TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.4K photos
1.47K videos
209 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
በትግራይ የኤርትራ ወታደሮች ጉዳይ ?

ከዚህ ቀደም በተደጋጋሚ የትግራይ ክልል የጊዜያዊ አስተዳደር ከፍተኛ አመራሮች በትግራይ ክልል ውስጥ የኤርትራ ወታደሮች ንብረት ዘርፈው ወደ ኤርትራ መውሰዳቸውን /ድንበር ተሻግረው ወደ ትግራይ ክልል ዘልቀው መግባታቸውን ሲገልፁ ነበር።

በቅርቡ እንኳን የትግራይ ክልል የኮንስትራክሽን ፣ መንገድ እና ትራንስፖርት ቢሮ በርካታ የኮንስትራክሽን ማሽኖች፣ ንብረቶች ወደ ጎረቤት ሀገር ኤርትራ መሸጋገራቸውን ገልፆ የተወሰዱትን ንብረቶች ለማስመለስም ከፌዴራል መንግስት ጋር ንግግር እንደሚደረግ ገልፆ ነበር።

የትግራይ ነዋሪዎችም በርካታ ጊዜያት በተዘጋጁ የውይይት መድረኮች ላይ የኤርትራ ሰራዊት ወደ ትግራይ መግባቱን በመግለፅ በአስቸኳይ የኢትዮጵያን ምድር ለቀው እንዲወጡ እንዲደረግ ሲጠይቁ ነበር።

በዛሬው ዕለት ደግሞ በትግራይ ክልል የሰሜናዊ ዞን ጊዜያዊ አስተዳደር ምክትል አስተዳደር ሙሉብርሃን ኃይሉ የኤርትራን ወታደራዊ መለዮ ለብሰው የህዝቡን ንብረት የሚዘርፉና ሴቶችን የሚደፍሩት "ህወሓት" የፈጠራቸው ወንበዴዎች ናቸው ብለዋል።

ምክትል አስተዳዳሪው ከኢዜአ ጋር በነበራቸው ቆይታ ፦

- በውጭ አገር ያሉ እና በእግራቸው ጫካ ለጫካ የሚኳትኑ ቀሪ የህወሓት አባላት በማህበራዊ ድረ-ገጾች የሀሰት ፕሮፖጋንዳ በመንዛት የትግራይን ህዝብ ለማታለል እየሞከሩ ነው ብለዋል።

- የክልሉን ወቅታዊ ሁኔታ በአካል ተገኝቶ መዘገብ ለሚፈልግ የመገናኛ ብዙሃን በሩ ክፍት ነው ብለዋል።

- "ህወሓት" በክልሉ የፈጠራቸውን ስራ አጥ ወጣቶች መሳሪያ በማስታጠቅ እና የኤርትራን ወታደራዊ መለዮ በማልበስ ሴቶችን እንዲደፍሩ በማድረግ በኤርትራ ወታደሮች ላይ ለማሳበብ ጥረት እየተደረገ ነው ብለዋል።

ተጨማሪ በ Instant View ያንብቡ።
https://telegra.ph/TigrayRegion-02-22
#TigrayRegion

በትግራይ ክልል 23,066 ዜጎች የኮቪድ-19 ክትባት መከተባቸውን የትግራይ ጤና ቢሮ ገልጿል።

ሁሉም ክትባቱን የወሰዱ ዜጎች በመቐለ ብቻ የሚገኙ እንደሆኑ ተነግሯል።

አሁን ላይ ወደሌሎች የትግራይ ከተሞች፦ ማይጨው ፣ ውቕሮ ፣ ዓዲግራት፣ ኣክሱም ክትባቱ እንዲሰጥ ለማድረግ ስራዎች እየተሰሩ ነው።

ክትባቱን ለማስጀመር አስፈላጊው ስልጠና የተሰጠ ሲሆን ክትባቱ ወደከተሞቹ ተልኳል።

ዓዲግራት፣ ወቕሮና ማይጨው ከሳምንት በፊት ክትባቱ ተልኮላቸው ክትባቱ መሰጠት ተጀምሯል።

አጭር መረጃ፦

- በትግራይ 5 ወር ያህል ተቋርጦ የነበረው የኮቪድ-19 ምርመራ ከሁለት ወር በፊት የጀመረ ሲሆን በቫይረሱ ተጠርጥረው ምርመራ ከተደረገላቸው መካከል 37% በቫይረሱ ተይዘው ተገኝተዋል።

- አስቀድሞ የሚሰሩት የኮቪድ-19 መከላከል ስራዎች የሉም።

- በተፈናቃይ ካምፖች የኮቪድ-19 ስርጭት እጅግ አሳሳቢ ነው። እንደምሳሌ፦ ሽረ ላይ ባለየተፈናቃይ መጠለያ በአንድ ክፍል ውስጥ እስከ 4 ቤተሰብ መሪ በተጨናነቀ ሁኔታ ይኖረል።

- ክትባት ከአንድ ወር በፊት ተጀምሮ በዝቅተኛ ደረጃ እየተሰጠ ነው።

- 119 ሺ ዶዝ የኮቪድ-19 ክትባት ትግራይ የተላከላት ሲሆን ከ23 ሺህ በላይ ጥቅም ላይ ውሏል።

- በጦርነት ምክንያት የኮቪድ-19 ጉዳይ ትኩረት በማጣቱ ፣ በህብረተሰቡ ዘንድ በክትባቱ ላይ ጥርጣሬ በመኖሩ ክትባቱ የተቀዛቀዘ ነበር ፥ የተከታቢ ቁጥር አነስተኛ ስለነበር የክትባቱ አገልግሎት ጊዜ ወደማብቃት ተጠግቷል፤ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን መነቃቃት እያሳየ ነው።

- ቅድሚያ 55ና በላይ እድሜ ያላቸው፣ እንዲሁም ተጓዳኝ ህመም ላለባቸው እየተሰጠ ሲሆን ከሚቀር ተብሎም ዕድሜያቸው 40 ለሆናቸውም እየተሰጠ ነው።

- በተፈናቃይ ካምፖች ክትባት መሰጠት አልተጀመረም። #ከዶቼቨለ

@tikvahethiopia
#WFP #UN #Ethiopia #TigrayRegion

ዛሬ የዓለም ምግብ ፕሮግራም ፤ አልሚ ምግብን ጨምሮ ህይወት አድን ፍጆታዎችን የጫኑ 47 ተሸከርካሪዎች ወደ ትግራይ ጉዞ መጀመራቸውን አሳውቋል።

ከ47ቱ ተሽከርካሪዎቹ በተጨማሪ ለመሰረታዊ አገልግሎቶች የሚውል ነዳጅ የጫኑ 3 ተሽከርካሪዎች ወደ ክልሉ በመጓዝ ላይ ይገኛሉ።

ከሁሉም ባለስልጣናት በተደረገው ድጋፍ እስካሁን ጉዞው የተሳካ እና መልካም የሚባል እንደሆነ ጠቁሟል።

ለሰብዓዊነት ተብሎ ግጭት የማቆም ውሳኔ ከተላለፈ በኃላ እስካሁን ድረስ ወደ 26 ተሸከርካሪዎች ብቻ ናቸው ወደ ክልሉ የገቡት።

የዓለም ምግብ ፕሮግራም በክልሉ በችግር ላይ የሚገኙ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎችን የሰብዓዊ ፍላጎት ለማሟላት በየዕለቱ 100 ተሽከርካሪዎች ወደ ክልል መግባታ እንዳለባቸው ከዚህ ቀደም መግለፁ ይታወሳል።

በሌላ መረጃ ፥ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ም/ቤት በ “any other business” ስር ዛሬ በኢትዮጵያ ስላለው ሁኔታ በዝግ ይመክራል።

በስብሰባው ላይ የሰብአዊ ጉዳዮች ም/ ዋና ጸሃፊ ማርቲን ግሪፍትስ ማብራሪያ ይሰጣሉ ተብሎ ይጠበቃል።

የዛሬውን ስብሰባውን የጠየቁት የA3 የምክር ቤቱ አባላት (ጋቦን፣ ጋና እና ኬንያ) ናቸው። #በA3 ብቻ በኢትዮጵያ ሁኔታ ላይ ስብሰባ ሲጠየቅ ይህ የመጀመሪያው መሆኑን ተመድን ዋቢ አድርጎ አል ዓይን አስነብቧል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update #Tigray, #Mekelle 📍 ትላንትና በጉዞ ላይ እንደነበሩ የተነገረላቸው አስፈላጊ የሆኑ የሰብዓዊ ድጋፍ አቅርቦቶችን የጫኑት የዓለም ምግብ ፕሮግራም ተሸከርካሪዎች የትግራይ ክልል መዲና መቐለ ደርሰዋል። ሁሉም (50ውም) ተሸከርካሪዎች በሰላም ነው መቐለ የደረሱት። ምን ይዘዋል ? ➡️ 1,000 ሜትሪክ ቶን ስንዴ እና ጥራጥሬ ፤ ➡️ 700 ሜትሪክ ቶን የጤና ፣ የተመጣጠነ ምግብ…
#WFP #USA #Ethiopia #TigrayRegion

የዓለም ምግብ ፕሮግራም (WFP) ወደ ትግራይ ክልል #ተጨማሪ ኮንቮይዎችን ለመላክ ዝግጁ መሆኑና ፍቃድም እንዳለው ገልጿል።

ቀጣዩ የሰብዓዊ እርደታ ኮንቮይ በተቻለ ፍጥነት በሰላም እንዲሄድ በአፋር ክልል ባለሥልጣናት ጋር በቅርበት እየሰራ መሆኑን ድርጅቱ ገልጿል።

በሌላ በኩል ፥ አሜሪካ ትላንት በውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤቷ በኩል ባወጣችው መግለጫ ፤ ከ1,700 ሜትሪክ ቶን በላይ ነፍስ አድን ሰብአዊ እርዳታ ትግራይ መግባቱ መልካም ዜና ነው ብላለች።

የእርዳታው እንዲደስ ትብብር ያደረጉትን የኢትዮጵያ መንግሥት፣ የትግራይ ክልል አስተዳዳሪዎች እና የአፋር ክልል አስተዳዳሪዎችን እንደምታደንቅም ገልፃለች።

በተጨማሪም ፤ አሜሪካ የትግራይ ኃይሎች ከአፋር ክልል ኤሬብቲ መውጣታቸውን እንደምትደግፍ ገልፃ ከሌሎችም የአፋር አካባቢዎች የትግራይ ኃይሎች ቢወጡ ጠቀሜታው የጎላ ነው ብላለች።

አሜሪካ በትላንት መግለጫዋ የኢትዮጵያ መንግስት እና የትግራይ ባለስልጣናት አሁን በታየው ለውጥ ቀጥለው ግጭቱን በድርድር፣ በዘላቂነት መፍታት የሚችሉበት መንገድ ማግኘት አለባቸው ብላለች።

ይህ እንዲሆንም በትግራይ ክልል መሠረታዊ አገልግሎቶች መመለስ እንዳለባቸው እና አካታች ፖለቲካዊ አካሄድ መተግበር እንዳለበት ገልጻለች።

የአሜሪካ መግለጫ : https://www.state.gov/delivery-of-humanitarian-assistance-in-tigray/

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Axum የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሰኔ 2016 ዓ/ም ወደ ትግራይ አክሱም ከተማ በረራ እንደሚጀመር መግለጹን ትግራይ ቴሌቪዥን ዘግቧል። የአክሱም ሃፀይ ዮውሃንስ አራተኛ አውሮፕላን ማረፍያ በትግራይ በነበረው ደም አፋሳሽ ጦርነት በደረሰበት ወድመት ምክንያት ከበረራ አገልግሎት ውጪ ሆኖ መቆየቱ ይታወሳል። በቅርቡ ግን አውሮፕላን ማረፊያው መልሶ አገልግሎት መስጠት እንደሚጀምር የኢትዮጵያ አየር መንገድ…
#Ethiopia

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በመጪው #ሰኔ_ወር 2016 ዓ/ም ወደ ሁለት የሀገር ውስጥ የበረራ መዳረሻዎች በረራ ይጀምራል።

አየር መንገዱ #ከሰኔ_10_ጀምሮ ወደ ወለጋ ፣ ነቀምቴ በረራ እንደሚጀምር አሳውቋል።

በረራው በሳምንት 4 ጊዜ እንደሚካሄድ ተገልጿል።

ከዚህም ባለፈ ፥ በትግራይ ጦርነት ምክንያት ተቋርጦ የቆየው ወደ አክሱም የሚደረገው በረራ ከሰኔ 1 ጀምሮ ዳግም እንደሚጀምር ታውቋል።

የአክሱም ሃፀይ ዮውሃንስ አራተኛ አውሮፕላን ማረፍያ በጦርነቱ በደረሰበት የከፋ ወድመት ምክንያት ከበረራ አገልግሎት ውጪ ሆኖ መቆየቱ ይታወሳል።

ከሰኔ 1 ጀምሮ ግን የመንገደኞች በረራ ያስተናግዳል ተብሎ ይጠበቃል።

#Ethiopia #OromiaRegion #TigrayRegion #Wollega #Axum
 
@tikvahethiopia
#Axum #Tigray

" በጦርነቱ ጊዜ እኮ #መከራው ከባድ ነበር !! "

ወ/ሮ በላይነሽ መኣሾ (የአክሱም ነዋሪ ለድምጺ ወያነ) ፦

" ሰላም በመሆኑ ጥሩ ነው ያለው።  ብርሃን አየን።

በሰላም እየተንቀሳቀስን ነው። #ሕጻናት እየተጫወቱ ነው።

ብዙ ለውጥ ነው ያለው።

በጦርነቱ ጊዜ እኮ #መከራው እጅግ ከባድ ነበር። አሁን በጣም በጣም ይሻላል ፤ ቢያንስ #እፎይ ብለን  መተኛት እንችላለን።

ቢሆንም ግን #የከፋው_ሰው_አለ ፤ ሰው የሚበላው የሚጠጣውን አጥቶ በጣም ከፍቶታል ፣ የመንግስት ሰራተኛውም ያለፉት ዓመታት ደመወዝ ባለመከፈሉ ለተለያዩ ችግሮች ተጋልጦ ነው ያለው ፣ የተፈናቃዮች ነገርማ #አይወራም ፣ ሕጻናት ልጆች የሚበሉትን አጥተው በየከተማው #በልመና ነው ተሰማርተው ያሉት። "

#Ethiopia #TigrayRegion #Peace

@tikvahethiopia
#TigrayRegion

" የሚሰራጨው ወሬ መሬት ላይ የሌለ ነው " - የምስራቃዊ ዞን አስተዳደር

በትግራይ ዛላኣንበሳና ኢሮብ የኢትዮ-ኤርትራ ደንበር ከቆየው የተለየ እንቅስቃሴ እንደሌለ የምስራቃዊ ዞን አስተዳደር አሳውቋል።

አሁንም ላለፉት 4 ዓመታት አከባቢ በኤርትራ ወታደሮች ቁጥጥር ስር የሚገኙ ስምንት የሚደርሱ የጉሎመኻዳና የኢሮብ ቀበሌ ገበሬ ማህበራት ላይ የታየ አዲስ ለውጥ እንደሌለ ተመላክቷል።

ከሰሞኑን አንዳንድ የማህበራዊ ሚዲያዎች " በትግራዩ ዛላኣንበሳ የኢትዮ-ኤርትራ ድንበር ከቆየው የተለየ እንቅስቃሴ አለ " ዘገባ ሲያሰራጩ ነበር።

የአከባቢው ነዋሪዎችና የትግራይ ምስራቃዊ ዞን አስተዳደር ግን ይህ ሀሰት ነው ሲሉ መልሰዋል።

ነዋሪች እና የዞኑ አስተዳደር " በዛላኣንበሳ የኢትዮ-ኤርትራ ድንበር ከቆየው የተለየ እንቅሰቃሴ የለም " ብለዋል።

የምስራቃዊ ዞን ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ፅህ/ቤት የጉሎመኻዳና ኢሮብ ወረዳ አስተዳደሮች ጠቅሶ ባሰራጨው መረጃ ፥ አከባቢዎቹ ከፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት በፊትም ሆነ በኋላ በኤርትራ መንግስት ቁጥጥር ስር እንደሚገኙ ገልጿል።

" ሉኣላዊ ግዛት ያለመከበር ጉዳይ እንዳለ ሆኖ ባላፉት ቀናት በአከባቢው አዲስ ወታደራዊ እንቅሰቃሴ የለም " ብሏል። 

" በተለያዩ የዜና ማሰራጫዎች በዛላኣንበሳና በኢሮብ አከባቢ ከኤርትራ መንግስት በኩል የተለየ እንቅሰቃሴ እንዳለ ተደርጎ የሚሰራጨው ወሬ መሬት ላይ የሌለና የአከባቢው ነዋሪዎች ይሁንታ ያለገኘ ነው " ሲል አክሏል።

አስከ አሁን ድረስ ዛላኣንበሳ ከተማ ጨምሮ 5 የጉሎመኸዳ ወረዳ የገጠር ቀበሌዎች እንዲሁም ከኢሮብ ወረዳ 4 የገጠር ቀበሌዎች  በኤርትራ ወታደሮች ቁጥጥር ስር እንደሚገኙ ፅ/ ቤት አስታውሷል።

ዞኑ " በሬ ወለደ ወሬ የሚናፍሱ ሚድያዎችና የማህበራዊ ትስስር ገፅ ፀሃፊያን ከድርጊታቸው እንደዲታቀቡ እናሳስባለን " ሲል አስጠንቅቋል።

በቅርብ እና በረቁ የሚገኙ የዓጋመና አከባቢዋ ተወላጆችና ወዳጆች በየዓመቱ በትግራይ ደረጃ በዓዲግራት ከተማ የሚከበረው የመስቀል በዓል ለማከበር እንዲታደሙ ጥሪ በማቅረብ አስተማማኝ የፀጥታ ሁኔታ እንዳለ አመልክቷል።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia 
#ወጣቶቻችን😥

" ከአንድ ወረዳ ብቻ ከ2 ሺህ በላይ ወጣቶች በህገ-ወጥ መንገድ ተሰደው 200 ያህሉ ለህልፈት ተዳርገዋል " - የእገላ ወረዳ አስተዳደር

እገላ ከትግራይ ማእከላዊ ዞን ወረዳዎች አንድዋ ስትሆን የኤርትራዋ ፆሮና ጎረቤት ናት።

ከትግራዩ ጦርነቱ በፊት የወረዳዋ ዋና ከተማ በሆነችው ገርሁስርናይ በቀን በርካታ የኤርትራ ስደተኞች በህገወጥ መንገድ ወደ ኢትዮጵያ ትግራይ ክልል የሚተላለፉባት ነበረች።

ከጦርነቱ በኋላ በእገላ ወረዳ በተለይ በገርሁስርናይ ከተማ ብዙ ነገሮች ተቀያይረዋል።

ወረዳዋ በተለይ ከተማዋ በከፍተኛ ሁኔታ ወድመዋል።

አሁንም ድረስ ወረዳዋ በኤትርራ ድንበር የምትገኝ በመሆንዋ የተሟላ ፀጥታ አላት ለማለት ያስቸግራል ይላሉ የአከባቢው ነዋሪዎች።

በወረዳዋ የሚታየው ህገ-ወጥ ስደት እጅግ አስደንጋጭና አስፈሪ መሆኑ የአደጋው ሰለባዎች እና የመንግስት አካላት ጭምር ይናገራሉ።

አቶ ዘርኢሰናይ መንግስቱ የተባሉ የገርሁስርናይ ከተማ ነዋሪ ለትግራይ የመገናኛ ብዙሃን ኤጀንሲ ሬድዮ ባጋሩት መረጃ የህዝብ ማመላለሻ መኪና ሹፌር በመሆን ሲተዳደር የነበረው የ22 ወጣት ልጃቸው ህገ-ወጥ ስደት ተነጥቀዋል።

ከእገላ ወረዳ አስተዳደር የተገኘው መረጃ እንደሚያሳየው ባለፈው 2016 ዓ/ም የመጨረሻ ወራት ብቻ 192 ሴቶች የሚገኙባቸው ከ 2 ሺህ በላይ  ወጣቶች በህገ-ወጥ መንገድ ተሰደው ከ1300 በላይ በስደት በተጓዙበት አገር ፓሊስ በአጭር ጊዜ ተይዘው ሲመለሱ 200 የሚያህሉ ግን ለህልፈት ተዳርገዋል።

የወረዳው ከፍተኛ አመራር ፅጌ ተ/ማርያም እንዳሉት፤ በአከባቢው የሚታየው ህገ-ወጥ የስደት ፍልሰት እጅግ አስፈሪና አስደንጋጭ ነው።

ወረዳው ከጦርነቱ ጋር በተያያዘ ይህ ነው የሚባል በጀት ያለው ባይሆንም የወጣቶች ስደት ለማስቀረት ያለመ የመስሪያ ቦታ በመስጠት ላይ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

በተያዘው የበጀት ዓመት የህገ-ወጥ ስደት ፍልሰት በከፍተኛ ቁጥር ለመቀነስ ወረዳው አቅዶ እየሰራ ነው።

ይሁን እንጂ ጦርነት ወለዱ የበጀት እጥረት ለተያዘው እቅድ መሳካት ሳንካ ሊሆን ስለሚችል በወጣቶች አቅም ግንባታ እና ህገ-ወጥ ስደት መከላከል ዙሪያ የሚሰሩ ምግባረ ሰናይ ድርጅቶች እንዲያግዙዋቸው ሃላፊው ጥሪ አቅርባዋል።

#Ethiopia #TigrayRegion

@tikvahethiopia