TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.3K photos
1.47K videos
209 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
አንፃራዊ ሰላም ሰፍኗል‼️

መንግስት የጦር መሳሪያ ሊያስፈታ ነው የሚለው ቅስቀሳ ከእውነት የራቀ መሆኑን የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ። በምዕራብ እና በማዕከላዊ ጎንደር ዞኖች አንፃራ ሰላም መስፈኑንም ኮሚሽኑ አስታውቋል፡፡

ኮሚሽኑ ዛሬ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ነው በሁለቱ ዞኖች አንፃራዊ ሰላም መታየቱን ያስታወቀው፡፡ በአካባቢው የነበረውን #አለመረጋጋት ወደ #ሰላማዊ እንቅስቃሴ ለመመለስ የጦር መሳሪያ ይዞ መንቀሳቀስ ክልከላ እና ሌሎች እገዳዎች ከተላለፉበት ቀን ጀምሮ በሰውም ይሁን በንብረት ላይ ይደርስ የነበረው ጉዳት መቀነሱን ገልፃል፡፡

የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ዘላለም ልጃለም እንደጠቆሙት የፌደራል እና የክልል የፀጥታ ሀይሎች ከህብረተሰቡ ጋር እየሰሩት ባለው ተግባር በቡድን ሲፈፀሙ የነበሩ የግድያ እና የንብረት ማጥፋት ወንጀሎች ቀንሰዋል፡፡

ከእገዳው በኋላ በጥምረት በተሰራው ስራም 11 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውንም ተናግረዋል። አሁንም አልፎ አልፎ በግለሰብ ደረጃ የሚፈፀሙ ወንጀሎች መኖራቸውንም ጠቁመዋል።
ከአሁን ቀደም ታግተው የነበሩ ግለሰቦችም ሙሉ በሙሉ መለቀቃቻን ኮሚሽነሩ አረጋግጠዋል፡፡

ከጎንደር መተማም ይሁን ከጎንደር ሁመራ የተሽከርካሪ መጓጓዣ አገልግሎት እየተሰጠ መሆኑንም አስታውቀዋል፡፡ በጎንደር ከተማ ከአሁን ቀደም የጥይት ተኩስ ይሰማ ነበር ያሉት ኮሚሽነር ዘላለም እገዳው ከተደረገ ወዲህ መቀነሱን አመላክተዋል፡፡

ይህ ደግሞ የፀጥታ ሀይሉ ከማህበረሰቡ ጋር በጋራ ሆኖ በመስራቱ የመጣ ነው፤ የጎንደር ከተማ ወጣቶች ለሰላም እያሳዩ ያሉት ትብብርም የሚደነቅ ነው ብለዋል፡፡

ወንድማማች ህዝቦቹ ካለፈው ጥፋት ተምረው በጋራ ችግሮቻቸውን ለመቅረፍ እየተወያዩ መሆናቸውም ታውቋል።

እገዳ በተደረገባቸው አካባቢዎች የጦር መሳሪያ ይዞ መንቀሳቀስ መከልከሉን ምክንያት አድርገው መንግስት የጦር መሳርያ #ሊያስፈታ ነው እያሉ ቅስቀሳ የሚያደርጉ አካላት አሉ፡፡ "ቅስቀሳው ከእውነት የራቀ ነው፤ #ብጥብጥ በመፍጠር ክልሉን ለማዳከም የታለመ ሀሳብ በመሆኑ ማህበረሰቡ በአሉባልታዎች እንዳይታለል" ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

ምንጭ፦ አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia