TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የዘንድሮው ከፍተኛ ውጤት አስመዝጋቢ!

በባሕር ዳር #የአየለች_ደገፉ መታሰቢያ ትምህርት ቤት የ12ተኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና የወሰደው ብሩክ ዘውዱ 645 ውጤት በማስመዝገብ በኢትዮጵያ ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገበ ተፈታኝ ሆኗል፡፡ ከአብመድ ጋር ቆይታ ያደረገው ብሩክ ውጤቱ #እንደጠበቀው መምጣቱን ተናግሯል፡፡

ዓመቱን በሙሉ ለብሔራዊ ፈተና ዝግጅት እንዲረዳው በቤተ መጻሕፍት ገብቶ በማንበብ፣ በመምህራን በግል የሚሰጠውን የድጋፍ ትምህርት በመከታተል፣ ትምህርት ቤትም የተለያዩ ፈተናዎችን በመውሰድ መዘጋጀቱን ጠቁሟል፡፡

“ከቤተሰብ እናቴ ሙሉ ድጋፏን በማበርከት በራሴ መንገድ እንዳጠና ታበረታታኝ ነበር” ብሏል፡፡ ጥረቱ በከፍተኛ ውጤት መታጀቡ እንደስደሰተውም ተናግሯል፡፡

“ማትሪክ የጉብዝና መለኪያ አይደለም፤ ከእኔ የተሻሉ ብዙ ተማሪዎች ይኖራሉ፤ የሥራ መለኪያ ነው፤ በደንብ ተግቶ ሳይሰለች መሥራት ከተቻለ የሚፈለገው ውጤት ይመጣል፡፡ ተማሪዎች ሁሌም ዓላማቸውን መዘንጋት የለባቸውም” የብሩክ ምክረ ሐሳብ ነው፡፡

የትምህትር ቤቱ ባለቤት አትሌት ሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴ በስልክ በሰጠው አስተያዬት “ይህ ታዳጊ የ18 ወይም 19 ዓመት ሕልሜን አሳክቶታል፡፡

ታሪክ ነው የሠራው፤ #ኮርተንበታል፤ ተማሪዎችን በማስጠናት አርአያ ልጅ እንደሆነም ሰምቻለሁ፤ የብሩክ ተከታዮች 13 የሚሆኑ ተማሪዎችም ከ600 በላይ ውጤት አስመዝግበዋል፤ ብሩክ ሥርዓት ያለው ልጅም ነው፤ ከፍተኛ ውጤት እንደሚያመጣም እንጠብቅ ነበር” ብሏል፡፡ ለቤተሰቡ፣ #መምህራኖቹና ጓደኞቹም ጥሩ አርአያ እንደሚሆን ሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴ ተናግሯል፡፡

Via #AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia