TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.44K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ትንሳኤ70እንደርታ

" የመቐለ ከተማ አስተዳደር የፈቀድልን ህዝባዊ ስብሰባ ተከለከልን " ሲል ትንሳኤ 70 እንደርታ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ቅሬታውን አሰማ።

የፓርቲው ሊቀመንበር ከበደ አሰፋ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ በሰጡት ቃል ፥ _ እሁድ ጳጉሜን 3/2016 ዓ.ም በመቐለ ከተማ አስተዳደር ግቢ በሚገኘው አግኣዚ የስብሰባ አዳራሽ ህዝባዊ ስብሰባ ለማካሄድ ተፈቕዶልን አባልና ደጋፊዎቻችን ጠርተን ስናበቃ አዳራሽ እንዳንገባ በታጣቂዎች ተከልክለናል " ብለዋል።

" በህጋዊ መንገድ የተፈቀደ ህዝባዊ ውይይት መከልከልና ታዳሚዎች ማንገላታት ኢ-ዴሞክራሲያዊ ነው " ያሉት የፓርቲው ሊቀመንበር በተግባሩ ማዘናቸው በመግለፅ ከሚመለከተው አካል ግልፅ ማብራርያ እንዲሰጣቸው መጠየቃቸው ተናግረዋል።

" የመቐለ ከተማ ፀጥታ ፅ/ቤት በፃፈልን ደብዳቤ መሰረት ስብሰባውን የፀጥታ ጥበቃ ለማድረግ ፓሊስ መድቦ በቦታው የተገኙ ሲሆን ማንነታቸውና ተጠሪነታቸው የማይታወቁ ሌሎች ሃይሎች ተሳብሳቢው ወደ ግቢ እንዳናሰግባ የአዳራሹ ሰራተኞች ሳይቀር እንዳይገቡ በር ላይ ለነበሩ የጥበቃ ሰራተኞች ትእዛዝ በመሰጠቱ ምክንያት ስብሰባው ሳይደረግ ቀርተዋል " ሲሉ አስረድተዋል።

" እንደምክንያት ያቀረቡትም የከንቲባ ፅ/ቤት ሃላፊ ወ/ሮ ለጋስ ማርያም ' እኔ ካልደወልኩኝ እንዳይገቡ ብለዋል ' የሚል ሲሆን ግለሰብዋ በደብዳቤ የፈቀዱትን ስብሰባ በዚህ መንገድ የከለከሉበት ምክንያት ለመጠየቅ ስልካቸው ላይ በተደጋጋሚ ብንደውልም ስላካቸውን በመዝጋታቸው ምክንያት ልናገኛቸው አልቻልንም " በማለት ገልጸዋል።

የመቐለ ከተማ ፀጥታ ዘርፍና ፓሊስ መንግስታዊ ሃላፊነቱን በአግባቡ ለመወጣት መሞከሩን አመልክተው " ምስጋና ይገባዋል " ብለዋል።

የመቐለ ከተማ አስተዳደርና ፓሊስ እስከ አሁን ሰዓት ስለ ክልከላው የሰጠው ይፋዊ ማብራርያም ሆነ መግለጫ የለም። 

ትንሳኤ 70 እንደርታ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ ከአንድ ዓመት በፊት ሰላማዊ ፓለቲካዊ ትግል ለማካሄድ ከኢትዮጵያ ብሄራዊ የምርጫ ቦርድ እውቅና አግኝቶ መመስረቱ ይታወቃል።

#TikvahEthiopiaMekelle

@tikvahethiopia