TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.7K photos
1.49K videos
211 files
4.06K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#Oromia " የልዩ ኃይል ስምሪት አቁመናል ፤ ... በክልሉ ያለውን የፀጥታ ማስከበር ሥራ የአገር መከላከያ ሠራዊት ተረክቧል " - የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን የኦሮሚያ ክልል መንግሥት የልዩ ኃይል አደረጃጀት ስምሪት ማቆሙን አስታወቀ። የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር አራርሳ መርዳሳ ከዶይቼ ቬለ ጋር ባደረጉት ቃለመጠይቅ ነው ይህንን ያሳውቁት። ዋና ኮሚሽነሩ ለሬድዮ ጣቢያው በሰጡት ቃል ፤  የፌዴራሉ…
#Oromia

የክልል ልዩ ኃይሎችን መልሶ የማደራጀት ተግባር መጀመሩን ተከትሎ የኦሮሚያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የልዩ ኃይል ስምሪት #ማቆሙን ገልጿል።

በክልሉ ያለውን የፀጥታ ማስከበር ስራ የአገር መከላከያ ሰራዊት መረከቡንም አሳውቋል።

የኦሮሚያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ጄነራል አራርሳ መርዳሳ ፤ ለዶቼ ቨለ ሬድዮ ጣቢያ በሰጡት ቃለ ምልልስ ነው ይህን ያሉህ።

ኦሮሚያ የሚንቀሳቀሰው መንግሥት " ሸኔ " እያለ የሚጠራውና እራሱን የኦሮሞ ነጻነት ጦር ብሎ የሚጠራው ታጣቂ ቡድን የመንግሥትን ጥሪ በመቀበል እንቅስቃሴውን የሚያቆም ከሆነ በክልል ሌሎች የፀጥታ ሥራዎች #በመደበኛ_ፖሊስ እንደሚከወኑ ያሳወቁት ጄነራል አራርሳ ለጊዜው ግን የዜጎች ደህንነት አደጋ ላይ እንዳይወድቅ የመከላከያ መከላከያ ሰራዊት ኃላፊነቱን ተረክቧል ብለዋል።

በኦሮሚያ ላይ አሁናዊ የፀጥታ ሁኔታው #አስተማማኝ_እንዳልሆነ ያልሸሸጉት ኮሚሽነሩ በተለያየ ስያሜ በመንቀሳቀስ ኅብረተሰቡን የሚያፈናቅሉ መኖራቸውን ለሬድዮ ጣቢያው በሰጡት ቃለምልልስ ገልጸዋል።

@tikvahethiopia