TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.7K photos
1.44K videos
207 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
" ... ህወሓቶች የሀገሪቱን ሕገ መንግስት እንዲያከብሩ ፤ እና እንደ ኢትዮጵያ አንድ #ክልል እንዲንቀሳቀሱ ለማሳመን እየሞከርን ነው " - ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ

የሰሜን ኢትዮጵያውን ጦርነት ሰላማዊ በሆነ መንገድ ለመፍታት በሚካሄደው ሂደት ከባድ የውጭ ጣልቃ ገብነት እንዳለ ጠቅላይ ሚኒስተር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ተናግረዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህን የተናገሩት ከCGTN  ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ነው።

ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ ሰላምን ለማምጣት ባለው ሂደት " የውጪ ጣልቃ ገብነት " ቢኖርም የሰላም ስምምነት እንደሚደረስ ተስፋ እንዳላቸው ገልጸዋል።

" በእርግጥ ከግራም ሆነ ከቀኝም በርካታ ጣልቃ ገብነቶች የሚኖሩ ከሆነ በጣም አስቸጋሪ ይሆናል " ያሉት ዶ/ር ዐቢይ ፤ " ኢትዮጵያውያን መረዳት ያለባቸው የራሳችንን ጉዳይ በራሳችን መፍታት አንደምንችል " ነው ሲሉ አክለዋል።

" ህወሓት የሀገሪቱን #ህገመንግስት እንዲያከብር ፤ ኢትዮጵያ ውስጥ እንደ አንድ ክልል  እንዲንቀሳቀስ ለማሳመን ጥረት እያደረገን ነው " ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፤ " ፍላጎታችንን መገንዘብ የሚችሉ ከሆነ እና የራሱን ህገመንግስት የሚያክብር እና በህጉ መሰረት የሚንቀሳቀስ ከሆነ ሰላም ይሰፍናል ብየ አስባሁ " ብለዋል።

(ሙሉ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ንግግር ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia