TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.4K photos
1.47K videos
209 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
አቶ ኢሳያስ ዳኘው‼️

ፍርድ ቤቱ በሙስና ወንጀል በተጠረጠሩት አቶ #ኢሳያስ_ዳኘው ላይ 10 ቀናት ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ፈቀደ።

አመልካች የፌዴራሉ ወንጀል ምርመራ ቢሮ በተጠርጣሪው ላይ ተጨማሪ 14 ቀናት የጊዜ ቀጠሮ ጠይቆ የነበረ ሲሆን የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ከታህሳስ 4 ቀን 2011 ዓ.ም ጀምሮ የሚታሰብ የ10 ቀናት ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ በመፍቀድ ለታህሳስ 15 ቀን 2011 ዓ.ም ፖሊስ ምርመራውን አጠናቆ እንዲቀርብ አዟል።

በተጠርጣሪነት የቀረቡት አቶ ኢሳያስ ዳኘው የኢትዮ­ ቴሌኮም የስራ ኃላፊ በነበሩበት ወቅት ድርጅታቸው በሶማሌ ክልል የሞባይል ተደራሽነትን ለማስፋት የሞባይል ሲ ዲ ኤም ስራዎችን ለማከናወን የብረታ ብረት ኢንጅነሪንግ ኮርፖሬሽን (ሜቴክ) ጋር የገባውን የውል ስምምነት ማሻሻያ በማድረግ በሌላቸው ኃላፊነት ሙሉ ክፍያ እንዲፈጽም በማድረግ ወንጀል ፖሊስ ጠርጥሯቸዋል።

በውሉ መሰረትም 201 ሚሊዮን ብር የነበረውን ውል ተጨማሪ ሳይት ለመገንባት በሚል ወደ 322 ሚሊዮን ብር ክፍያ እንዲፈም ለፋይናንስ ክፍል ደብዳቤ ጽፈዋል ብሏል።

ተጠርጣሪው ትናንት በችሎቱ ቀርበው በነበሩበት ወቅት ኢትዮ ቴሌኮም ሥራውን ካለምንም ጨረታ ለሜቴክ ቢሰጥም ሜቴክ ግን ለ17 ንዑስ ተቋራጮች በመስጠት ጥራት በጎደለው ሁኔታ እንዲሰራ፣ የተከናወነው ሥራም 91 ነጥብ 8 በመቶ ቢሆንም ሙሉ ክፍያው መፈጸሙን አስረድቷል።

የተጠርጣሪው ጠበቆች በበኩላቸው በተቋማቱ መካከል ስምምነቱ በተደገበት ወቅት በሶማሌ ክልል በነበረው የጸጥታ ችግር ምክንያት ሌሎች ተቋራጮች እንዳይገቡ ተደርጎ በቦርድ ውሳኔ ለሜቴክ የተሰጠ በመሆኑ ተጠርጣሪን አይመለከትም ብለዋል።

ለዚህ ደግሞ ተጠረጣሪው አስፈላጊውን ማስረጃ መስጠት እንደሚችሉ፣ መርማሪለመወሰን ፖሊስ ምርመራውን በትጋት ባለመስራቱ እንጂ ተጠርጣሪውን ለ35 ቀናት በእስር ሊያስቆይ የሚችል ምክንያት እንደሌለ በመግለፅ ተከራክረዋል።

ተጠርጣሪው የዋስትና መብታቸው ተከብሮ በውጭ ሆነው እንዲከራከሩም ጠበቆቹ ጠይቀዋል።

የግራ ቀኙን ክርክር ያደመጠው አስረኛው ወንጀል ችሎት በተጠየቀው የተጨማሪ ጊዜና ዋስትና ጥያቄ ላይ ለዛሬ ከሰዓት ቀጠሮ በሰጠው መሰረት ግራ ቀኙ ባደረጉት ክርክር መሰረት ለፖሊስ 10 ተጨማሪ የምርመራ ቀናት ፈቅዷል።

 ምንጭ፦ ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አቶ ኢሳያስ በዋስ ሊለቀቁ ነው‼️

የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቶ #ኢሳያስ_ዳኘው (የሜጀር ጀነራል ክንፈ ዳኛው ወንድም) በ200 መቶ ሺህ ብር ዋስ እንዲለቀቁ ወሰነ። ግለሰቡ በኢትዮ ቴሌኮም የኤን ጂ ፒ ኦ ዳይሬክተር የነበሩትና ለሜቴክ የተሰጠን ውል በማሻሻልና ክፍያ እንዲፈጸም በማድረግ በመንግስት ላይ ጉዳት እንዲደርስ አድርገዋል በሚል በከባድ የሙስና ወንጀል ነበር የተጠረጠሩት።

መርማሪ ፖሊስ በተፈቀደለት የሰባት ቀን ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ውስጥ ኢትዮ ቴሌኮም ከፕሮጀክቱ ጋር የተያያዘ የኦዲት ሪፖርት እንዲያዘጋጅልን ጠይቀን እንዳልጨረሱልን የሚገልጽ ደብዳቤ ጽፈውልናል ብሏል።

ከዚህ ባለፈም ከሳይት ርክክብ ጋር በተያያዘ ከአዲስ አበባ ውጭ የምንቀበለውን የምስክርነት ቃል በተሰጠን ጊዜ ውስጥ መቀበል ባለመቻላችን ተጨማሪ የ14 ቀን የማጣሪያ ጊዜ ይፈቀድልን ብሎ ጠይቆም ነበር።

የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 10ኛ የወንጀል ችሎትም የቴሌ ታወር ተከላ ፕሮጀክቱ ትልቅ እንደመሆኑ ኢትዮ ቴሌኮም የኦዲት ሪፖርት አላሰራም ገና እያሰራ ነው መባሉ አሳማኝ ምክንያት አለመሆኑን ጠቅሷል።

ከአዲስ አበባ ውጭ የምንቀበለው የምስክርነት ቃል አለ በሚል የተገለጸውም ቢሆን በተሰጣችሁ ጊዜ ውስጥ የምስክርነት ቃሉን መቀበል ትችሉ ነበር በማለት መርማሪ ፖሊስ የጠየቀውን ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ቀጠሮ ሳይፈቅድ ቀርቷል።

የተጠርጣሪ ጠበቆች መርማሪ ፖሊስ ስራውን በተገቢ ሁኔታ እየሰራ አይደለም፤ እስካሁን የተፈቀደው ቀን ይበቃል ተጠርጣሪው በዋስ ወጥተው እንዲከራከሩ ይፈቀድልን በሚል ያቀረቡትን ጥያቄ ችሎቱ ተቀብሎ ተጠርጣሪው በዋስ እንዲወጡ ወስኗል።

የተጠርጣሪውን የግል ሁኔታ ከግምት በማስገባትም በሁለት መቶ ሺህ ብር ዋስ እንዲለቀቁ ችሎቱ ወስኗል፤ ከዚህ ባለፈም ተጠርጣሪው ከሃገር እንዳይወጡ እግድ ተላልፎባቸዋል።

መርማሪ ፖሊስም ይግባኝ ስለምጠይቅ ዋስትናው ይታገድልኝ ሲል ጠይቆ ችሎቱ አቤቱታውን በጽሁፍ ማመልከቻ እንዲያስገባ አዟል።

ምንጭ፦ fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ከፍተኛው ፍርድ ቤት ለሙስና ተጠርጣሪው የጄኔራል ክንፈ ዳኘው ወንድም #ኢሳያስ_ዳኘው ፈቅዶት የነበረውን የዋስትና መብት ዛሬ ጠቅላይ ፍርድ ቤት እንደሻረው ካፒታል ዘግቧል፡፡ ከፍተኛው ፍርድ ቤት የቀድሞው የኢትዮ-ቴሌኮም ከፍተኛ ሃላፊ ለነበሩት ተጠርጣሪ ከሳምንት በፊት በዋስትና እንዲፈቱ ማዘዙ ይታወሳል፡፡ ተጠርጣሪው ከብረታ ብረትና ኢንጅነሪንግ ኮርፖሬሽን (ሜቴክ) ጋር በተያያዘ ሙስና ወንጀል ነበር ተጠርጥረው የታሰሩት።

via wazemaradio
@tsegabwolde @tikvahiopia
TIKVAH-ETH ማጠቃለያ🗞ጥር 20/2011 ዓ.ም.

የጀርመን ፌዴራል ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት ዶ/ር #ፍራንክ_ዋልተር_ሽቴይንሜይር በኢትዮጵያ ይፋዊ የስራ ጉብኝት እያደረጉ ይገኛሉ።
.
.
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቀድሞ አፈ ጉባኤ አቶ #ዳዊት_ዮሃንስ ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸው ተሰምቷል።
.
.
ቅዱስ ጴጥሮስ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል #የደም_ስር_መጥበብ ችግር ላለባቸው ታካሚዎች ከዛሬ ጀምሮ ለአምስት ተከታታይ ቀናት የፒሲአይ የነጻ ህክምና አገልግሎት መስጠት ጀምሯል።
.
.
ጠ/ሚር #ዐቢይ_አሕመድ ኢትዮጵያን እየጎበኙ ካሉት ከጀርመን ፌደራል ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት ፍራንክ ዋልተር ስታይንማየር ልዑካቸውን ተቀብለው አነጋግረዋል።
.
.
ለኢፌድሪ ፕረዝዳንት ወ/ሮ ሳህለወርቅ ዘውዴ እና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ም/ከንቲባ ታከለ ኡማ(ኢ/ር) የEuropean Tourism Academy Membership ሽልማት ሊሠጥ እንደሆነ ተሰምቷል።
.
.
የኢትዮጵያ ክፍያ መንገዶች ኢንተርፕራይዝ በ2011 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ስድስት ወራት 4 ሚሊየን 234 ሺህ 856 መቶ ተሸከርካሪዎች በማስተናገድ በአጠቃላይ ብር 124 ሚሊየን 578 ሺህ 594 መቶ ብር መሰብሰብ መቻሉ ተሰምቷል።
.
.
#አለን_ኢትዮጵያ የበጎ-አድራጎት ድርጀት የሰው ልጆች የለውጥ ማዕከል ህጋዊ እውቅና በማግኘት ትላንት በ19/05/01 ዓ.ም በወላይታ ሶዶ ከተማ በይፋ ሥራ ጀምሯል።
.
.
በአንድ ፒካፕ ተሽከርካሪ ላይ በተደረገ ፍተሻ ከባህርዳር ወደ አዲስ አበባ ሲጓጓዙ የነበረ ሦስት መትረየስ፣ 1924 የስታር እና 1856 የማካሮቭ ሽጉጥ ጥይቶች ከ37 የጥይት መያዥ ጋር #መያዙን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል።
.
.
የጀርመኑ ግዙፍ የመኪና አምራች ኩባንያ ቮልስዋገን ከኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ጋር የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርሟል።
.
.
የሚድሮክ ግሩፕ የሼክ ሙሀመድ ሁሴን አሊ አላሙዲንን ከእስር #መፈታትን ምክንያት በማድረግ ሠራተኞቹን #አንበሻብሿል
.
.
ከፍተኛው ፍርድ ቤት ለሙስና ተጠርጣሪው የጄኔራል ክንፈ ዳኘው ወንድም #ኢሳያስ_ዳኘው ፈቅዶት የነበረውን የዋስትና መብት ዛሬ ጠቅላይ ፍርድ ቤት እንደሻረው ካፒታል ዘግቧል፡፡
.
.
ጠ/ሚር ዶክተር #ዐቢይ_አሕመድ ዛሬ ምሽት #በብሄራዊ_ቴአትር በየሶስት ወሩ የሚካሄደውን የኪነ ጥበብና የባህል ምሽት ተካፍለዋል።
.
.
ሚድሮክ ኢትዮጵያ የሼክ ሞሃመድ አላሙዲን መፈታት አስመልክቶ፦ የሚድሮክ ንብረት በሆነው #ዩኒቲ_ዩኒቨርስቲ የሚማሩ ተማሪዎች ላንድ ወሰነ ትምህርት(1 ሴሚስተር) #በነጻ እንዲማሩ ፈቅዶላቸዋል፡፡
.
.
ምንጭ፦ ዋልታ፣ ፋና፣ ኢ.ፕ.ድ.፣ ዋዜማ ሬድዮ፣ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን፣ የጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት፣ የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት
.
.
ሰላም እደሩ!!
የነገ ሰው ይበለን!!
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አቶ ኢሳያስ ከእስር #እንዲፈቱ ትዕዛዝ ተሰጠ‼️

የሥር ፍርድ ቤት ማለትም የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ አሥረኛ ወንጀል ችሎት በ100 ሺሕ ብር ዋስ እንዲፈቱ ትዕዛዝ ከሰጠ በኋላ፣ ትዕዛዙ በይግባኝ ታግዶ ለአንድ ወር ታስረው የከረሙት አቶ #ኢሳያስ_ዳኘው በተመሳሳይ ዋስትና ከእስር እንዲፈቱ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ማክሰኞ የካቲት 5 ቀን 2011 ዓ.ም. ትዕዛዝ ሰጠ፡፡

የሥር ፍርድ ቤትን ትዕዛዝ በመቃወም የፌዴራል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ይግባኝ ብሎ ወደ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመሄድ፣ በተጠርጣሪው ላይ ቀሪ ምርመራ እንዳለው በማስረዳት ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ እንዲሰጠው ጠይቆ ነበር፡፡ ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት ግን ይግባኙን ውድቅ ሲያደርግበት፣ ሐሳቡን በመቀየር የክስ መመሥረቻ ጊዜ እንዲሰጠው ጠይቋል፡፡

ፍርድ ቤቱም አሥር ቀናት በመፍቀድ በተሰጠው ቀናት ውስጥ ክስ ማቅረብ ካልቻለ፣ የሥር ፍርድ ቤት ቀደም ብሎ በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት ተጠርጣሪውን ከእስር እንዲፈታቸው ትዕዛዝ ሰጥቶ ነበር፡፡

ዓቃቤ ሕግ በይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት በተሰጠው አሥር ቀናት ውስጥ ክሱን መመሥረት ባይችልም፣ የሥር ፍርድ ቤት የክስ መመሥረቻ 15 ቀናት እንዲፈቅድለት አቅርቦ ነበር፡፡ ፍርድ ቤቱ የተጠርጣሪ ጠበቆች አስተያየት እንዲሰጡበት ሲጠይቅ፣ የሥር ፍርድ ቤት የበላይ ፍርድ ቤትን ትዕዛዝ መፈጸም እንጂ ያንን አልፎ የሚያከራክርበት ሥልጣን እንደሌለው በመግለጽ፣ ደንበኛቸው በጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ መሠረት ከእስር እንዲፈቱላቸው ጠይቀው ነበር፡፡

ዓቃቤ ሕግ በበኩሉ በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 109(1) መሠረት ክስ የመመሥረቻ ጊዜና ቀናት ብቻ መሆኑን ቢደነገግም፣ በተለያዩ አዋጆች ተጨማሪ ጊዜ ማስፈቀድ የሚቻል መሆኑን ለማስረዳት ሞክሮ ነበር፡፡

ፍርድ ቤቱ ግን የሁለቱንም ወገኖች መከራከሪያ ሐሳብ በማለፍ፣ ቀደም ብሎ ከሰጠው ትዕዛዝ ውጪ ተጨማሪ ትዕዛዝ የመስጠት ሥልጣን እንደሌለው በመግለጽ፣ ተጠርጣሪው በሌላ ፍርድ ቤት አመልክተው ከእስር እንዲፈቱ ማድረግ እንደሚችሉ (HabeasCorpus) በመግለጽ መዝገቡን ዘግቶት ነበር፡፡

የተጠርጣሪው ጠበቆች በድጋሚ ለጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ በማለት፣ ቀደም ብሎ የሰጠው ትዕዛዝ ተግባራዊ አለመሆኑንና የሥር ፍርድ ቤት መዝገቡን እንደዘጋው በመግለጽ አመልክተዋል፡፡ ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት የሥር ፍርድ ቤት ለዓቃቤ ሕግ የተፈቀደለት አሥር ቀናት ሲጠናቀቅ ተጠርጣሪን እንዲፈታ ትዕዛዝ መስጠቱን አስታውሶ፣ ግለሰቡ አቤቱታው እስካቀረበበት ቀን ድረስ (ከየካቲት 1 እስከ 5 ቀን 2011 ዓ.ም. ድረስ) ለሕገወጥ እስር መዳረግ እንዳልነበረባቸው በመግለጽ፣ ከእስር እንዲፈቱ በድጋሚ ትዕዛዝ መስጠቱ ታውቋል፡፡ 

ምንጭ፦ ረፖርተር
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አቶ ኢሳያስ በዋስ እንዲወጡ ተወሰነ‼️

ፍርድ ቤቱ መርማሪ ፖሊስ አቶ #ኢሳያስ_ዳኘው በዋስ ሊለቀቁ አይገባም በሚል ያቀረበውን ይግባኝ ውድቅ አደረገ። በከባድ የሙስና ወንጀል የተጠረጠሩት አቶ ኢሳያስ ዳኘው በተጠረጠሩበት ወንጀል በፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 10ኛ የወንጀል ችሎት ቀርበው ጉዳያቸውን ሲከታተሉ ከቆዩ በኋላ በ50 ሺህ ብር ዋስ እንዲወጡ #ተፈቅዶላቸዋል

መርማሪ ፖሊስም ግለሰቡ በዋስ መውጣት የለባቸውም በሚል ለጠቅላይ ፍርድ ቤት ያቀረበው ይግባኝ ውድቅ ተደርጎበታል።

በመሆኑም ከዚህ ቀደም በተወሰነው መሰረት በ50 ሺህ ከሃገር እንዳይወጡ በተጣለ እገዳ #በዋስ እንዲለቀቁ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ውሳኔውን አፅንቷል።

አቶ ኢሳያስ ዳኘው በኢትዮ ቴሌኮም የኤን ጂ ፒ ኦ ዳይሬክተር ሆነው በሚሰሩበት ወቅት ለሜቴክ የተሰጠን ውል በማሻሻልና ክፍያ እንዲፈጸም በማድረግ በመንግስት ላይ ጉዳት እንዲደርስ አድርገዋል በሚል በከባድ የሙስና ወንጀል ነበር የተጠረጠሩት።

ምንጭ፦ ፋና ብሮድካስቲንግ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሰበር ዜና‼️

ዛሬ ጠዋት ጠቅላ ፍርድ ቤት የፌደራል ፖሊስ አቤቱታን ውድቅ በማድረግ ከእስር እንዲፈቱ ትእዛዝ የተሰጠላቸው አቶ #ኢሳያስ_ዳኘው ሌላ ክስ ተመስርቶባቸው ማረሚያቤት ወረዱ። የተመሰረተባቸው ክስ ዩኒቨርስቲዎችን በኔትወርክ ለማገናኘት ከተደረገ ውል ጋር በተገናኘ ነው ተብሏል።

ምንጭ፦ ታምሩ ፅጌ (ሪፖርተር)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETH ማጠቃለያ🗞የካቲት 13/2011 ዓ.ም. #ሼር #Share @tikvahethiopia

የለገጣፎ -ለገዳዲ ከተማ አስተዳደር አረንጓዴ ቦታዎችን፥ የወንዝ ዳርቻዎችን፥ ከፈቃድ ውጭ የተያዙ እና ካሳ ተከፍሎባቸው ግንባታ የተካሄደባቸው ናቸው ያላቸውን ቤቶች እያፈረሰ ውሏል።
.
.
በሃዋሳ ከተማ ነገ ለሚካሄደው የሲዳማ ህዝበ ውሳኔ #ይፋጠንልን ህዝባዊ ሰላማዊ ሰልፍ በሰላም እንዲጠናቀቅ በቂ ዝግጅት ማድረጉን የሃዋሳ ከተማ ፖሊስ አስታውቋል።
.
.
የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ባደረገው ክትትል በተሽከርካሪ አካል ውስጥ በረቀቀ መንገድ #ተደብቆ ወደ አዲስ አበባ የገባ 4 መትረዬስ ጠብመንጃ እና ከ46 ሺ በላይ ጥይት መያዙን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሸን አስታውቋል፡፡
.
.
ዛሬ ጠዋት ጠቅላ ፍርድ ቤት የፌደራል ፖሊስ አቤቱታን ውድቅ በማድረግ ከእስር እንዲፈቱ ትእዛዝ የተሰጠላቸው አቶ #ኢሳያስ_ዳኘው ሌላ ክስ ተመስርቶባቸው ማረሚያቤት ወርደዋል።
.
.
በምዕራብ ጎንደር ዞን #መቃ በተባለች አነስተኛ ከተማ በትንሹ 17 ሰዎች በትናንትናው ዕለት በአካባቢው ነዋሪዎች #መታገታቸውን የዐይን እማኝ ተናግረዋል።
.
.
ነገ ለሚደረገው #ሰላማዊ_ሰልፍ የሀዋሳ ከተማ ፖሊስ ከዞን ፖሊስ፣ ከክልሉ ልዩ ሃይልና #ከፌደራል_ፖሊስ ጋር በመቀናጀት ሰልፉ በሚካሄድባቸው አካባቢዎች በቂ ጥበቃ ያደርጋል።
.
.
ጠ/ሚር #ዐቢይ_አሕመድ የሶማሊላንድ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ሙሴ ቢሂ አብዲንና ልዑካቸውን በጽ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።
.
.
የደኢህዴን ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ መደበኛ ስብሰባ ከየካቲት 12/06/2011 ዓ.ም ጀምሮ #በአርባምንጭ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።
.
.
የአማራ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (አዴፓ) ለተፈናቀሉ ወገኖች 5 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ማድረጉን አስታውቋል፡፡
.
.
የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን እና ሬድዮ /ኢሳት/ ጋዜጠኞች ዛሬ ኢቢሲን ጎብኝተዋል።
.
.
የሀረሪ ብሄራዊ ሊግ ማዕከላዊ ኮሚቴ መደበኛ ስብሰባውን እያካሄደ ነው፡፡ ማዕከላዊ ኮሚቴው ለሁለት ቀናት  በሚያካሂደው መደበኛ ስብሰባም በአራት አጀንዳዎች ላይ ውይይት በማድረግ ውሳኔ ያሳልፋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
.
.
አክሱም ሽረ እንደስላሴ መስመር ላይ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ7 ሰዎች ህይወት አለፈ፡፡ የትራፊክ አደጋው ከሽረ እንደስላሴ ወደ አክሱምና ከአክሱም ወደ ሽረ እንደስላሴ  ሲጓዙ የነበሩ ተሽከርካሪዎች #በመጋጨታቸው ያጋጠመ ነው ተብሏል፡፡
.
.
በህገ ወጥ ግንባታዎች ላይ እየተወሰደ ያለው እርምጃ ህግን መሰረት ያደረገ መሆኑን የኦሮሚያ ክልል መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ቢሮ ሃላፊ ዶክተር #ሚልኬሳ_ሚደግሳ ተናግረዋል።
.
.
በለገጣፎ_ለገዳዲ ከተማ ቤታቸው #የፈረሰባቸው ዜጎች ችግር ላይ መውደቃቸውን ተናግረዋል።

ምንጭ፦ ኢዜአ፣ ኢ.ፕ.ድ፣ fbc፣ etv፣ ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት፣ የአሜሪካ ድምፅ ራድዮ፣ wazemaradio፣ የጀርመን ራድዮ፣ OBN፣ የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር

@tsegabwolde @tikvahethiopia