TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.3K photos
1.47K videos
209 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update ሱዳን ውስጥ የዳቦና የነዳጅ ዋጋ ንሮብናል ብለው #ተቃውሞ የወጡ ዜጎች ከፖሊስ ጋር ተጋጩ። ፖሊስ ሰልፈኞቹን ለመበተን አስለቃሽ ጭስ የተጠቀመ ሲሆን፤ መንግስት አፋጣኝ ምላሽ እንደሚሰጥ ይጠበቃል።

©BBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ማሻሻያ ማድረጉን ተከትሎ ተከራዮች የበተለያየ መንገድ #ተቃውሞ በማሰማት ላይ ይገኛሉ። መኢአድ የተባለው የፖለቲካ ፓርቲም ጭማሪውን በመቃወም መግለጫ አውጥቷል። የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ረሻድ ከማል ለበርካታ አመታት ከገቢያ ዋጋ በታች በመክፈል ተጠቃሚ ነበሩ በማለት የተከራዮችን ተቃውሞ እንደማይቀበሉት አስታውቀዋል። ፒያሳ ባቅላባ ቤት 6 ሺ ብር፤ ጆሊ ባር 5 ሺ ብር፤ ቱሪስት ሆቴል 13 ሺ ብር፤ ሮሚና ካፌ 3 ሺ ብር፡ ሎመባርዲያ 1777ሺ ብር፤ ሃራምቤ ሆቴል 35 ብር፤ ብቻ ሲከፍሉ ቆይተዋል በማለት ሀላፊው ምሳሌ ጠቅሰዋል።

Via~ELU
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Alert‼️

የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በግቢው የጥበቃና ደህንነት አሠራር ላይ ያላቸው ከፍተኛ #ተቃውሞ ከምሽቱ 4:30 አንስቶ በማሰማት ላይ ይገኛሉ።

በተለይም የተቋሙ ሴት ተማሪዎች፦ መብታቸው እንዲከበር፤ ደህንነታቸው እንዲጠበቅ፤ በግቢ ውስጥ የሚፈፀሙ ዝርፊያዎች በአስቸኳይ እንዲቆሙ ጠይቀዋል።

🔹በሌላ በኩል የተቋሙ ተማሪዎች በግቢ ውስጥ ከሚፈፀሙ ዝርፊያዎች በተጨማሪ በዩኒቨርሲቲው አካባቢ ያለው ዝርፊያ መንግስት በአስቸኳይ እንዲያስቆም እና ወንጀለኞችም ለፍርድ እንዲቀርቡ ጠይቀዋል።

▫️በአሁን ሰዓት #የሀገር_መከላከያ_ሰራዊት እና #ፌደራል_ፖሊስ ወደ ዩኒቨርሲቲው በመግባት ተማሪዎችን ለማረጋጋት እና ለማነጋገር እየጣሩ ይገኛሉ። ከተማሪዎች እንደሰማነውም በነገው ዕለት ተማሪው የሚካፈልበት ስብሰባ ተጠርቷል።

ምንጭ፦በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ የTIKVAH-ETHIOPIA ቤተሰብ አባላት
@tsegabwolde @tukvahethiopia
#update ከድሬዳዋ ደወሌ ጅቡቲ መንገድ በሱማሊ ክልል ሲቲ ዞን በተቀሰቀሰ #ተቃውሞ ዛሬ #ተዘግቶ ውሏል። ተቃውሞ የተቀሰቀሰው በአፋር ክልል በሚኖሩ የሱማሊ ዒሳ ጎሳ አባላት ላይ ጥቃት ደርሷል የሚል መረጃ መሰራጨቱን ተከትሎ ነው።

Via ELU
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሳይንት ወረዳ‼️

በአማራ ክልል በአምሀራ ሳይንት ወረዳ በአጅባር ከተማ በተቀሰቀሰ #ተቃውሞ የመንግስትም ሆነ የግል ተቋማት ከትላንት ከሰዓት ጀምሮ አገልግሎት መስጠት ማቋረጣቸውን ነዋሪዎች ገለጹ። ትላንት ለተቃውሞ የወጡ ነዋሪዎች ከተማይቱን ከደሴ ከተማ ጋር የሚያገናኛት መንገድን ዛሬም ዘግተው ውለዋል።

ከደሴ በስተምዕራብ 189 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው የአጅባር ከተማ በንግድ ስራ ላይ የተሰማሩ አንድ ነዋሪ ዛሬ ለጀርመን ድምፅ ራድዮ እንደገለጹት የትላንቱን ተቃውሞ ተከትሎ ከተማይቱ ዛሬ “ጸጥ ረጭ” ብላ ውላለች። “ሱቅም ዝግ ነው። መስሪያ ቤቶች ዝግ ናቸው። የትራንስፖርት እንቅስቃሴ የለም” ሲሉ በከተማይቱ ያለውን ሁኔታ የገለጹት ነዋሪው “መንገዶችም በድንጋይ እና በሌሎች ቁሳቁሶች ተዘግተዋል” ብለዋል።

በደቡብ ወሎ ዞን ስር የምትገኘው የአጅባር ከተማ ሰባት ሺህ ገደማ ነዋሪዎች አሏት። ነዋሪዎቿ “አካባቢያችን ከልማት ወደ ኋላ ቀርቷል፤ የክልል እና የዞን ባለስልጣናት ችግራችንን ሊመለከቱልን አልቻሉም” በሚል ትላንት እስከ እኩለ ቀን ድረስ የዘለቀ የአደባባይ ተቃውሞ አድርገው ነበር። ነዋሪዎቹ ጎማዎችን በማቃጠል መንገዶችን ዘግተዋል። በችግሩ ዙሪያ ለመወያየት ከደቡብ ወሎ ዞን የመጡ ባለስልጣናት ከመንገድ ተመልሰዋል መባሉ ነዋሪዎቹን ይበልጥ እንዳስቆጣቸው የዓይን እማኙ ተናግረዋል።

በትላንቱ ሰልፍ ላይ መሳተፋቸውን የሚናገሩት ነዋሪው በሰላማዊ ሰልፉ ወቅት በሰውም ሆነ በንብረት ላይ ጉዳት አለመድረሱን ይናገራሉ። ነዋሪዎችን አደባባይ ላስወጣቸው የመንገድ እና የሌሎችም የመሰረተ ልማት ችግሮች ከባለስልጣናት በኩል እስካሁን ምንም አይነት መፍትሄ አለመሰጡትንም አስረድተዋል።

የትላንትናው ተቃውሞው ሰላማዊ እንደነበር ለጀርመን ድምፅ ራድዮ ያረጋገጡት የአምሀራ ሳይንት ወረዳ የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አንዳርጌ እሸቴ እስካሁንም ድረስ ግን ከተማይቱን ከደሴ ጋር የሚያገናኘውመንገድ አልተከፈተም ብለዋል። ነዋሪዎች ላነሷቸው ጥያቄዎች መፍትሄ ለማበጀት በዛሬው ዕለት ከነዋሪው ጋር ለውይይት መቀመጣቸውን ገልጸዋል።

“አሁን በቀጣይ ሊሆን የሚችለው ከነጋዴው፣ ከአርሶ አደሩም፣ ከመንግስት ሰራተኛም፣ ከአመራርም ጭምር መርጠን የሚመለከታቸው አካላት ጋር ሄደን ምላሽ እናግኝ የሚል ነው” ብለዋል። በከተማይቱ ዘላቂ መፍትሄ እስኪገኝ ድረስ መንገዶቹ ተከፍተው አገልግሎታቸውን እንዲቀጥሉ ከነዋሪው ጋር ማምሻውን ስምምነት ላይ መድረሳቸውን አክለዋል። የተዘጉ መንገዶች ተከፍተው የመኪና እንቅስቃሴ መጀመሩንም የጠቆሙት ኃላፊው ከነገ ጀምሮ የመንግስት መስሪያ ቤቶችም ሆነ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ወደ መደበኛ ስራቸው እንደሚመለሱ ገልጸዋል።

ምንጭ፦ የጀርመን ድምፅ ራድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETH ማጠቃለያ🗞ጥር 22/2011 ዓ.ም.

በሶማሌ ክልል የቀድሞው ፕሬዚዳንት አቶ አብዲ #መሃመድ_ዑመርን ጨምሮ በ47 ግለሰቦች ላይ #ክስ ተመስርቷል።
.
.
ለከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች የትራንስፖርት አገልግሎት በመስጠት ላይ ያሉትን ‹‹ቪ8›› መኪኖች በሌሎች አዳዲስና ወጪ ቆጣቢ ተሽከርካሪዎች የመተካቱ ሂደት በመጠናቀቅ ላይ መሆኑ ተገልጿል።
.
.
በድሬዳዋ ከተማ ተፈጥሮ በነበረው #አለመረጋጋት እና የተቃውሞ ቀናት ጉዳት ሳይደርስበት በሀሰት ጉዳት የደረሰበት በማስመሰልና ይህንን የሃሰት ፎቶ በማህበራዊ ድረ ገፅ በመልቀቅ ግጭቶች እንዲፈጠሩ ለማድረግ የሞከረው ግለሰብ በቁጥጥር ስር ውሏል፡፡
.
.
በቅርቡ የፀደቀውን የስደተኞች አዋጅ በመቃወም በአዲስ አበባና በጋምቤላ #የተቃውሞ_ሠልፍ ሊደረግ እንደሆነ ተሰምቷል።
.
.
በሶማሌ ክልል ግጭት፣ ግድያና ቃጠሎ ጋር በተያያዘ ከአራት ወራት በላይ በእስር ላይ የነበረው #ቴዎድሮስ_አዲሱ (ቴዲ ማንጁስ) በ80,000 ብር ዋስ ከእስር እንዲፈታ ፍርድ ቤት ትእዛዝ ሰጥቷል።
.
.
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ባለስልጣን "ግዴታዬን እወጣለሁ ፣ መብቴንም እጠይቃለሁ!" በሚል መርህ ቃል የከተማ አቀፍ የታክስ ንቃናቄ መድረክ ተካሂዷል።
.
.
ከኮንሶ ዞን ወደ ሶያማ ቡርጂ ወረዳ ሲጓዝ በነበረ የጭነት መኪና ላይ ባልታወቁ #ታጣቂዎች በተከፈተ ተኩስ በትላንትናው ዕለት የአራት ሰዎች ህይወት አልፏል።
.
.
#በምሥራቅ_ወለጋ_ዞን በተለያዩ ወረዳዎች የሚገኙ በጎ ፈቃደኛ ተማሪዎች 2ሺህ 380 ዩኒት ደም መለገሳቸውን የነቀምቴ ደም ባንክ አገልግሎት አስታውቋል።
.
.
የመልካም አስተዳደርና የሥራ  አጥነት መሠረታዊ ጥያቄዎች በፍጥነት ለመመለስ የሚያግዝ የ60 ቀናት ዕቅድ ተዘጋጅቶ እንቅስቃሴ መጀመሩን የድሬደዋ አስተዳደር ከንቲባ ተናግረዋል።
.
.
ሰሞኑን በድሬዳዋ በተፈጠረው ሁከትና ነውጥ #በማራገብ ሂደት #ፖሊስ እና #አድማ_በታኝ አሉበት፤ ይህም በፖሊስ ውስጥ መሠረታዊ ሪፎርም እንደሚያስፈልግ ያመለክታል ተብሏል።
.
.
15ኛው የኢትዮ-ጅቡቲ የጋራ ኮሚሽን ስብሰባ በዛሬው ዕለት በጂቡቲ ተጀምሯል፡፡
.
.
ትናንት በሶማሌ ክልል መዲና- ጅግጅጋ የሃይማኖት ክብረ በዓልን ተከትሎ በተፈጠረ ግጭት ሁለት ሰዎች መገደላቸው ተነግሯል።
.
.
የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ለማ መገርሳ እና የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው #በኔዘርላንድ የሚገኙ ኩባንያዎችን ጎብኝተዋል።
.
.
የኢትዮጵያ #ጉብኝታቸዉን አጠናቀዉ ወደ ሀገራቸው ለመመለስ በዝግጅት ላይ ያሉት የጀርመኑ ፕሬዝዳንት ፍራንክ ቫልተር ሽታይንማየር የሚበሩበት አዉሮፕላን የቴክኒክ #እክል ገጥሞት መዘግየቱ ተሰምቷል።
.
.
ከአዲስ አበባ ወደ ነቀምት በህገ-ወጥ መንገድ ሲጓጓዝ የነበረ 11 ሺህ ሊትር ነዳጅ መያዙን የኢሉገላን ወረዳ ፖሊስ አስታውቋል።
.
.
በአማራ ክልል በአምሀራ ሳይንት ወረዳ በአጅባር ከተማ በተቀሰቀሰ #ተቃውሞ የመንግስትም ሆነ የግል ተቋማት ከትላንት ከሰዓት ጀምሮ አገልግሎት መስጠት ማቋረጣቸውን ነዋሪዎች ገልፀዋል።
.
.
ከጥረት ኮርፖሬት የሃብት ምዝበራ ጋር በተያያዘ የአምባሰል ንግድ ስራዎች ስራ አስኪያጅ የነበሩትን አቶ #ምትኩ_በየነን ጨምሮ አምስት ሰዎች ዛሬ በአዲስ አበባ ከተማ በህግ ቁጥጥር ስር ውለዋል።
.
.
የኢትዮጵያ፣ ኤርትራ፣ ኬንያ፣ ሶማሊያና ዩጋንዳ የፖሊስ አመራሮችና አቃቤ ሕጎች የሶስት ቀናት አውደጥናትን ዛሬ #በኤርትራ_አስመራ ተጀምሯል፡፡
.
.
በአለም ላይ ያለውን የነዳጅ ምርቶች ዋጋ ጭማሪን ግምት ውስጥ በማስገባት እና በህዳር ወር ተደረገው ዋጋ #ማስተካከያ ዝቅተኛ በመሆኑ፥ በነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ #መጠነኛ_ጭማሪ ማድረጉን የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታውቋል።

ምንጭ፦ etv፣ fbc፣ የጀርመን ራድዮ፣ ኢ.ፕ.ድ፣ ኢዜአ፣ የንግድ እና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር፣ የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት

ሰላም እደሩ!!
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሀዋሳ

በሀዋሳ ከተማ በመካሄድ ላይ የሚገኘው የደኢህዴን አመራሮች ክልል አቀፍ ጉባኤ ዛሬ እንዲቀጥል ሙከራ የተደረገ ቢሆንም፣ ከመሰብሰቢያ አዳራሹ ፊት ለፊት በተነሳ #ተቃውሞ ጉባኤው ሳይደረግ ቀርቷል።

በከተማው ውስጥ ወጣቶች ተደራጅተው የተሰቀሉ የደቡብ ክልል #ባንዲራዎችን ሲያወርዱ እንደተመለከቱ የአይን እማኞች ነገርውናል። (ከሀዋሳ በተጨማሪ በአንዳንድ የሲዳማ ዞን ከተሞች በተመሳሳይ የደቡብ ክልልን ባንዲራ የማውረድ እንቅስቃሴ ታይቷል)

በትላንትናው ዕለት የሲዳማ ብሔር ተወላጅ የደኢህዴን አመራሮች ለመወያያ ቀርቧል በተባለ ሰነድ ሳቢያ ስብሰባውን ረግጠው እንደወጡ ይታወቃል።

ከተማውን ተዘዋውሮ የተመለከተው የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባል (W) በአሁን ሰዓት ምንም የፀጥታ መደፍረስ እንደማይስተዋል ገልፆል።

@tsegabwolde @tikvahethiopua
ደብረብርሃን🔝

በደብረ ብርሃን ከተማ ትላንት የጀመረ #ተቃውሞ ዛሬም የቀጠለ ሲሆን፣ ትራንስፖት ተቋርጧል የአገልግሎት መስጫ ተቋማት #ተዘግተዋል

#ELU
የጥናት ሪፖርቱ ይፋ ሊደረግ ነው...

ከአካባቢ ብክለት ጋር በተያያዘ ከፍተኛ #ተቃውሞ የቀረበበት ንብረትነቱ የሚድሮክ ጎልድ የሆነው #የለገደምቢ ወርቅ ማውጫ ላይ ሲያካሂድ የነበረውን ጥናት ሪፖርት በመጪው ሳምንት ይፋ እንደሚያደርግ፣ የማዕድንና ነዳጅ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

የሚድሮክ ጎልድ ኩባንያ በለገደምቢ ወርቅ ለማምረት የሚጠቀምበት ኬሚካል በአካባቢውና በማኅበረሰቡ ጤና ላይ ቀውስ እንደፈጠረ በመግለጽ፣ የሻኪሶ ከተማና የአካባቢው ነዋሪዎች ከፍተኛ ተቃውሞ በማሰማታቸው የማዕድን ሚኒስቴር ጉዳዩ በገለልተኛ ወገን እስኪጣራ የኩባንያው የማዕድን ምርት ፈቃድ ከአንድ ዓመት በፊት ማገዱ ይታወሳል፡፡

ሚያዝያ 16 ቀን 2011 ዓ.ም. ጋዜጣዊ መግለጫ የሰጡት የማዕድንና ነዳጅ ሚኒስትር አቶ #ሳሙኤል_ሁርቃቶ፣ በገለልተኛ ባለሙያዎች በሚድሮክ ጎልድ ኩባንያ አሠራር ላይ ሲካሄድ የነበረው ጥናት ሪፖርት #በመጪው ሳምንት ይፋ እንደሚደረግ አስታውቀዋል፡፡

የማዕድንና ነዳጅ ሚኒስቴር የአካባቢ ተፅዕኖ ጥናት ቀደም ሲል በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አስጠንቶ የነበረ ቢሆንም፣ ውጤቱ ለሕዝብ ይፋ ሳይደረግ ቆይቷል፡፡ ሚኒስቴሩ የሚድሮክ ጎልድን ፈቃድ #ካገደ በኋላ ከኩባንያው ኃላፊዎች፣ ከአካባቢው ኅብረተሰብ ተወካዮችና ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር ባዘጋጀው የምክክር መድረክ ተጨማሪ ጥናት በገለልተኛ ወገን እንዲከናወን ከስምምነት ላይ መድረሱ ይታወሳል፡፡

የካናዳ መንግሥት ለማዕድን ሚኒስቴር በሚሰጠው የድጋፍ ፕሮግራም፣ በለገደምቢ ወርቅ ማውጫ ላይ ለሚካሄደው ጥናት የገንዘብ ድጋፍ አድርጓል፡፡ ጥናቱ በካናዳ ከፍተኛ ባለሙያዎች እንደተካሄደ ታውቋል፡፡ በጥናቱ ግኝት ላይ ተመርኩዞ ሚኒስቴሩ የውሳኔ ሐሳብ እንደሚያሳልፍ ይጠበቃል፡፡ ሚድሮክ ጎልድ ሥራው በመቋረጡ ለከፍተኛ ኪሳራ እንደተዳረገ በመግለጽ፣ ጥናቱ በአፋጣኝ እንዲሠራ ሲወተውት መቆየቱ ይታወሳል፡፡

በማዕድን ኩባንያዎችና በአካባቢ ማኅበረሰቦች ስለሚፈጠሩ ግጭቶች የተናገሩት አቶ ሳሙኤል፣ አንዳንድ ኩባንያዎች የማኅበረሰብ አቀፍ ሥራ እንደማያከናውኑ ከክልል መንግሥታት ጋርም ግንኙነት እንደሌላቸው ገልጸዋል፡፡ ‹‹ከፌዴራል መንግሥት የማዕድን ሥራ ፈቃድ የተሰጣቸው ኩባንያዎች በክልል ውስጥ ደሴት ሆነው የሚሠሩ ነበሩ፡፡ ከክልል መንግሥት ጋር ምንም ዓይነት ግንኙነት አያደርጉም፡፡ ክልሉም ምን እንደሚሠሩ አያውቅም፡፡ ልክ ችግር ሲፈጠር ኩባንያዎቹ የክልሉን መንግሥት ያናግራሉ፤›› ያሉት አቶ ሳሙኤል፣ ይህን አሠራር ለመለወጥ ሚኒስቴሩ በማዕድን ኩባንያዎችና በክልል መንግሥታት መካከል መልካም የሥራ ግንኙነት ለመፍጠር እየሠራ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

ክልሎች የማዕድን ኩባንያዎች የሚያከናውኗቸውን ሥራዎች አውቀው አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲያደርጉላቸው እየተሠራ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ በማኅበረሰብ ልማት ፕሮጀክቶች ላይ ሊነገሩ የሚገቡ መልካም ሥራዎች የሠሩ ኩባንያዎች እንዳሉም ጠቁመዋል፡፡

ሚድሮክ ጎልድ የለገደምቢ የወርቅ ማውጫን በ1989 ዓ.ም. ከፕራይቬታይዜሽን ኤጀንሲ በጨረታ በ172 ሚሊዮን ዶላር መግዛቱ ይታወሳል፡፡ የወርቅ ማውጫው በዓመት አራት ቶን ወርቅ የማምረት አቅም አለው፡፡

ምንጭ፦ ሪፖርተር
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ #ተቃውሞ ገጠመው!

ዛሬ በእስክንድር ነጋ የሚመራው የአ/አ ባላደራ ምክርቤት መግለጫ ተቃውሞ ማስተናገዱ ተሰምቷል። መግለጫውን ሲቃወሙ የነበሩት ወጣቶች ይህን ሲሉም ተደምጧል፦

"ኢትዮጵያን በደማችን ነው ያቆምናት!!"

"ይሄው🇪🇹ባንዲራችን!"

"ጥያቄ አለን! እንጮሃለን~እኛ የሚያስፈልገን ሃገር መገንባት ነው እንጂ ሀገር ማፍረስ አይደለም!!"

"በደም የተገነባች ሀገር ናት"

"የሚያፈርሰንን አንፈልግም፤ በብሄር መከፋፈል አንፈልግም!"

"አትከፋፍላትም፤ አይሳካልህም፤አይሳካላችሁም"

"ዛሬም ነገም ኢትዮጵያ ትኖራለች!"

"ኢትዮጵያ አትፈርስም!"

"የራስን ቤት ማፍረስ አይቻልም!"

#TIKVAH_ETH
ቪድዮ: ኢትዮ ታይምስ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በግብፅ ከተቀሰቀሰው #ተቃውሞ ጋር በተያያዘ የBBC ዌብሳይት፣ ፌስቡክ ሜሴንጀር፣ የማህበራዊ ሚዲያ CDN ሰርቨሮች መዘጋታቸውን እና አገልግሎት እንዳይሰጡ መደረጋቸውን ኔት ብሎክስ አስታውቋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia