#ችሎት
የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ ፍርድ ቤት አንደኛ ወንጀል ችሎት በሲዳማ ዞን የተለያዩ አካባቢዎች ተከስቶ የነበረዉን ሁከት #ቀስቅሰዋል በሚል ተጠርጥረው የተያዙ ዘጠኝ ግለሰቦች በዋስ እንዲፈቱ ወሰነ።
ፍርድ ቤቱ ዛሬ በዋለው ችሎት በዋስ እንዲፈቱ ከወሰነላቸዉ ተጠርጣሪዎች መካካል የሲዳማ ሚዲያ ኔትዎርክ ዋና ስራ አስኪያጅ ጌታሁን ደጉዬ ፣ ምክትላቸው ታሪኩ ለማ እና የእዚሁ ጣቢያ የቦርድ አባል የሆኑት በላይ ባልጉዳ ይገኙበታል። ፖሊስ #በተጠርጣሪዎቹ ላይ #ቀሪ የምስል፣ የድምፅ፣ የሰነድ እና የሰው ማስረጃዎችን ለማሰባሰብ ተጨማሪ የ14 ቀናት የጊዜ ቀጠሮ እንዲሰጠው ፍርድ ቤቱን ጠይቆ ነበር።
ፍርድ ቤቱ ግን እስከአሁን አራት የጊዜ #ቀጠሮዎች መሰጠታቸውንና መርማሪ ፖሊስም በማስረጃ አሰባሰብ ሂደት አከናወንኩ ያላቸው ስራዎች ተመሳሳይ መሆናቸውን በመጥቀስ የቀረበውን ተጨማሪ የ14 ቀናት የጊዜ ቀጠሮ ዉድቅ አድርጎታል። ፍርድ ቤቱ ተጠርጣሪዎቹ እያንዳንዳቸው የ50 ሺህ ብር ዋስትና በማቅረብ ጉዳያቸውን ውጭ ሆነው እንዲከታተሉ ወስኗል። ተጠርጣሪዎቹ ለነሀሴ 14 ቀን 2011 ዓ.ም. እንዲቀርቡም አዟልም።
Via #DW
@tsegabwolde @tikvahethiopia

"ከዚህ በኃላ ፍትህን ከመንግስት ሳይሆን ከእግዜያብሄር ነው የምጠብቀው"
በሲዳማ ዞን የተለያዩ አካባቢዎች ተከስቶ የነበረዉን ሁከት #ቀስቅሰዋል በሚል ተጠርጥረው የተያዙ ዘጠኝ ግለሰቦች በዋስ እንዲፈቱ የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ ፍርድ ቤት አንደኛ ወንጀል ችሎት የወሰነላቸው ቢሆንም እስካሁኗ ደቂቃ ድረስ ከእስር እንዳልተፈቱ ቤተሰቦቻቸው ለTIKVAH-ETH ተናገሩ። ፍርድ ቤቱ ትላንት በዋለው ችሎት በዋስ እንዲፈቱ ከወሰነላቸዉ ተጠርጣሪዎች መካካል የሲዳማ ሚዲያ ኔትዎርክ ዋና ስራ አስኪያጅ ጌታሁን ደጉዬ ፣ ምክትላቸው አቶ ታሪኩ ለማ እና የጣቢያው የቦርድ አባል የሆኑት በላይ ባልጉዳ ይገኙበታል።
በጉዳዩ ላይ ለTIKVAH-ETH የተናገሩት ከታሳሪዎቹ ቤተሰቦች አንደኛው ይህን ብለዋል፦
"የዋስትና ደብዳቤውን በጊዜ ነው ጨርሰን የሄድነው፤ ፖሊስ ግን ሊፈታቸው ፍቃደኛ አልነበረም። ፖሊስ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ደብዳቤ አስገብቻለሁ አለን፤ ነገር ግን ሄደን ስናይ ያስገባውና የተፈቀደለት እግድ የለም ነገር ግን ልጆቹን አልሠጣችሁም አለን። የፖለቲካ እስረኞች ናቸው ህጉ የሚፈታው አይደለም። ...እዚህ አገር ላይ ከፍርድ ቤትና ከህግ የሚበልጠው እላይ ያለው ደውሎ ልቀቅ የሚል ሰው ነው ይህ እኛ እንደተረዳነው የፖለቲካ ጉዳይ ነው። በሚዲያ ቀርቦ የምናገኘው ፍትህ የለም። ለውጥ የሚባል ነገር የሌለበት ሀገር ላይ ነው ያለነው። ፍትህን ከእግዚያብሄር ጠብቀን እንኖራለን። አሁንም ቢሆን የሲዳማ ህዝብ ልጆቹ ይለቀቃሉ ብሎ ጠብቆ ነበር። በቦታው የነበረው ሰው ሀላሌ ይፍታልን ብሎ ነው የሄደው። የሲዳማ ህዝብ ሲዳማ ብቻ ስለሆኑ የታሰሩ ልጆች ላይ የሚደረገውን ጭቆና አይቶ አሁንም ቢሆን መንግስት ፍትህን ይሰጣል ብሎ አይጠብቅም፤ አይጠይቅም። ከእግዚያብሄር ነው ፍትህን የሚጠብቀው ይህ ህዝብ"
#ቲክቫህ