም ኢትዮጵያ ውስጥ ለሰዓታት ተቋርጦ ነበር።

ዛሬ ጥዋት #ቴሌግራም ተቋርጦ እንደነበር ለማወቅ ተችሏል። አገልግሎቱ የ12ኛ ክፍል ፈተና ማብቃት ከታወቀ በኃላ ተመልሷል።

ምንም እንኳን ዛሬ ሙሉ በሙሉ ቢቋረጥም ከትላንት ጀምሮ ፍጥነቱ ቀንሶ ፣ ፎቶዎች እና ቪድዮችን ለመለዋወጥ አስቸጋሪ ሆኖ ነበር።

ከ12ኛ ክፍል ፈተና ጋር በተያያዘ ከቀናት በፊት የተማሪ ወላጆች እና ተፈታኝ ተማሪዎች ያነሷቸውን ቅሬታ አጋርተን ነበር።

በአንዳንድ ቦታዎች የሞባይል ስልክ ይዘው ወደ መፈተኛ ክፍሎች የሚገቡ ተማሪዎች ፈተናውን ፎቶ በማንሳት በቴሌግራም የመስራት ሁኔታ እንደነበረ በቂ ማስረጃ እንዳላቸው የቲክቫህ አባላት የሆኑ ተማሪዎች እና ወላጆች መግለፃቸው አይዘነጋም።

ምንም እንኳን ቴሌግራም ከትላንት ጀምሮ ፍጥነቱ ቢቀንስም ፥ ዛሬ ደግሞ ሙሉ በሙሉ ቢዘጋም VPN በመጠቀም የዛሬውን ፈተና ከመፈተኛ ክፍል ውስጥ ፎቶ በማንሳት በሺዎች የሚቆጠሩ አባላት ባላቸው የቴሌግራም ግሩፖች ላይ የማሰራጨት ነገር እንደነበር ተስተውሏል።

የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና መጠናቀቅን ተከትሎ የትምህርት ሚኒስቴር በሰጠው መግለጫ ዘንድሮ የፈተና ስርቆትን ለማስቀረት 8 ፈተናዎች በ32 ስብጥር በማድረግ ኩረጃ እንዳይኖር ለመከላከል መሰራቱን አሳውቃል።

በተጨማሪ የዘንድሮ የ12ኛ ክፍል ፈተና በፍፁም እንዳልተሰረቀ አረጋግጣለሁ ብሏል ፤ በአንዳንድ የፈተና ጣቢያዎች ስልክ ይዘው የገቡ በጣም ጥቂት ተማሪዎች መኖራቸውን ግን ገልጿል ፤ ይህ ሁኔታ ከፈተና ኩረጃ ጋር የሚያያዝ እንጂ የፈተና ስርቆት ነው ማለት አያስችልም ብሏል የትህምርት ሚኒስቴር።

@tikvahethiopia
ትላንት የፌስቡክ ፣ ዋትስአፕ፣ ኢንስታግራምና ሜሴንጀር መቋረጥ ለሌሎች ተመሳሳይ አይነት አገልግሎት ለሚሰጡ መተግበሪያዎች ትልቅ በር ከፍቶ ነው ያለፈው።

ትዊትር በትላንትናው ዕለት በአንድ ጊዜ ከፍተኛ የሆነ የአገልግሎቱ ተጠቃሚዎች አስመዝግቧል።

ዛሬ ምሽት የቴሌግራም መስራች እንዲሁም ዋና ስራ አስኪያጅ ፓቬል ዱሮቭ ይፋ ባደረጉት መረጃ ፥ በአንድ ቀን ብቻ ከሌሎች ፕላትፎርሞች 70 ሚሊዮን አዳዲስ የቴሌግራም ተጠቃሚዎች ተመዝግበዋል።

ፓቬል ዱሮቭ ፤ አዳዲስ የቴሌግራም ተጠቃሚዎችን "ወደ ትልቁ #ነፃ የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ወደ #ቴሌግራም እንኳን በደህና መጡ" ብለዋል።

@tikvahethiopia
#Ethiopia

ባለፉት ቀናት በ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ምክንያት ተቋርጠው የነበሩት #ቴሌግራም እና #ፌስቡክ መሰል የማህበራዊ ትስስር መተግበሪያዎች ትላንት ፈተናው መጠናቀቁን ተከትሎ ወደ መደበኛ አገልግሎታቸው መመለሳቸውን ለማወቅ ተችሏል።

በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ኢትዮጵያ ውስጥ ሙሉ በሙሉ ኢንተርኔት እንደተዘጋ ተደርጎ የሚያሰራጨው መረጃ ሀሰተኛ ነው።

@tikvahethiopia
#ቴሌግራም

በተለያዩ የዓለም ሀገራት ሚገኙ የቴሌግራም መተግበሪያ ተጠቃሚዎች በአገልግሎቱ ላይ ችግር እንዳጋጠማቸው በ " ዳውን ዲቴክተር " በኩል በመግለፅ ላይ ይገኛሉ።

አንዳንዶች ሙሉ በመሉ አገልግሎት መቋረጥ ፣ አንዳንዶች ፎቶ እና ቪድዮ አለመላክ፣ አንዳንዶች የሚላኩላቸውን መልዕክቶች በአግባቡ አለመድረስ ፣ የአገልግሎት ፍጥነት መቀነስ የመሳሰሉትን ሪፖርት እያደረጉ ናቸው።

የአገልግሎት ፍጥነት መቀነስ ባለፉት ቀናትም ያጋጠማቸው ችግር መሆኑን ሪፖርት ያደረጉ አሉ።

እስካሁን ድረስ ድርጅቱ በተገልጋዮች በኩል ስለሚቀርቡት ችግሮች ምላሽ አልሰጠም።

ውድ የቲክቫህ አባል እርሶ ባሉበት ሀገር ከላይ ከተጠቀሳት መካከል ያጋጠሞት ችግር አለ ?

አዎ ! አለ
የለም

@tikvahethiopia
#ቴሌግራም

ቴሌግራም ዘንድሮም ልክ እንደ 2021 በመላው ዓለም ላይ በብዛት ዳውንሎድ ከተደረጉ ምርጥ አምስት (5) መተግበሪያዎች አንዱ መሆን ችሏል።

ቲክ ቶክ የ1ኛ ደረጃን ሲይዝ ፤ ኢንስታግራም ሁለተኛ ፣ ፌስቡክ ሶስተኛ ፣ ዋትስአፕ ደግሞ አራተኛ ደረጃን ይዘዋል።

ምንጭ፦ https://www.searchenginejournal.com/tiktok-most-downloaded-app-in-q1-2022/447790/

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ETHIOPIA ከትላንት ምሽት አንስቶ በኢትዮጵያ ቴሌግራም ፣ ፌስቡክ  እንዲሁም ሌሎች የማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎች እንዲገደቡ መደረጉ ታውቋል። አገልግሎቶቹ በሁለቱም የቴሌኮም አገልግሎት አቅራቢዎች ማለትም በኢትዮ ቴሌኮም እንዲሁም በሳፋሪኮም በኩል እየሰሩ እንዳልሆነ ለመረዳት ችለናል። ከማህበራዊ መገናኛዎቹ አገልግሎት መገደብ ጋር በተያያዘ በሌሎች ለአብነት በጎረቤት ሀገራት ውስጥ እስካሁን የታየ መቆራረጥ…
#Ethiopia

ከጥቂት ቀናት በፊት አገልግሎታቸው እንዲገደብ የተደረጉት የማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ዛሬም አገልግሎታቸው ወደ ቦታው እንዳልተመለሰ ለመረዳት ታችሏል።

#ቴሌግራም ጨምሮ ሌሎች የማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎች አገልግሎታቸው እንዲገደብ ከተደረገ ቀናት ያለፉ ሲሆን ጉዳዩን በተመለከተ ያብራራ/ያሳወቀ የለም።

የአገልግሎት ገደቡ በሁለቱም የቴሌኮም አገልግሎት አቅራቢዎች (ኢትዮ ቴሌኮም እና ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ) ተፈፃሚ እየሆነ ይገኛል።

የማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ከኢትዮጵያ ውጭ ባሉ ለአብነት በጎረቤት ሀገራት ያለ አንዳች ገደብ እየሰሩ ሲሆን በኢትዮጵያ አገልግሎት የመገደብ እርምጃ ከምን በመነሳት እንደተወሰደ እና እስከመቼ ድረስስ እንደሚቆይ ያብራራ አካል የለም።

ምንም እንኳን አገልግሎቶች ላይ ገደብ ቢደረግም የማህበራዊ መገናኛ ተጠቃሚዎች በ #VPN ገደቡን በማለፈ አገልግሎት እየተጠቀሙ ይገኘሉ።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Ethiopia ከጥቂት ቀናት በፊት አገልግሎታቸው እንዲገደብ የተደረጉት የማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ዛሬም አገልግሎታቸው ወደ ቦታው እንዳልተመለሰ ለመረዳት ታችሏል። #ቴሌግራም ጨምሮ ሌሎች የማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎች አገልግሎታቸው እንዲገደብ ከተደረገ ቀናት ያለፉ ሲሆን ጉዳዩን በተመለከተ ያብራራ/ያሳወቀ የለም። የአገልግሎት ገደቡ በሁለቱም የቴሌኮም አገልግሎት አቅራቢዎች (ኢትዮ ቴሌኮም እና ሳፋሪኮም…
#ETHIOPIA

በኢትዮጵያ የማህበራዊ መገናኛዎች ላይ ገደብ ከተገደረገባቸው ስድስተኛ ቀኑን ይዟል።

" #ቴሌግራም " ን ጨምሮ ሌሎች የማህበራዊ መገናኛዎች ምክንያቱ በግልፅ ወይም በይፋ ባልተነገረበት ሁኔታ ገደብ ከተደረገባቸው ስድስተኛ ቀን ሆኗል።

ይህ መልዕክት ተፅፎ እስከተላከበት ሰዓት ድረስ አገልግሎቶቹ ያልተመለሱ ሲሆን በኢትዮጵያ ውስጥ ባሉት ሁለቱም የቴሌኮም አገልግሎት አቅራቢዎች " ኢትዮ ቴሌኮም " እና " ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ " አማካኝነት አገልግሎት ማግኘት አልተቻለም።

የአገልግሎት ገደብን በተመለከተ " በዚህ ምክንያት ነው ፤ ለዚህን ያህል ጊዜም ይቆያል " ብሎ ያብራራ አካል እስካሁን ብቅ አላለም።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከተለያዩ ቤተሰቦቹ ለማጣራት ባደረገው ጥረት በሁለቱም የቴሌኮም አገልግሎት አቅራቢዎች " ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ እና ኢትዮ ቴሌኮም "  ቴሌግራም፣ ፌስቡክ፣ ቲክቶክ ፣ ዩትዩብ የመሳሰሉት የማህበራዊ መገናኛዎች አገልግሎት እየሰጡ የማይገኙ ሲሆን #ትዊተር፣  #ኢንስታግራም እና #ዋትስአፕ ገደብ ሳይደረግባቸው አገልግሎት እየሰጡ ነው።

ምንም እንኳን በተለያዩ የማህበራዊ መገናኛ አገልግሎቶች ላይ ገደብ ተጥሎ ቢገኝም በVPN አገልግሎቱን ማስቀጠል ይቻላል፤ ከዚህ ቀደም መሰል እርምጃዎች ከተወሰዱበት ጊዜ አንፃር ሲታይ በዚህኛው ከፍተኛ የሰው ቁጥር አገልግሎት ለማግኘት VPN የመጠቀም ሁኔታው መጨመሩን ከቲክቫህ ቤተሰብ አባላት ለመረዳት ችለናል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ETHIOPIA በኢትዮጵያ የማህበራዊ መገናኛዎች ላይ ገደብ ከተገደረገባቸው ስድስተኛ ቀኑን ይዟል። " #ቴሌግራም " ን ጨምሮ ሌሎች የማህበራዊ መገናኛዎች ምክንያቱ በግልፅ ወይም በይፋ ባልተነገረበት ሁኔታ ገደብ ከተደረገባቸው ስድስተኛ ቀን ሆኗል። ይህ መልዕክት ተፅፎ እስከተላከበት ሰዓት ድረስ አገልግሎቶቹ ያልተመለሱ ሲሆን በኢትዮጵያ ውስጥ ባሉት ሁለቱም የቴሌኮም አገልግሎት አቅራቢዎች " ኢትዮ ቴሌኮም…
#ETHIOPIA

በኢትዮጵያ ምክንያቱ ግልፅ ባልተደረገበት ሁኔታ የማህበራዊ ሚዲያዎች ገደብ ከተደረገባቸው ከአንድ ሳምንት በላይ ተቆጥሯል።

#ቴሌግራም እና ፌስቡክ መሰል የማህበራዊ መገናኛዎች ከተቋረጡ ዛሬ አስራ ሁለተኛ (12) ቀን ተቆጥሯል።

የማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ለምን ገደብ እንደተጣለ እንዲሁም ገደቡ መቼ እንደሚነሳ በየትኛውም አካል በኩል ለህዝብ ማብራሪያም ሆነ ገለፃ ያደረገ የለም።

ቴሌግራም ፣ ፌስቡክ እና ሌሎችም የማህበራዊ መገናኛዎች በሁለቱም የቴሌኮም አገልግሎት አቅራቢዎች በኩል ተገድበው የሚገኙ ሲሆን በርካቶች ገደቡን በVPN በማለፍ አገልግሎት እያገኙ ናቸው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ETHIOPIA ከትላንት ምሽት አንስቶ በኢትዮጵያ ቴሌግራም ፣ ፌስቡክ  እንዲሁም ሌሎች የማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎች እንዲገደቡ መደረጉ ታውቋል። አገልግሎቶቹ በሁለቱም የቴሌኮም አገልግሎት አቅራቢዎች ማለትም በኢትዮ ቴሌኮም እንዲሁም በሳፋሪኮም በኩል እየሰሩ እንዳልሆነ ለመረዳት ችለናል። ከማህበራዊ መገናኛዎቹ አገልግሎት መገደብ ጋር በተያያዘ በሌሎች ለአብነት በጎረቤት ሀገራት ውስጥ እስካሁን የታየ መቆራረጥ…
#ETHIOPIA

ማህበራዊ ሚዲያዎች ያለ VPN መስራት ጀመሩ።

ለወራት ያህል በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ተጥሎ የነበረው ገደብ መነሳቱን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከቤተሰቦቹ ለማረጋገጥ ችሏል።

#ቴሌግራም ፣ ዩትዩብ ፣ ፌስቡክ ፣ ቲክቶክ መሰል የማህበራዊ ሚዲያዎች ከወራት በፊት (የካቲት ወር 2015 ዓ/ም) በተጣለባቸው ገደብ ያለ VPN መስራት እንዳቆሙ ይታወቃል።

ዛሬ ሰኞ ከሰዓታት በፊት ግን እነዚህ የማህበራዊ ሚዲያዎች #ያለ_VPN_እየሰሩ እንደሚገኙ እና ገደቡም መነሳቱን #ማረጋገጥ ችለናል።

@tikvahethiopia
ዋትስ አፕ አዲሱን የቻናል ሥርዓቱን ጀመረ።

በ " ሜታ " ባለቤትነት ስር የሚገኘው ዋትስ አፕ የመልክእት መተግበርያ የቻናል ሥርዓትና ሌሎች አዳዲስ ማዘመኛዎችን ከ150 በላይ ሀገራት አስተዋውቋል።

ዋትስ አፕ ቻናል መመስረትና ማስተዳደር የሚያስችለውን አገልግሎት በሲንጋፖር እና ኮሎምቢያ ቢጀምርም ከዛሬ ሴፕቴምበር 19 ጀምሮ ስርጭቱን ወደቀሩት የዓለም ሀገራት አስፋፍቷል።

አዲስ ያስተዋወቀው ይህ ማዘመኛ ከ #ቴሌግራም ጋር ይበልጥ እንደሚያመሳስላቸው እየተነገረ ይገኛል።

በቀጣይም ዋትስ አፕ በሚደረጉለት አዳዲስ ማሻሻያዎች እንደ ተጠቃሚዎች የራሳቸውን ቻናሎች መመስረትና ማስተዳደር እንዲሁም መልእክቶችን ከቻናሎች ወደ ግላዊ ማህደራቸው ማውረድ የሚያስችላቸውን ባህሪያት አካትቶ ብቅ ብሏል።

Follow the TIKVAH-ETHIOPIA channel on WhatsApp: https://whatsapp.com/channel/0029Va9S9ChCXC3OmB1b7R2U

@tikvahethiopia