TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.7K photos
1.44K videos
207 files
3.98K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ጥንቃቄ

ከኢትዮጵያ ብሄራዊ ሚትዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት በተገኘ መረጀ በሐምሌ የመጀመርያዎቹ ሳምንታት ከፍተኛ የሆነ ነጎድጓዳማና በረዶ የቀላቀለ ዝናብ ይኖራል።

በተከታታይ ቀናት የሚኖረው የዝናብ መጠን ጎርፍና የመሬት መንሸራተት ሊፈጥር ስለሚችል አስፈላጊው ጥንቃቄ ሊደረግ ይገባል፡፡

በአርብቶ አደር አካባቢዎች የሚገኘውን ውኃ በጥንቃቄ መያዝም እንደሚገባ ተገልጿል።

የሚፈጠረው ዝናብ ከመጠን በላይ ማሣ ላይ ውኃ እንዲተኛ ስለሚያደርግ በእርሻ እንቅስቃሴው ላይ አሉታዊ እንቅስቃሴ እንዳያስከትል የማጠንፈፊያ ቦዮችና የጎርፍ መከላከያ እርከኖች በመሥራት ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባ ማሳሰቢያ ተሰጥቷል።

ከመደበኛ በላይና መደበኛ ዝናብ የሚጠበቅባቸው ቦታዎች ፦
- አፋር፣
- አማራ፣
- ትግራይ፣
- ኦሮሚያና ደቡብ ክልሎች መሆናቸውን ኢንስቲትዩቱ አሳውቋል።

በተለይም ለጎርፍ ተጋላጭ የሆኑ ማለትም ተዳፋትና ገደላማ አካባቢዎች የሚኖሩ ዜጎች ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ማሳሰቢያ ተላልፏል።

የክረምቱ የዝናብ ሁኔታ በሐምሌና ነሐሴ ወራት እንደሚጠናከር የሚጠበቅ ሲሆን መብረቅ፣ ጎርፍና የበረዶ ግግር ሊኖር ስለሚችል ማኅበረሰቡ ጥንቃቄ ማድረግ ይኖርበታል ተብሏል።

መረጃውን የኢትዮጵያ ብሄራዊ ሚትዎሮሎጂ ኢንስቲትዩትን ዋቢ አድርጎ ሪፖርተር ነው ያጋራው።

@tikvahethiopia
#ጥንቃቄ

ክረምቱ እየተጠናከረ ነውና #ከፍተኛ_ጥንቃቄ አድርጉ።

በተለይም በአዲስ አበባ ከተማ እየጣለ ካለው ከፍተኛ ዝናብ ጋር በተያያዘ በጎርፍ ምክንያት የሰዎች ህይወት እየጠፋ ፣ ንብረትም ላይም ጉዳት እየደረሰ ነው።

ትላንት ከክረምቱ ጋር በተያያዘ አደጋ ደርሶ የሰው ህይወት ጠፍቷል ፤ ንብረት ላይም ጉዳት ደርሷል።

- በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ወረዳ 3 አማኑኤል ሆስፒታል አካባቢ በአንድ መጋዘን ቤት ውስጥ ውሃ በመሙላቱ ግንቡ ተደርምሶ ከስር በሚገኙ መኖሪያ ቤቶች ውስጥ ግለሰቦች ላይ ጉዳት ደርሷል፤ በዚህም የ2 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል። ሌሎች ግለሰቦች ላይ ደግሞ ከባድ የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል። በአጠቃላይ በ8 ቤቶች የሚኖሩ 30 ቤተሰቦች ላይ ጉዳት ደርሷል።

🌊 የትላንቱ አደጋ የደረሰው የፍሳሽ ቦዮች በግንባታ ተረፈ ምርት በመደፈናቸውና ከዚህም ጋር ተያይዞ በጣለው ከባድ ዝናብ ሳቢያ ገንፍሎ የወጣ ጎርፍ በመጋዘን ቤት ውስጥ ተጠራቅሞ የመጋዘኑን አንዱን የግንብ ግድግዳ በመናዱ ነው። ቦታው ከዚህ ቀደም በስጋት ቀጠና ከተለዩት አንዱ ነው።

- በለሚ ኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 9፣ ልዩ ቦታው ፋና ወጊ በተባለ ቦታ ትላንት 9:00 ሰዓት ላይ በጣለው ከባድ ዝናብ በአካባቢው ነዋሪዎች የንብረት ጎዳትና መሠረት ልማቶች ላይ፤ የኮብልስቶን ንጣፍ መንገድ ፣ የወንዝ ድጋፍ ግንባታ ላይ ጉዳት ደርሷል። በዚህ ለሚ ኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 9 እና ወረዳ 07 ነዋሪዎችን የሚያገናኝ ድልድይ ላይ ጉዳት ደርሷል።

በሌሎችም አከባቢዎች ለጎርፍ አደጋ ስጋት የሆኑ ቦታዎች ላይ ህብረተሰቡ አስፈላጊውን ሁሉ ቅድመ ጥንቃቄ እንዲያደርግ መልዕክት ተላልፏል።

መረጃው የተሰባሰበው ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ነው።

@tikvahethiopia
#ጥንቃቄ

ከሰሞኑን እየጣለ ባለው ከባድ ዝናብ ሳቢያ በአማራ ክልል የሰው ህይወት ጠፍቷል ፤ በሰብል እንዲሁም በንብረት ላይ ጉዳት ደርሷል።

በምሥራቅ ጎጃም ዞን አዋበል ወረዳ ላይ አንድ አባዎራ ከባለቤታቸውና ልጃቸው ጋር ስራ ውለው ሲመለሱ በአካባቢው የሚገኘው ወንዝ በጎርፍ በመሙላቱ ለመሻገር ሙከራ እያደረጉ በወንዙ ተወስደዋል።

በዚህም የአንድ ቤተሰብ አባል የሆኑ የ3 ሰዎች ሕይወት አልፏል።

በሰሜን ወሎ ዞን ግዳን ወረዳ (በተከዜ ወንዝ መነሻ ላይ) በጎርፍ አደጋ  የ3 ሰዎች ሕይወት አልፏል።

ሕይወታቸው ካለፈው ሰዎች ሁለቱ፥ የአንድ ቤተሰብ አባላት ሲሆኑ አንዱ ከአጎራባች ወረዳ ለማኅበራዊ ጉዳይ በስፍራው የተገኘ ነበር።

በደቡብ ወሎ ዞን ወግዲ ወረዳ ነሃሴ 4 በጣለው ከባድ ዝናብ ባስከተለው ጎርፍ በሰብል እና ሌሎች ንብረቶች ላይ ከፍተኛ ጉዳት ደርሷል።

በስስይ እና ልጎ ጎጦች 30 ሄክታር በሚሆን መሬት ሰብል ጤፍ፣ ስንዴና ባቄላ ላይ ጉዳት አድርሷል። 120 አስሮ አደሮች እና 600 የሚሆኑ ቤተሰቦች በጎርፍ አደጋው ቤት ንብረታቸው አዝመራቸው ተጎድቷል።

12 አርሶ አደሮች የከፋ ውድመት የደረሰባቸው ሲሆን 4 አርሶ አደሮች የዕለት ጉርስ የሌላቸውና አቸኳይ ድጋፍን የሚጠብቁ ሆነዋል።

ባለፈው ሀምሌ ወር መጨረሻ ደግሞ በመርሀቤቴ ወረዳ 4 የአንድ ቤተሰብ አባላት በጎርፍ አደጋ ህይወታቸው አልፏል።

የግብርና ሥራን ለማከናወን 3 ልጆቹንና አንድ የልጅ ልጁን ይዞ ከመርሀቤቴ ወደ ሚዳ ወረሞ ወረዳ የተጓዘ አባወራ " ወንጭት " ወንዝን ሲያቁርጡ በደራሽ ጎርፍ ተወስደዋል።

በአደጋው የአባትን ሕይወት ማትረፍ ሲቻል ቀሪዎቹ የቤተሰብ አባላት ሕይወታቸው አልፏል።

መረጃዎች ፦ ከአዋበል፣ ወግዲ፣ ግዳን ኮሚኒኬሽኖች እና ኤፍ ቢሲ የተሰበሰቡ ናቸው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ጥንቃቄ

የወገኖቻንን ህይወት እየቀጠፈ ፤ ንብረትም እያወደመ ያለው የጎርፍ አደጋ !

በያዝነው ክረምት በተለያዩ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ በጎርፍ አደጋ የወገኖቻችን ህይወት እያለፈ ንብረትም እየወደመ ነው።

ለአብነት በአዲስ አበባ በተለያየ ጊዜ ህፃናት በጎርፍ አደጋ ህይወታቸው አልፏል ንብረት ወድሟል፣ በአማራ ክልል በተለያዩ ወረዳዎች በደረሰ የጎርፍ አደጋ የሰው ህይወት ጠፍቷል ፣ የአርሶ አደሮች ንብረትም እንዳልነበር ሆኗል።

ከትላንት በስቲያ ደግሞ ከወደ ኦሮሚያ ክልል፣ ጅማ ዞን ማና ወረዳ ሃሮ ቀበሌ እንደተሰማው የአንድ ቤተሰብ አባላትን የሆኑ ወገኖቻችን በጎርፍ ተወስደው ህይወታቸው አልፏል።

ከወረዳዋ ከተማ የቡ ተነስተው ሃሮ ወደተባለች ቀበሌ 3 ልጆቻቸውን ይዘው ሲጓዙ የነበሩ ቤተሰብ አንድ የ13 ዓመት እና ህጻን ልጅ በደራሽ ጎርፍ ሲወሰዱ አንድ ታዳጊ በህይወት ማግኘት ተችሏል።

በጎርፉ ከተወሰዱት የቤተሰብ አባላቱ የአባት አስከሬን በዕለቱ ሲገኝ፤ የሟች እናትና ሁለት ልጆች አስከሬን ትላንት ጠዋት ተገኝቷል።

የቤተሰብ አባላቱ ፤ በጎርፉ የተወሰዱት ዘመዶቻቸውን ለመጠየቅ ወደ ስፍራው ሲያቀኑ በነበረበት መሆኑን ዶቼ ቨለ ሬድዮ ጣቢያ የወረዳውን ኮሚኒኬሽን ዋቢ አደርጎ ዘግቧል።

በአማራ ክልል በአምባሰል ወረዳ ወገኖቻችን በጎርፍ አደጋ እና በመሬት መንሸራተት ከቤታቸው ተፈናቅለዋል ፤ ንብረታቸው ወድሟል።

በአጠቃላይ 150 አባወራዎች እና እማወራዎች ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለው በትምህርት ቤቶች፣ በቀበሌ ማዕከል፣ በገበሬ ማሰልጠኛዎችና በዘመድ ቤት ተጠልለው ይገኛሉ ብለዋል።

በወረዳው በቂ ለድጋፍ የሚሆን ሐብት ባለመኖሩ ለተጎጅዎች የሚመለከታቸው አካላት ሁሉ ድጋፋቸውን እንዲያደርጉ ተጠይቋል።

በሌላ በኩል ደግሞ ከሰሞኑን በአፋር ክልል በጎርፍ አደጋ የወገኖቻችን ህይወት ጠፍቷል ፤ ወገኖቻችን ተፈናቅለዋል፤ ከፍተኛ የሀብት ጥፋትም ደርሷል።

በሠመራ ከተማ ብቻ ጎርፍ ባስከተለው አደጋ በትንሹ የሶስት ሰዎች #ህይወት_አልፏል

በኤሊደአር  ወረዳ  ዶቢ ቀበሌ ደግሞ በጎርፍ አደጋ ከ3 መቶ ሺ ኩንታል በላይ የጨው ምርት ሙሉ በሙሉ ወድሟል።

በአካባቢው ላይ ከ300 በላይ የሚሆኑ ባለሀብቶች በጨው ምርት ላይ ተሰማርተው የሚገኙ ሲሆን አሁን ላይ ሁለት መቶ  የሚሆኑት አምራቾች በጎርፉ ምክንያት ኪሳራ ደርሶባቸዋል።

በተጨማሪም ጨው ለማምረት ተዘጋጅተው የነበሩ የጨው ማምረቻ ቦታወችም በጎርፉ ምክንያት ተበላሽተዋል።

አንድ አምራች የምርት ቦታዎችን ለማዘጋጀት ከ200 ሺ ብር በላይ ሊያወጣ ይችላል የተባለ ሲሆን ባጠቃላይ አምራቾች ላይ የደረሰው ኪሳራ ቀላል ሊባል የሚችል አይደለም።

በተጨማሪም ፤ በአሳይታና አፋምቦ ወረዳ ወገኖቻችን በአዋሽ ወንዝ ሙላት ሳቢያ በተከሰተ የጎርፍ አደጋ በቤት እና ንብረቶቻቸው ላይ ጉዳት ደርሶባቸዋል።

አሳይታ በርጋ ቀበሌ የሚኖሩ ወገኖቻችን በጎርፍ አደጋ እንስሳቶቻቸው ሞተውባቸዋል፣ ቤታቸው እንዳልነበር ሆኗል ፣ ሁለት ሺህ ሄክታር መሬት እርሻ ላይ ጉዳት አድርሶባቸዋል።

በአሁን ሰዓት ከቤታቸው ተፈናቅለው መጠለያ ውስጥ ናቸው።

የመንግስት፣ ማህበራዊ አገልግሎት ሚሰጡ ተቋማት በውሃ ውስጥ ናቸው ያሉት።

በተመሳሳይ ፤ በአፋምቦ ወረዳ ወገኖቻችን በአዋሽ ወንዝ ሙላትና በከባንድ ዝናብ ሳቢያ ቤት ንብረታቸው በጎርፍ አደጋ እንዳልነበር ሆኗል እነሱም ተፈናቅለዋል ፤ እንስሳቶቻቸው ሞተውባቸዋል ፤ እነኚህ ወገኖቻችን የመንግስት ድጋፍ እንፈልጋለን ብለዋል።

በዚሁ ወረዳ 6 ሺህ ሄክታር የጥጥ እና ሰሊጥ እርሻ ላይ ከፍተኛ የሆነ ጉዳት ደርሷል።

መረጃዎቹ የተሰባሰቡት ፦ ከአፋር ብዙሃን መገናኛ ፣ ከኤሊዲአር ወረዳ ኮሚኒኬሽን፣ ከዶቼ ቨለ ሬድዮ ፣ ከአምባሰል ወረዳ ኮሚኒኬሽን ነው።

@tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#ጥንቃቄ

በአዲስ አበባ ከባድ ዝናብ የጣለ ነው። በዚህም ሳቢያ በተለያዩ አካባቢዎች ላይ መንገዶች ለተሽከርካሪዎች ፈታኝ ሆነዋል።

አሽከርካሪዎች ፤ በእንደህ ያለው ወቅት ባለማሽከርከር የራሳችንን እና የሌሎችን ወገኖች ደህንነት ማስጠበቅ ይገባናል።

ቪድዮ : አብዱራህማን መኪ - ከደቂቃዎች በፊት ፒያሳ
አካባቢ (Tikvah Family)

@tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#ጥንቃቄ

የዘንድሮው ክረምት ተጠንክሮ በመቀጠሉ በሁሉም አካባቢ ያላችሁ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰቦቻችን ጥንቃቄ ማድረጋችሁን እንዳትዘነጉ።

በተለይ ለጎርፍ ተጋላጭ በሆኑ አካባቢዎች ያላችሁ አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንድታደረጉ ለማስታወስ እንወዳለን።

የመኪና አሽከርካሪ የሆችሁ ቤተሰቦቻችንም በየአካባቢው እየጣለ ባለው ከባድ ዝናብ ሳቢያ ጉዞ ላይ ከፍተኛ ጥንቃቄ በማድረግ የራሳችሁን እና የሌሎችንም ወገኖች ደህንነት ልታስጠብቁ ይገባል።

ሌላው ልጆች ያላችሁ የቤተሰባችን አባላት ልጆቻሁን ጠብቁ ፤ በተቻለ መጠን ከባድ ዝናብ ሲጥል ቤት ውስጥ እንዲቀመጡ በማድረግ ወቅቱን ማሳለፍ ይገባል። እጅግ አስፈላጊ ቦታ የሚሄዱ ከሆነም እንዲጠነቀቁ ማሳሰብ እንዳትዘነጉ።

#መልዕክት : ክረምት ሲመጣ ኑሯቸውን በጎዳና ላይ ያደረጉ ወገኖቻችን ምን ያህል እንደሚሰቃዩ ይታወቃል ፤ በግለሰብ ደረጃ ዘላቂ መፍትሄ መስጠት ባንችልም አንዳንድ የሚለበሱ ለብርድ የሚሆኑ አልባሳትን በመስጠት እንደሁል ጊዜው በበጎ ስራችን እንቀጥል።

ቪድዮ : AN ከአዲስ አበባ (አዳዋ ድልድይ) ቲክቫህ ቤተሰብ

@tikvahethiopia
#ጥንቃቄ

ከሰሞኑን በአዲስ አበባ ከባድ ያለ ዝናብ የጣለ ነው።

ዛሬም በረዶ የቀላቀለ ዝናብ ጥሏል።

ውድ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል የሆናችሁ አሽከርካሪዎች በዚህ ወቅት ስታሽከረክሩ የአየር ሁኔታውን ታሳቢ አድርጋችሁ እንዲሆን አደራ እንላለን።

ወላጆችም ልጆቻችሁን ጠብቁ። በተለይም ደግሞ ወቅቱ የትምህርት ሰዓት እንደመሆኑ ከቤት ወደ ከትምህርት ቤት ሲሄዱና ሲወጡ ከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ልጆቻችሁን አሳስቡ። የአየር ሁኔታውን ታሳቢ በማድረግ የሚደረብ ልብስም እንዲይዙ አድርጉ።

የትምህርት ተቋማት በዚህ በዝናብ ወቅት ለልጆች ደህንነት ተገቢውን ጥንቃቄ አድርጉላቸው።

በአጠቃላይ ውድ የአ/አበባ ቤተሰቦቻችን በተለይ ለጎርፍ ተጋላጭ በሆኑ ቦታዎች ያላችሁ ከፍተኛ ጥንቃቄ እንድታደርጉ እንላለን።

በአዲስ አበባ ከትናንት በስቲያ ምሽት በጣለው ዝናብ እናት እና ልጆችን ጨምሮ አራት ሰዎች በጎርፍ ተወስደው ህይወታቸው ማለፉ ይታወቃል።

ፎቶ፦ ከማህበራዊ ሚዲያ

@tikvahethiopia
#ድሬ

ትላንት ምሽቱን በድሬዳዋ ከተማ በጣለው ከባድ ዝናብ ምክንያት በጎርፍ የአንድ ሰው ህይወት ያለፈ ሲሆን በንብረትም ላይ ጉዳት ደርሷል።

የድሬዳዋ ከተማ ፖሊስ እንዳሳወቀው ፤ በቀበሌ 07 አፈተ-ኢሳ / አሸዋ ሰልባጅ ተራ / ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ በጎርፍ መውረጃ አሸዋ ውስጥ ተኝቶ የነበረው የ55 አመት ጎልማሳ በተከሰተው የጎርፍ አደጋ በተኛበት ህይወቱ አልፎ የተገኘ ሲሆን የሰልባጅ ልብስ መሸጫ ቦታው ላይ ጉዳት ደርሷል።

የ55 አመቱ ጎልማሳ በአካባቢው ላይ የቀን ስራ እየሰራ ራሱን እና ቤተሰቡን የሚያስተዳድር ግለሰብ መሆኑን የገለጸው ፖሊስ ለተጨማሪ ምርመራ አስክሬኑ ወደ ድልጮራ ሪፈራል ሆስፒታል ተልኳል ብሏል።

ከመጋቢት 7 - መጋቢት መጨረሻ ድረስ መደበኛ እና ከመደበኛ በላይ ዝናብ ሊዘንብ እንደሚችል የሜትዮሮሎጂ ትንበያ መረጃ የሚያመለክት ሲሆን በድሬዳዋ አስተዳደር ለጎርፍ ተጋላጭ የሆኑ አካባቢዎች ላይ ያሉ የህብረተሰብ ክፍሎች ተገቢውን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ የድሬዳዋ የአደጋ ስጋት ኮሚሽን የቅድመ ማስጠንቀቂያ ዳሬክቶሬት መረጃ ሲሰጥ ቆይቷል ተብሏል።

በሌላ ዜና ፦ መጋቢት 18 ቀን 2015 ዓ.ም ከቀኑ ዘጠኝ ሰአት ገደማ ቀበሌ 09 " ገንደ ገመቹ " ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ከአንድ ግለሰብ መኖሪያ ቤት የገባ #ከርከሮ በቤቱ ባለቤት ላይ ከባድ የአካል ጉዳት አድርሷል።

በአሁኑ ወቅት ግለሰቡ በድልጮራ ሪፈራ ሆስፒታል በህክምና ላይ የሚገኝ ሲሆን በድሬዳዋ ከተማ ዳርቻ የሚኖሩ የህብረተሰቡ ክፍሎች ተገቢውን #ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለባቸው ፖሊስ አሳስቧል፡፡

#ድሬፖሊስ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የሱዳን ነገር ከቁጥጥር እየወጣ ይሆን ? የአል-ሱዳኒ ጋዜጣ ማኔጂንግ ኤዲተር ያሲር አብዱላህ ሀገሪቱ ወደ ከፋ የእርስ በርስ ጦርነት እያመራች እንደሆነ አስጠንቅቋል። በሀገሪቱ ያለው ሁኔታ እጅግ በጣም አሳሳቢ ነው ብሏል። እስር በርስ የሚደረገውን ግጭት ለማስቆም በሰራዊት አመራሮች በኩል ምንም አይነት ጣልቃ ገብነት ከሌለ ሁኔታው እጅግ ወደ ከፋ ሙሉ የእርስ በርስ ጦርነት እያመራ ነው ሲል ገልጿል።…
#ጥንቃቄ

ሱዳን ለምትገኙ የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት !

የሱዳን አየር ኃይል የRSF ኃይሎች ይገኙባቸዋል ባላቸው አካባቢዎች ቅኝት እንደሚያካሂድ አሳውቋል።

አየር ኃይሉ ሁሉም በሱዳን ውስጥ ያሉ ዜጎች / ሰዎች በቤት ውስጥ የመቆየት / ከቤታቸው እንዳይወጡ አስጠንቅቋል።

በሱዳን ያላችሁ የቲክቫህ ቤተሰቦቻችን እራሳችሁን እና የምትወዷቸውን ሁሉ እንድትጠብቁ ፤ የሚወጡትን ትዕዛዞችን እየተታተላችሁ እንድትፈፅሙ አደራ እንላችኃለን።

@tikvahethiopia
#ጥንቃቄ

ዛሬ ጥዋት ፤ በወላይታ ዞን #ከአረካ ወደ #ሶዶ ተሳፋሪዎችን ጭኖ ይጓዝ በነበረ አንስተኛ የሕዝብ ማመላለሻ መኪና ላይ የመገልበጥ አደጋ ደርሷል።

በአደጋውም የአንድ ሰው ሕይወት ሲያልፍ 4 ሰው ላይ ቀላል የአካል ጉዳት መድረሱ ታውቋል።

- አደጋ የደረሰበት ተሽከርካሪ ፦ ኮድ-3 ደቡብ 25715 በተለምዶ ሀይሩፍ እየተባለ የሚጠራው መኪና ነው።

- 17 ተሳፋዎችን ይዞ ከፍጥነት በላይ ሲጓዝ መሥመር በማሳት ከላሾ ከተማ ወረድ ብሎ በሚገኘው ካሬታ ሃታ/ወንዝ ውስጥ ገብቷል።

- በአደጋው የአንድ ሰው ህይወት ሲየልፍ በአራት ሰው ላይ ቀላል አደጋ ደርሷል።

የሶዶ ዙሪያ ወረዳ ፖሊስ ጽህፈት ቤት ፤ የመኪና አሽከርካሪዎች ጊዜው #የዝናብ_ወቅት ስለሆነ በክፍተኛ ጥንቃቄ እንዲያሽከረከሩ ጥሪ አቅርቧል።

መረጃው የወላይታ ዞን ኮሚኒኬሽን ነው።

@tikvahethiopia @tikvah_Eth_BOT