TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.44K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ይበቃናል‼️

በየዕለቱ አዳዲስ አጀንዳዎችን እየፈጠሩ ወደ ለውጥ፣ ልማት፣ ሰላምና አንድነት የምናደርገውን ጉዞ #እያደናቀፉ ያሉ አካላት አሉ። እነዚህን ቀንደኛ የሀገር ጠላቶች እና የጥፋት ሀይሎች አምርረን #ልንታገላቸው ይገባናል።

በቃን! በቃን! በቃን! ለብዙ አመታት በጦርነት ተሰቃይተናል፣ ሰዎች ገብረናል፣ ችግር አይተናል፣ ረሀብ ተፈራርቆብናል፣ ድህነት መጠሪያችን ሆኗል፣ ስማችን በዓለም ተዋርዷል፣ የሌላ ሀገር መሬትን ተመኝተን ባህር ገብተን ሞተናል፣ የበረሀ ሲሳይ ሆነናል፣ እርስ በእርሳችን እየተጋጨን የድህነትን ኑሮ ገፍተናል ወገኖቼ አሁን ግን ይበቃናል!!

•ችግሩ ይበቃናል
•ጥላቻው ይበቃናል
•ተንኮሉ ይበቃናል
•ሞቱ ይበቃናል
•ረሀቡ ይበቃናል
•መፈናቀሉ ይበቃናል
•ለቅሶው ይበቃናል
•ለመኖር መስጋቱ ይበቃናል
•ወጥቶ ለመግባት #መፍራቱ ይበቃናል

ኑ ያለፈውን ትተን ለመጪው እንስራ። ኑ ታላቅ እንሁን። ለኛ እንኳን ባይሆን ለልጅ ልጆቻችን ስንል ጠንካራ ሀገር #ገንብተን እንለፍ። ምንም ባናወርስ #ፍቅሯ#አንድነቷ#ሰላሟ የተረጋገጠች ሀገር እናውርስ!

አመሰግናለሁ!
ፀጋአብ ወልዴ
@tsegabwolde @tikvahethiopia