TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.9K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
" ኢትዮጵያ የአረብ ሊግ መግለጫን አጥብቃ ትቃወማለች " - አምባሳደር ምስጋኑ አረጋ የኢፌዴሪ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ፤ ኢትዮጵያ የአረብ ሊግ መግለጫን አጥብቃ ትቃወማለች ብለዋል። የአረብ ሊግ መግለጫ በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ እና ሉዓላዊነት ላይ ጣልቃ የመግባት ሙከራ ነው ብለዋል። " ኢትዮጵያ ከብዙ የአረብ ሀገራት ጋር ጥሩ የሁለትዮሽ ግንኙነት አላት። " ያሉት ሚኒስትር…
" ግብፅ እና አረብ ሊግ የአንድ ሳንቲም ሁለት ገፅታ ናቸው "

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር መለስ አለም ስለ ግብፅ እና አረብ ሊግ ምን አሉ ?

" ከአረብ ሊግ የተሰጠው መግለጫ ተቀባይነት የለውም።

ይህ ድርጅት በማን እንደሚዘወር ይታወቃል። የወጣው መግለጫ ተቋሙንም አባል ሀገራቱንም የሚመጥን አይደለም። የማን ድርጅት እንደሆነም ይታወቃል።

ከምንም በላይ ለአፍሪካውያን ንቀት ነው። አፍሪካውያን የራሳቸውን ችግር የመፍታት ብቃቱ አላቸው፤ በተግባርም አሳይተዋል።

ለአፍሪካዊ ችግር አፍሪካዊ መፍትሄ የሚለውን እሳቤ የሚያጣጥል ነው ተቀባይነት የለውም።

... በግብፅ እና አረብ ሊግ መካከል ያለው ግንኙነት የአንድ ሳንቲም ሁለት ገፅታ ተደርጎ ነው መወሰድ ያለበት፤ ምንም ልዩነት የለውም በግልፅ መናገር ያስፈልጋል ይሄ ወጣቱ ትውልድም እንዲያውቀው መደረግ አለበት።

የግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የሰጡት መግለጫ ጠቃሚ አይደለም። ሁለቱ ሀገሮች ካላቸው ግንኙነት አንፃር የሚመጥን አይደለም። ግብፅ እና ኢትዮጵያ የአባይ ልጆች ናቸው፤ ከአንድ ውሃ ነው የሚጠጡት ከአንድ ውሃ ነው የሚጠቀሙት።

በኢትዮጵያ በኩል ነገሮችን ማጋጋም ፣ ከልካቸው በላይ መስቀል ፣ማጋነን ጠቃሚ ነው ብላ አታምንም። ከምንም በላይ የአፍሪካ ህብረት እንደገለፀው የውጭ ጣልቃ ገብነት የሚደገፍ አይደለም።

ይህ የመጀመሪያ ጊዜ አይደለም። ከህዳሴ ግድብ ጋር በተያያዘ በርካታ መግለጫዎች ሰጥተዋል። በእኛ በኩል ድርድሩም የሁለትዮሽ ውይይቱንም በሚዲያ ማድረግ አንፈልግም።

የአረብ ሊግ ከህዳሴ ግድብ ጋር በተያያዘ ስንት መግለጫው አውጥቷል ? የኢትዮጵያ ጥያቄ ውሃ የማግኘት ሳይሆን ብርሃን የማግኘት ጉዳይ ነው። ተማሪዎች ብርሃን ያስፋጋቸዋል፤ እህቶቻችን በወሊድ መሞት የለባቸውም ሀኪም ቤት መሄድ አለባቸው ሀኪም ቤቶች ብርሃን ያስፈልጋቸዋል።

ስለዚህ ' ምንም በማያቁበት ሀገር ሄዶ ቁርበት አንጥፉልኝ ይላል ' ኢትዮጵያ ያለመረጋጋት ሳይሆን የመረጋጋት መንስኤ ናት ለዚህ አካባቢ ፤ ኢትዮጵያን በአለመረጋጋት መንስኤነት መክሰስ በአንድ ቃል ለመግለፅ #ቧልት ነው፤ የዘመኑ ቀልድ ተብሎ ሊቀመጥ ይችላል። "

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ግብፅ #ሱማሊያ

በግብፁ ፕሬዜዳንት አብዱል ፈታህ አልሲሲ ግብዣ የተደረገላቸው የሶማሊያው ፕሬዜዳንት ሀሰን ሼክ ሞሀሙድ ግብፅ ካይሮ ገብተዋል።

ሁለቱ ፕሬዜዳንቶች በሁለትዮሽ እና ቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ ይመክራሉ ተብሏል።

የኢትዮጵያ እና ሶማሌላንድ የመግባቢያ ስምምነት በተፈረመ ማግሥት " ከሶማሊያ ጎን እቆማለሁ " ብላ በስምምነቱ ላይ ተቃውሞ ያሰማቸው ግብፅ ነበረች።

ከዚህም ባለፈ የሶማሊያ ፕሬዜዳንት በስምምነቱ ተቃውሞ ዙሪያ ቀደመው ስልክ ከደወሉላቸው መሪዎች አንደኛው ፕሬዜዳንት አልሲሲ እንደነበሩ አይዘነጋም።

ፕሬዜዳንት አልሲሲም ከቀናት በኃላ ፕሬዜዳንቱ ወደ ኤርትራ ባቀኑበት ወቅት ግብፅን እንዲጎበኙ ጥሪ አድርገውላቸው የነበረ ሲሆን በዚሁ ጥሪ መሰረት ለሁለት ቀን ጉብኝት ትላንት ምሽት ካይሮ ገብተዋል።

ግብፅ ፤ #ኢትዮጵያ 🇪🇹 የባህር በር እንዲኖራት እድልን ይሰጣል ከተባለውና ከሶማሌላንድ ጋር ከተደረገው የመግባቢያ ስምምነት ወዲህ ኢትዮጵያን የሚወነጅሉ አስተያየቶችን ስትሰጥ የነበረ ሲሆን ከሰሞኑን " ኢትዮጵያን በአካባቢው የአለመረጋጋት ምንጭ እየሆነች ነው " የሚል ንግግር በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ በኩል ተናግራለች።

ኢትዮጵያም ግብፅ በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ በኩል ለተናገረችው ንግግር በአምባሳደር መለስ አለም በኩል ፤ " ኢትዮጵያን በአለመረጋጋት መንስኤነት መክሰስ በአንድ ቃል ለመግለፅ #ቧልት ነው፤ የዘመኑ ቀልድ ተብሎ ሊቀመጥ ይችላል። " በሚል የመልስ ምት ሰጥታታለች።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ግብፅ #ሱማሊያ በግብፁ ፕሬዜዳንት አብዱል ፈታህ አልሲሲ ግብዣ የተደረገላቸው የሶማሊያው ፕሬዜዳንት ሀሰን ሼክ ሞሀሙድ ግብፅ ካይሮ ገብተዋል። ሁለቱ ፕሬዜዳንቶች በሁለትዮሽ እና ቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ ይመክራሉ ተብሏል። የኢትዮጵያ እና ሶማሌላንድ የመግባቢያ ስምምነት በተፈረመ ማግሥት " ከሶማሊያ ጎን እቆማለሁ " ብላ በስምምነቱ ላይ ተቃውሞ ያሰማቸው ግብፅ ነበረች። ከዚህም ባለፈ የሶማሊያ ፕሬዜዳንት…
የግብፁ መሪ ምን አሉ ?

የግብፁ ፕሬዜዳንት አብዱል ፈታህ አልሲሲ ከሶማሊያው ፕሬዝዳንት ጋር የሁለቶሽ ምክክር ካደረጉ በኃላ በጋራ ሆነው መግለጫ ሰጥተው ነበር።

በዚህም ወቅት የግብፁ መሪ ፤ " የአረብ ሊግ ቻርተር በሉዓላዊነታቸው እና በግዛታቸው ላይ ጥቃት የሚደርስባቸውን የአረብ ሀገራት እንድንከላከል ያስገድደናል " ሲሉ ተደምጠዋል።

" ግብፅ በሶማሊያ ደህንነት ላይ ምንም አይነት ስጋት እንዲፈጠር አትፈቅድም " ሲሉ የተናገሩት አልሲሲ ፤ " የግብፅ ሃያልነት ወንድማማች የሆነ ሀገሮች ላይ ስጋት በመፍጠር መሞከር የለበትም ፤ አትፈታተኑን " ብለዋል።

" ግብፅን አትሞክሩ ፤ የግብፅ ወንድሞች የሆኑ ሀገራት ላይም ስጋት ለመሆን አትሞክሩ " ሲሉ የተደመጡ ሲሆን ጥያቄ ከቀረበልን ጣልቃ እንገባለን ሲሉ ተናግረዋል።

የግብፁ ፕሬዜዳንት ፤ " በተለይ ወንድማማች ሀገሮች ከጎናቸው እንድንቆም በሚጠይቁን ጊዜ ለመቆም ዝግጁ ነን " ያሉ ሲሆን " ግብፅ በአንዱ አረብ አገር ላይ ጥቃት ቢሰነዘርበት ለመደገፍ ዝግጁ ነች " ሲሉ ተደምጠዋል።

ፕሬዝዳንት በንግግራቸው #የኢትዮጵያንም 🇪🇹 ስምን አንስተው ሲናገሩ ነበር።

አልሲሲ ፤ " ለኢትዮጵያ ያለኝ መልዕክት የሶማሊያን አንድን መሬት ለመቆጣጠር የሚደረግ ጥረት አይሳካም በዚህ የሚስማማም የለም " ብለዋል።

የሶማሊላንድ እና ኢትዮጵያ የመግባቢያ ስምምነት በግብፅም በሶማሊያም ዘንድ ተቀባይነት የለውም ፤ ጣልቃ እንድንገባ ከተጠየቅን ደግሞ በሶማሊያ ላይ የሚፈጸም የሉዓላዊነት እና ግዛት አንድነት ጥቃትን ለመመከት ድጋፍ እናደርጋለን ሲሉ ተናግረዋል።

ግብፅ ፤ ኢትዮጵያ የባህር በር እንድታገኝ እድል ይፈጥራል የተባለውን የመግባቢያ ስምምነት ከሶማሌላንድ ጋር በፈረመች በማግስቱ ነው ከሶማሊያ ጎን እቆማለሁ በማለት ተቃውሞ ማሰማት የጀመረችው።

                          _________

" ግብፅ እና አረብ ሊግ የአንድ ሳንቲም ሁለት ገፅታ ናቸው "

ኢትዮጵያ ከሰሞኑን አረብ ሊግ ባወጣው መግለጫ ዙሪያ ምላሽ በሰጠችበት ወቅት ፤ " ግብፅ እና አረብ ሊግ የአንድ ሳንቲም ሁለት ገፅታዎች ናቸው " ስትል ነው የገለፀችው።

" ይህ ድርጅት በማን እንደሚዘወር ይታወቃል " ያለችው ኢትዮጵያ የወጣው መግለጫ ተቋሙንም አባል ሀገራቱንም የሚመጥን እንዳልሆነና የማን ድርጅት እንደሆነም እንደሚታወቅ ገልጻለች።

በግብፅ እና አረብ ሊግ መካከል ያለው ግንኙነት የአንድ ሳንቲም ሁለት ገፅታ ተደርጎ እንደሚወሰድና ምንም ልዩነት እንደሌለው በግልፅ መናገር እንደሚያስፈልግ ይሄን ደግሞ ወጣቱ ትውልድም እንዲያውቀው መደረግ እንዳለበት አስገንዝባለች።

ከሰሞኑን የግብፅ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር " ኢትዮጵያ ለቀጠናው ያለመረጋጋት ምንጭ እየሆነች ነው " ብለው ለተናገሩት ንግግር በኢፌዴሪ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በተሰጠ ምላሽ ፤ ኢትዮጵያ ለአካባቢው የመረጋጋት መንስኤ እንደሆነችና ኢትዮጵያን በአለመረጋጋት መንስኤነት መክሰስ #ቧልት / የዘመኑ ቀልድ ተብሎ ሊቀመጥ እንደሚችል መገለፁ ይታወሳል።

@tikvahethiopia