TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.8K photos
1.49K videos
211 files
4.06K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ፎቶ፦ ድምፃዊ #ዳዲ_ገላን #BBC
ዳዲ #በጥይት_ተመቶ ህይወቱ አለፈ‼️
.
.
ፖለቲካዊ ይዘት ያላቸውን ሙዚቃዎችን በመጫወት የሚታወቀውና በዘፈኖቹ በተደጋጋሚ ለእስር ተዳርጎ የነበረው የኦሮምኛ ዘፋኝ #ዳዲ_ገላን ሰኞ እለት ሙዚቃዎቹን ባቀረበበት መድረክ በጥይት #ተመትቶ ሞቷል።

በምስራቅ ሸዋ በቢሾፍቱ አቅራቢያ በምትገኘው የሊበን ዝቋላ ወረዳዋ ትንሿ የገጠር ከተማ አሹፌ ካለፈው ቅዳሜ እስከ ሰኞ ምሽት ደስታና ጭፈራ ነበር። ይጨፈር የነበረው ለአንድ ሆቴል ምርቃት ነበር። ደስታና ጭፈራው ግን አልዘለቀም።

የምርቃቱ ታዳሚዎች በደስታ ጥይት ወደላይ ይተኩሱ ነበር። የመድረኩ ፈርጥ የነበረው ታዋቂው ኦሮምኛ ዘፋኝ ዳዲ ገላን ድንገት በጥይት ተመትቶ እንደወደቀ የሆቴል ምርቃቱ የሙዚቃ ድግስ መድረክ አስተባባሪ የነበረው ጓደኛው አቶ ቱፋ ወዳጆ ይናገራል።

"ለቅሶም ላይም ይተኮሳል። ልጅም፣ አባትም ክላሽ መታጠቅ ባህል ነው። በወቅቱ እየተተኮሰ እያለ ማን እንደሆነ አይታወቅም ከመሀል ልቡን መትቶት ወደቀ" በማለት ይገልፃል።

በህግ የተከለከለ ቢሆንም በተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች ለሰርግ፣ ለሃዘን፣ ለልደትና ለሌሎችም መሰል አጋጣሚዎች ጥይት መተኮስ የተለመደ ነው ማለት ይቻላል።

በሃይማኖት አባቶችና በገዳዎች ምክር ጭምር ጥይት መተኮስ ቀርቶ የነበረ ቢሆንም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እንደ አዲስ እንደተጀመረ ዘፋኙ ህይወቱን ያጣበት የሊበን ዝቋላ ወረዳ ፖሊስ ፅፈት ቤት ሃላፊ ምክትል ኢንስፔክተር #ግርማ_ሚደቅሳ ለቢቢሲ ገልፀዋል።

ከ2009 ዓ.ም የለውጡን እንቅስቃሴ ተከትሎ በተለያዩ በዓላትና አከባበሮች ላይ ደስታንም ሆነ ኃዘንን ለመግለፅ መተኮስ እንደተጀመረ ኢንስፔክተር ግርማ በተጨማሪ ገልፀዋል።

ባለፈው አመትም አቅራቢያው በሚገኝ ሌላ አካባቢ አንድ ወጣት የደስደስ ጥይት ሲተኩስ ጓደኛውን በመግደሉ መልሶ ራሱን እንዳጠፋ ኢንስፔክተር ግርማ ያስታውሳሉ።

ኦሮምኛ ሙዚቃዎችን የሚጫወተው ዳዲ አስከሬን ለምርመራ ተልኮ ከነበረበት ጳውሎስ ሆስፒታል ዛሬ ከሰዓት በኋላ የትውልድ ቀዬው አሹፌ መድረሱን ኢንስፔክተሩ ገልፀዋል።

ምንጭ፦ BBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia