TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ የቲክቫህ አባላት :

• ከC2 99 ተማሪዎች መካከል አብዛኞቹ ወደግቢ አልሄዱም።

• ከC1 ወደ 60 ተማሪዎች መካከል አብዛኞቹ ወደግቢ አልሄዱም።

ከዚህ ቀደም ደግመን ደጋግመን በሰላም ጉዳይ በሰራንባቸው ወቅቶች እንደገለፅነው የአንድ ቦታ ሰላም እጦት ጉዳቱ ለዛ አካባቢ ብቻ ሳይሆን ለሌላውም የሚተርፍ ነው።

ሰላም ማጣት እዛው ያለውን ህዝብ ብቻ ሳይሆን መላውን ሰላም ወዳድ ዜጋ የሚጎዳ ነው።

በተለይም ጦርነት በቦታው ላይ ያሉ እናቶች፣ህፃናት፣ ሴቶች፣ ተማሪዎች በእጅጉ ይጎዳል። በትግራይ ያየነውም ይኸው ነው።

በተለይ የተማሪዎች ጉዳይ አሳስቢ ነው። አንድም እዛው ትግራይ ያሉ እና በሌሎች ቦታዎች መማር ያለባቸው በሌላ በኩል ወደትግራይ ሄደው የሚማሩ ተማሪዎች የሚደርስባቸው ተፅእኖ ቀላል አይደለም።

ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ ሜዲስን ተማሪዎች የቲክቫህ አባልት ከሰሞኑን ወደዓዲግራት ሄደው ለመማር እንደሚቸገሩ ገልፀውልናል።

ዓዲግራት ተማሪዎቹን እንዲገቡ የጠራው ያለፈው ሚያዚያ 5 እስከ ሚያዚያ 7 ሲሆን የሜዲስን ተማሪዎች የኛ ጉዳይ ይለያል መፍትሄም ይፈልጋል ብለዋል።

ዓዲግራት በጦርነቱ ምክንያት ያላት የጤና ተቋሟ ከተጎዱባት የትግራይ ከተሞች አንዷ ናት።

በዚህ ምክንያት ተማሪዎቹ በቀራቸው ጊዜ በቂ የሆነ እና አስፈላጊውን ጥራት በጠበቀ መልኩ የጤና ትምህርታቸውን ተከታትለው ለመጨረስ እንደሚያስቸግራቸው ገልፀዋል።

የዓዲግራት ሆስፒታል ተኝነተው የሚታከሙ ህምምተኞችን እስተናገደ እንዳልሆነ መረጃው እንዳላቸው ገልፀው የእነሱ ትምህርት ደግሞ በቀጥታ ከዚህ ጋር የሚገናኝ መሆኑን ነው ያነሱት።

ያንቡቡ👇
https://telegra.ph/Tikvah-Family-Adigrat-04-21

#TikvahFamilyAdigrat

@tikvahethiopia
#ትግራይ

በትግራይ ክልል በነበረው ጦርነት ምክንያት የ2 ነጥብ 1 ቢሊዮን ብር የሚገመት የንብረት ውድመት እንደደረሰበት የገለጸልን የዓዲግራት ካቶሊካዊት ቤተክርስትያን ሃገረ ስብከት ተራድኦ ድርጅት ለ364 ሺህ 311 የጦርነት ተፈናቃዮች የድርቅና ረሃብ ተጠቂዎች እርዳት በማቅረብ ላይ እንደሚገኝ ገለፀ።

ከፓለቲካ ነፃ መሆኑ የሚጠቅሰው የካቶሊካዊት ቤተክርስትያን የተራድኦ ድርጅት በትግራይ ጦርነት ጊዜ ለሰብአዊ አገልግሎት ስራ ሲጠቅምባቸው  የነበሩ 14 መኪኖች መዘረፉ አስታውሶ ዘራፊዎቹ ለሰብአዊ አገልግሎት መኪኖቹ እንዲመልሱ " በፈጣሪ ስም እማፀናለሁ " ብሏል።

የምግባረ ሰናይ ድርጅቲ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ተወልደ ሃይለስላሴ ወደ ዓዲግራት ለተጓዘው የመቐለ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል በሰጡት ቃለመጠይቅ እንደገለፁት ፤ ምግባረ ሰናይ ድርጅቱ ባለፈው 2023 የፈረንጆች ዓመት ብቻ ከ433 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ ለ364 ሺህ 311 ህዝብ አስቸኳይ እርዳታ አቅርበዋል።

ከተረጂዎቹ 50 በመቶ በላይ ሴቶች መሆናቸው ያብራሩት ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ እገዛው በመላ ትግራይና ዓፋር ዞን 2 እንደተከናወነ አብራርተዋል።

ያንብቡ https://telegra.ph/Tikvah-Ethiopia-03-09

#TikvahFamilyAdigrat

@tikvahethiopia