#ETHIOPIA በሞሮኮ ራባት በሚካሄደው 12ኛው መላ አፍሪካ ጨዋታ የሚሳተፈው የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን አሸኛኘት ተደርጎለታል። ትናንት በአዲስ አበባ ሂልተን ሆቴል በተካሄደው የሽኝት መርሀ ግብር የኢፌዴሪ ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር ርስቱ ይርዳው፣ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝዳንት ሱፐር ኢንቴደንት ኮሎኔል ደራርቱ ቱሉ እንዲሁም ሌሎች የኮሚሽኑ እና የኦሎምፒክ ኮሚቴ የሥራ ኃላፊዎች ታድመዋል፡፡
የሥራ ኃላፊዎቹ ተሳታፊዎችን አበረታትተዋል፤ መልካም ምኞታቸውንም ገልጸውላቸዋል፡፡ የኢፌዴሪ ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር ርስቱ ይርዳው 12ኛው የመላ አፍሪካ ጨዋታ ከዚህ በፊት ከነበረው በተሻለ መልኩ ዝግጅት የተደረገበት መሆኑን ተናግረዋል፡፡ አትሌቶች የተሻለ የቴክኒክ፣ የታክቲክ እና ስነ ልቦና ዝግጅት ያደረጉበት፣ አሠልጣኞች በቂ ጊዜ ወስደው ሠልጣኞችን ለማብቃት እና ውጤታማ ለማድረግ ተግተው የሰሩበት፣ የስፖርት ተሳትፎውም የጨመረበት ነው ብለዋል ኮሚሽነር ርስቱ።
ስፖርተኞችም የወከሉት ሀገርን መሆኑን በማሰብ በጠንካራ የቡድን መንፈስ፣ በኢትዮጵያዊ ሥነ ምግባር እና ብቃት የተሻለ ውጤት እንዲያስመዘግቡ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡ በዚህም ኢትዮጵያ በአፍሪካ መድረክ ደምቃ እና ሰንደቋ ከፍ ብሎ እንዲታይ ሊያደርጉ እንደሚገባ ነው የመከሩት፡፡
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝዳንት ሱፐር ኢንቴደንት ኮሎኔል ደራርቱ ቱሉ ደግሞ ስፖርተኞቹ ሀገርን መወከል ምን ያህል ከባድ መሆኑን መገንዘብና ሕዝብ የሚጠብቀውን ውጤት ለማስመዝገብ መሥራት እንዳለባቸው ነው መልዕክት ያስተላለፈችው፡፡ በጥሩ ሥነ ምግባር እና ስፖርታዊ ጨዋነት ኢትዮጵያን ማስጠራትም እንዳይዘነጋ ብላለች ኮሎኔል ደራርቱ ቱሉ።
Via አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia

ምዕራባዊ ኤርትራ አንጃሃይ በተባለ አካባቢ በተከሰተው ሄሊኮፕተር አደጋ፣ የሞቱት አራት ሰዎች የቀብር ሥነ ስርዓት ተፈፅሟል፡፡ በአደጋው ከሞቱት መካከል አንዱ የፕሬዚዳንታዊ ጽሕፈት ቤት አባል ሲሆኑ ሦስቱ የኤርትራ የአየር ኃይል ባልደረቦች ናቸው፡፡ በአደጋው ህይወታቸው ያለፈው የኤርትራ ኃይል አባላት ካፒቴን ንጉሤ ናይግዚ፣ ምክትል መቶ አለቃ ሙሴ ገ/ሕይወት፣ ጀነራል ተወልደ መድኅን እስጢፋኖስና ሃምሳ አለቃ ሺሻይ ተስፋማርያም መሆኑን የመንግሥት የዜና ምንጮች ገልፀዋል፡፡
Via #VOA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Via #VOA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ኢትዮጵያ የዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ ላይ ትኩረት ሰጥታ እየሰራች እንደሆነ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶ/ር ኢንጂነር ጌታሁን መኩሪያ አስታወቁ፡፡
ሚኒስትሩ ይህንን ያስታወቁት በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶ/ር ኢንጂነር ጌታሁን መኩሪያ የተመራ የኢትዮጵያ የልኡካን ቡድን በቻይና በተዘጋጀላቸው የኢኮኖሚ አውደ ጥናት ላይ በተሳተፉበት ወቅት ነው፡፡
ሚኒስትሩ በቻይና ግዙፉ የባሉበት ነጋጅ (ኦን ላይን ግብይት ፈፃሚ) ከሆነው አሊባባ ቡድን ጃክ ማ ጋርም ተወያይተዋል፡፡ የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ ዲጂታላይዝ ለማድረግ በዘርፉ ልምድ ያለው አሊባባ ድጋፍ እንዲያደርግላቸው የጠየቁ ሲሆን የአሊባባ ቡድንም ልምዳቸውን ለኢትዮጵያ ለማካፈል ዝግጁ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡
ኢትዮጵያ የዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ ላይ ትኩረት ሰጥታ እየሰራች ነው ያሉት ዶ/ር ኢንጂ. ጌታሁን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድም ጉዳዩን ቀዳሚ አጀንዳቸው አድርገውታል ብለዋል፡፡ ከሚኒስቴሩ የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው ልኡካን ቡድኑ የአሊበባን ዋና ቢሮ ጎብኝቷል፡፡
@tsegabwolde @tikvajethiopia

#ETHIOPIA በአዲስ አበባ ግዮን ሆቴል አካባቢ ዛሬ ጠዋት በደረሰ የትራፊክ አደጋ ሰዎች ተጎዱ። አደጋው የደረሰው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ተሰራተኞች አውቶቡስና የአንበሳ የከተማ አውቶቡስ በመጋጨታቸው እንደሆነ የአይን እማኞች ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል። የአይን እማኞች እንደተናገሩትም የአየር መንገዱ አምቡላንስ በመዘግየቱ ምክንያት ግለሰቦች ተጎጅዎችን ይዘው ወደ በሆስፒታል ይዘው ሄደዋል። የአዲስ አበባ ፖሊስ በበኩሉ አደጋው በተሽከርካሪዎች ላይ ጉዳት ከማድረስ ባለፈ በሰዎች ላይ የከፋ ጉዳት አልደረሰም ብሏል።
Via ኢትዮ ኤፍ ኤም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Via ኢትዮ ኤፍ ኤም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የዘንድሮው ከፍተኛ ውጤት አስመዝጋቢ!
በባሕር ዳር #የአየለች_ደገፉ መታሰቢያ ትምህርት ቤት የ12ተኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና የወሰደው ብሩክ ዘውዱ 645 ውጤት በማስመዝገብ በኢትዮጵያ ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገበ ተፈታኝ ሆኗል፡፡ ከአብመድ ጋር ቆይታ ያደረገው ብሩክ ውጤቱ #እንደጠበቀው መምጣቱን ተናግሯል፡፡
ዓመቱን በሙሉ ለብሔራዊ ፈተና ዝግጅት እንዲረዳው በቤተ መጻሕፍት ገብቶ በማንበብ፣ በመምህራን በግል የሚሰጠውን የድጋፍ ትምህርት በመከታተል፣ ትምህርት ቤትም የተለያዩ ፈተናዎችን በመውሰድ መዘጋጀቱን ጠቁሟል፡፡
“ከቤተሰብ እናቴ ሙሉ ድጋፏን በማበርከት በራሴ መንገድ እንዳጠና ታበረታታኝ ነበር” ብሏል፡፡ ጥረቱ በከፍተኛ ውጤት መታጀቡ እንደስደሰተውም ተናግሯል፡፡
“ማትሪክ የጉብዝና መለኪያ አይደለም፤ ከእኔ የተሻሉ ብዙ ተማሪዎች ይኖራሉ፤ የሥራ መለኪያ ነው፤ በደንብ ተግቶ ሳይሰለች መሥራት ከተቻለ የሚፈለገው ውጤት ይመጣል፡፡ ተማሪዎች ሁሌም ዓላማቸውን መዘንጋት የለባቸውም” የብሩክ ምክረ ሐሳብ ነው፡፡
የትምህትር ቤቱ ባለቤት አትሌት ሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴ በስልክ በሰጠው አስተያዬት “ይህ ታዳጊ የ18 ወይም 19 ዓመት ሕልሜን አሳክቶታል፡፡
ታሪክ ነው የሠራው፤ #ኮርተንበታል፤ ተማሪዎችን በማስጠናት አርአያ ልጅ እንደሆነም ሰምቻለሁ፤ የብሩክ ተከታዮች 13 የሚሆኑ ተማሪዎችም ከ600 በላይ ውጤት አስመዝግበዋል፤ ብሩክ ሥርዓት ያለው ልጅም ነው፤ ከፍተኛ ውጤት እንደሚያመጣም እንጠብቅ ነበር” ብሏል፡፡ ለቤተሰቡ፣ #መምህራኖቹና ጓደኞቹም ጥሩ አርአያ እንደሚሆን ሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴ ተናግሯል፡፡
Via #AMMA

ከደቦ ፍርድ ለጥቂት ያመለጠው የኤሌክትሪክ ሰራተኛ!
በደቡብ ወሎ ዞን ጃማ ወረዳ በተሳሳተ መረጃ በመንጋ ውሳኔ ሊገደል የነበረው የመብራት ሃይል ሰራተኛ በፖሊስ ድጋፍ ህይወቱን ማትረፍ ተችሏል።
በዞኑ የጃማ ወረዳ ፖሊስ ፅህፈት ቤት ሃላፊ ኢንስፔክተር ተሾመ ለገሰ ለኢዜአ እንደገለፁት ትናንት ከሰዓት በኋላ አንድ የፌዴራል ኤሌክትሪክ ሃይል ሰራተኛ ከዓለም ከተማ ወደ ቃስታ የተዘረጋውን መስመር በማስተካከል ስራ ላይ ተሰማርቶ ነበር።
ሰራተኛው በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የተደገፈ መረጃ ለመሰብሰብና የተበላሹ መስመሮቹን ለማስተካከል የተሰማራ ቢሆንም የህፃናት ኩላሊት ለመስረቅ የመጣ ነው የሚል የተሳሳተ መረጃ በመናፈሱ ምክንያት የአካባቢውን ህዝብ ለደቦ ውሳኔ እንዲነሳሳ አድርጎታል።
በወረዳው የ017 ቀበሌ ህዝብ ተሰባስቦ ወንጀል ለመፈፀም ሲንቀሳቀስ የአካባቢው ፖሊስ በፍጥነት ደርሶ ህይወቱን እንዳተረፈው ኢንስፔክተሩ ገልፀዋል ።
ሰራተኛው በህይወት ተርፎ በፖሊስ ከለላስር ከዋላ በኋላም በጉልበት ነጥቀው ለመግደል የሞከሩ አምስት ሰዎች በቁጥጥርስር እንዲውሉ ተደርጓል።
ጥቂት ግለሰቦች በነዙት አሉባልታ ተነሳስቶ የሰው ህይወት ለመቅጠፍ መንቀሳቀስ ተገቢነት እንደሌለው የገለፁት ሃላፊው ሰራተኛው በማያውቀው ምክንያት ከመገደል የተረፈው ለጥቂት ነው ተብሏል። ህብረተሰቡ ለወደፊቱም ቢሆን በተሳሳተመረጃ ወደ ጥፋት በመግባት የህግ ጥሰት እንዳይፈጸም ዛሬ በደጎሎ ከተማ የምክክር መድረክ ተካሔዷል።
በመድረኩ ላይ ህብረተሰቡበተሳሳተመረጃ ተነሳስቶ ወደ ደቦፍርድ ከመግባት እንዲቆጠብ ትምህርት ተሰጥቷል። አጠራጣሪ ጉዳይ ቢያጋጥም እንኳን ለፀጥታ ሃይሎች መጠቆም እንጂ በሰላማዊ ዜጎች ላይ ወንጀል መፈፀም ከተጠያቂነት እንደማያድን በአፅንኦት ተነግሯል።
ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/DEBO-08-14

#update የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ከጃፓን ጠቅላይ ሚኒስትር ሺንዙ አቤ ልዩ መልዕከተኛ አምባሳደር ዮሺፉሚ ኦካሙራ እና ልዑካቸው ጋር ተወያዩ፡፡ ዛሬ ጠዋት በተደረገው በዚህ ውይይትም የሁለቱን ሀገራት ዘርፈ ብዙ ግንኙነት አሁን ካለበት ደረጃ በተሻለ ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መክረወል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ በአፍሪካ ሰላምን ለማረጋገጥ ኢትዮጵያና ጃፓን በጋራ መስራት በሚችሉበት ሁኔታ ላይ አተኩረው መወያየታቸውን ነው ከጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት የትዊተር ገፅ የተገኘው መረጃ የሚያመለክተው።
Via #EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Via #EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በምዕራብ ጉጂ ዞንና በደቡብ ክልል አራት ሰዎች ተገደሉ!
በምዕራብ ጉጂ ዞን #ገላና ወረዳና በደቡብ ክልል አማሮ ወረዳ፣ ባለፉት ሁለት ቀናት በደረሱ ጥቃቶች አራት ሰዎች እንደተገደሉ የወረዳዎቹ ባለሥልጣናት ተናገሩ፡፡ በጥቃቱ 5 ሰዎች መቁሰላቸውም ታውቋል።
Via #VOAAmharic
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በምዕራብ ጉጂ ዞን #ገላና ወረዳና በደቡብ ክልል አማሮ ወረዳ፣ ባለፉት ሁለት ቀናት በደረሱ ጥቃቶች አራት ሰዎች እንደተገደሉ የወረዳዎቹ ባለሥልጣናት ተናገሩ፡፡ በጥቃቱ 5 ሰዎች መቁሰላቸውም ታውቋል።
Via #VOAAmharic
@tsegabwolde @tikvahethiopia
“የኢትዮጵያ አየር መንገድ ባወጣው ጨረታ ማጭበርበር ፈጽሞብናል” ቅሬታ አቅራቢዎች
“ጨረታው ተበልቷል” የፌዴራል የመንግስት ግዥ ኤጀንሲ
“ጨረታው ግልጽ ስለሆነ የጨረታ መመሪያና ማብራሪያ አልሰጥም” አየር መንገዱ
“ጨረታውን ማሳገድ ይችላሉ”ፌዴራል ጠቅላይ አቃቢ ህግ
.
.
የኢትዮጵያ አየር መንገድ አዲስ ለሚያስገነባው ቁጥር ሁለት ተርሚናል ለተለያዩ የንግድ አገልግሎቶች የሚውሉ ክፍሎች ያወጣውን ጨረታ ማጭበርበሩና ጨረታውን መሰረዙ አግባብ ያለመሆኑን ቅሬታ አቅራቢዎች ገለጹ። አየር መንገዱ ‹‹ጨረታውን የሰረዝኩት በተቋሙ መመሪያና አሰራርመሰረት ነው፤ አሰራሬ ግልፅ ስለሆነም ስለጨረታው ማብራሪያም ሆነ የተቋሙን መመሪያ አልሰጥም›› ብሏል። የፌዴራል የመንግስት ግዥ ኤጀንሲ በበኩሉ “ጨረታው ተበልቷል ማለት ይቻላል›› ብሏል።
አየር መንገዱ ባወጣው ጨረታ የተሳተፉና የቴክኒክ መስፈርቱን ያሟሉ ስምንት ቅሬታ አቅራቢዎች ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ ባቀረቡት አቤቱታ ‹‹ተቋሙ ከአገሪቱና ከዓለም አቀፍ ህግ የጨረታ ስርዓት ውጪ ያፈነገጠ አሰራርን ፈፅሞ ስላጭበረበረን ጉዳት አድርሶብናል›› ብለዋል።
እንደ ቅሬታ አቅራቢዎቹ ማብራሪያ የጨረታው የመዝጊያና የመክፈቻ ጊዜ በግልጽ መነገር ሲገባው በሚጠበቀው ሰዓት አልተካሄደም፤ ጨረታውን ለማሸነፍ 40 በመቶ ነጥብ የሚይዘውን ቴክኒካል መወደዳሪያ ነጥብ በጊዜው በጽሁፍ አላሳወቀም፤ 60 በመቶ ነጥብ የሚይዘውን የቀረበውን የገንዘብ መጠን መወዳደሪያ ያሳወቀው ከረጅም ጊዜ በኋላ ነው።
ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/EP-08-14
ምንጭ፦ አዲስ ዘመን

ፎቶ📸የ12ኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎች በውጤታቸው ላይ ያላቸውን ቅሬታ ለማቅርብ በሀገር አቀፍ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ በር ላይ!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ፎቶ📸የ12ኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎች በውጤታቸው ላይ ያላቸውን ቅሬታ በሀገር አቀፍ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ በማቅረብ ላይ!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Dr. Tilaye...
"Congratulations to all Grade 12 students on your big academic achievement. As we are receiving complains on your Scholastic Aptitude Test result, #NEAEA will give it a second look and get back to you. Thank you for your patience. Wishing all the best!"

በአትሌት ሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴ ወጪ በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ፃግብጂ ወረዳ የሚገነባው ትምህርት ቤት ነሐሴ 17 ቀን 2011ዓ.ም እንደሚመረቅ ተነግሯል፡፡
Via #AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Via #AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ለ12ተኛ ክፍል ተማሪዎች በሙሉ፦
የዩንቨርስቲ መግቢያ /የ12ኛ ክፍል/ ፈተና ውጤት በትላንትናው ዕለት 7/12/2011 መለቀቁ ይታወሳል፡፡ ይህንንም ተከትሎ በዛሬው ዕለት በስኮላስቲክ አፕቲቲዩድ የፈተና ውጤት ላይ ከተማሪዎች፣ ከወላጆች እና ከመምህራን ስፋት ያለው ቅሬታ በመቅረቡ የማጣራት እርምጃ በመውሰድ ላይ የምንገኝ ሲሆን በአጭር ቀናት የማስተካከያ እርምጃ ወስደን ስለምንገልጽ እንደተለመደው በትዕግስት እንድትጠባበቁ እንጠይቃለን፡፡
ሀገር አቀፍ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ

በብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት የቀድሞ ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው የክስ መዝገብ ተካተው የተመሠረተባቸውን ክስ ከማረሚያ ቤት እየቀረቡ በመከታተል ላይ የሚገኙ ተከሳሾች ክስ የተመሠረተባቸው ወንጀል ሠርተው ሳይሆን፣ ታስረው በተፈለገባቸው ወንጀል መሆኑን አንድ ተከሳሽ ለፍርድ ቤት ተናገሩ፡፡
ተከሳሹ ለፍርድ ቤቱ የተናገሩት ዓቃቤ ሕግ ማክሰኞ ነሐሴ 7 ቀን 2011 ዓ.ም. ለስድስት ምስክሮች ስልክ በመደወል በዕለቱ ቀርበው እንደሚመሰክሩ የገለጸ ቢሆንም፣ አለመቅረባቸውን ለፍርድ ቤቱ በተናገረበት ጊዜ ነው፡፡
ተከሳሹ ፍርድ ቤቱን አስፈቅደው በሰጡት አስተያየት እንደገለጹት፣ ምስክርነት ከተጀመረ ጀምሮ ያለው ውጣ ውረድ ብዙ ነው፡፡ ከታሰሩ አንድ ዓመት እንደሆናቸውና የሠሩት ወንጀል ተጣርቶ መታሰር ሲገባቸው፣ ወንጀል የተፈለገባቸው ታስረው መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ያሰራቸውና የመረመራቸው ዓቃቤ ሕግ ሆኖ ሳለ፣ የማያውቃቸው ፖሊስ ምስክሮችን አፈላልጎ እንዲያቀርብ መደረጉ ተገቢ አለመሆኑን ገልጸዋል፡፡
ተጨማሪ የንብቡ👇
https://telegra.ph/ET-08-14

የትግራይና የአማራ አጎራባች ወረዳዎች የአሸንዳና አሸንድዬ በዓልን በጋራ ሊያከብሩ ነው!
የትግራይና የአማራ ክልል ዘጠኝ አጎራባች ወረዳዎች የአሸንዳ/አሸንድዬ በዓልን በጋራ ለማክበር ዝግጅት እየተደረገ ነው። የበዓሉ ዋናው ባለቤት የሆኑት ልጃገረዶች፣ የሚመለከታቸው አካላትና የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች በሰጡት አስተያየት በዓሉን በጋራ ማክበራቸው በሁለቱም ክልል ሀዝቦች ለዘመናት የቆየውን የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ይበልጥ እንዲጠናከር ለማድረግ ነው።
የትግራይ ማእከላዊ ዞን የቆላ ተምቤን ወረዳ ባህልና ቱሪዝም ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ንጉሰ አብርሃ እንደገለፁት ከትግራይ ክልል ማእከላዊ ዞን አራት ወረዳዎችና ከአማራ ክልል ዋግኽምራ አምስት ወረዳዎች የተወጣጡ ልጃገረዶችና ወጣት ሴቶች በጋራ በዓሉን በድምቀት ለማክበር ተዘጋጅተዋል።
በተምቤን ዓብይዓዲ ከተማ በጋራ የሚከበረው የአሸንዳ/አሸንድዬ በዓል በሁለቱም ክልሎች አጎራባች ወረዳዎች የሚገኙ ህዝቦች የበዓሉን ቱሩፋቶች ተጠቅመው በመካከላቸው የቆየውን ግንኙነት ለማጠናከር ፋይዳው የጎላ ነው። በአማራ ክልል የዋግኸምራ ዞን ባህልና ቱሪዝም መምሪያ ተወካይ አቶ ምስገናው መስፍን ለኢዜአ በስልክ በሰጡት አስተያየት የልጃገረዶች የነጻነት መገለጫ ተደርገው የሚታሰቡ የአሸንድዬና/አሸንዳ በዓላት በጋራ ለማክበር መነሳሳት መፈጠሩ ተገቢነት አለው ብለዋል።
ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/AT-08-14

#update የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በ2012 የትምህርት ዘመን በመንግስት ትምህርት ቤቶች ለሚማሩ ተማሪዎች የዩኒፎርምና የመማሪያ ቁሳቁስ ድጋፍ ለማድረግ የያዘውን እቅድ መሰረት በማድረግ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አመራሮችና አባለት ባወጡት ገንዘብ የተገዛ ከ49 ሺ በላይ ደብተሮች ፣ ከ 8ሺ በላይ ስክሪብቶዎች ፣ እርሳስ ፣ ላጲስና መቅረጫዎች በድምሩ 778 ሺ 262 ብር ዋጋ ያለቸውን የመማሪያ ቁሳቁስ ለአስተዳደሩ አስረክቧል፡፡
@tsegabwolde @tikvahethiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ናይጄሪያ
ፕሬዚዳንት ሙሃሙዱ ቡሃሪ ለናይጄሪያ ማዕከላዊ ባንክ በጻፉት መመሪያ የምግብ ምርቶችን ከውጭ ወደ ሀገሪቱ ለማስገባት የውጭ ገንዘቦች ምንዛሬ የሚጠይቁ ነጋዴዎች አገልግሎቱን እንዲከለከሉ ትዕዛዝ ሰጥተዋል። መመሪያው የተሰጠው የሀገር ውስጥ የግብርና ምርትን ለማበረታታት በማሰብ መሆኑ ነው የተሰማው።
Via #BBC

በአዲስ አበባ ከተማ በ2012 ዓ.ም ከ250 ሺ በላይ አዳዲስ የስራ ዕድሎች ለወጣቶች እንደሚፈጠሩ የከተማ አስተዳድሩ አስታወቀ። ኢ/ር ታከለ ኡማ በ2012 የስራ ዕድል ፈጠራ ዕቅድ ዙሪያ ከከተማ አስተዳደሩ ከተውጣጡ የባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት አካሂደዋል፡፡
@tsegabwplde @tikvahethiopia
@tsegabwplde @tikvahethiopia
ለ200ሺህ ዜጎች የስራ እድል የሚፈጥር ፕሮጀክት!
በአዲስ አበባ ከተማ ለሚገኙ 200 ሺህ ዜጎች የስራ እድል የሚፈጥር ፕሮጀክት ይፋ ሆኗል፡፡ ሊ ዌይ ፕሮግራም የተሰኘዉ ይህ ፕሮጀክት በአዲስ አበባ ያለዉን የስራ አጥነት ችግር ይቀንሳል ተብሎ ተስፋ ተጥሎበታል፡፡
የፕሮጀክቱ ዳይሬክተር አቶ ቴዎድሮስ የሺወርቅ እንዳስታወቁት፤ ፕሮግራሙ ለቀጣይ 5 አመታት የሚቆይ ሲሆን ሴቶች እና ወጣቶች ወደ ንግድ እንዲገቡ ያስችላል ብለዋል፡፡
በአዲሰ አበባ ከተማ አስተዳደር የማኅበራዊ ዘርፍ ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር እንዳወቅ አብጤ በበኩላቸዉ የፕሮጀክቱ ዋነኛ ተጠቃሚዎቹ ሴቶች እና ወጣቶች መሆናቸዉን ገልፀዉ በተለይም የማህበራዊ ችግር ተጋላጭ ለሆኑ ወገኖች ትኩረት እንደሚደረግባቸው ተናግረዋል።
ከዚህ በተጨማሪም የጎዳና ተዳዳሪዎችን በማንሳት የፕሮጀክቱ ተጠቃሚ እንዲሆኑ እንሰራለንም ብለዋል፡፡ አሁን ላይ ለሀገሪቱ አሳሳቢ የሆነዉን ስራ አጥነት ለመቀነስም ከመንግስት በተጨማሪ የግሉ ዘርፍም ሊረባረብ እንደሚገባም ተጠቁሟል፡፡
የሊ ዌይ ፕሮጀክት ለቀጣዮች 5 አመታት ተግባራዊ የሚሆን ሲሆን አሁን ላይ ከ2 ሺህ በላይ የሚሆኑ ዜጎችን ወደ ንግዱ ለማሳመራት 20 ሚሊዮን ዶላር መመደቡንም ተሰምቷል።
Via #ETHIOFM