TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.8K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ሰበር መረጃ📌አዲስ አበባ የሚገኘው የዩናይትድ ስቴትስ ኤምባሲ ነገ፣ መስከረም 9/2018 ዓ.ም. #ዝግ እንደሚሆን አስታውቋል።

ኤምባሲው ለነገ አገልግሎቱን የሚያቋርጠው በከተማዪቱ ውስጥ በሚካሄደው “ግዙፍ ሊሆን ይችላል” ባለው #ሰልፍ ምክንያት የተጠናከረ ጥንቃቄ ለመውሰድ ሲባል መሆኑን ገልጿል።

ቀደም ሲል ተይዘው የነበሩ የቪዛ ቀጠሮዎችና ኤምባሲው ለአሜሪካዊያን ዜጎች ለሚሰጣቸው አገልግሎቶች ለነገ መስከረም 9/2018 ዓ.ም /19 September 2018/ ተቀጥረው የነበሩ ጉዳዮች በሙሉ የተሠረዙ መሆናቸውን አስታውቋል።

አሜሪካዊያን በኤምባሲው ዌብሳይት አማካይነት አዲስ ቀጠሮ እንዲይዙ መክሯል።

ከኢሚግራንት ቪዛ ጠያቂዎች ጋር ተለዋጭ ቀጠሮ ለማድረግ ኤምባሲው በቅርቡ የሚያገኛቸው መሆኑንና ነን-ኢሚግራንት ቪዛ ለማግኘት ያመለከቱ ደግሞ በኤምባሲው ዌብሳይት ላይ አዲስ ቀጠሮ እንዲጠይቁ አሳስቧል።

አጣዳፊ አገልግሎት የሚፈልጉ አሜሪካዊያን ዩናይትድ ስቴትስ ኤምባሲ ዌብሳይት ላይ ያለውን የአድራሻ/የመገናኛ መረጃ እንዲያዩ መክሯል።

ከኤምባሲው መደበኛ አገልግሎቶች በተጨማሪ አዲስ አበባ ውስጥ የሚገኘው የአሜሪካ ማዕከል እና ዩናይትድ ስቴትስ ኤምባሲ ውስጥ የሚገኘው ሳችሞ ማዕከልም ነገ ዝግ ሆነው እንደሚውሉ አስታውቋል።

በሰልፉ ላይ #የሚሣተፉ ሁሉ ሃሣቦቻቸውንና ፍላጎቶቻቸውን በሰላማዊ መንገድ መግለፃቸውን እንደሚያበረታታም ኤምባሲው ገልጿል።

©VOA 24(የአማርኛው አገልግሎት)
@tsegabwolde @tikvahethiopia