TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.9K photos
1.49K videos
211 files
4.07K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ጥቆማ‼️

"ጠዋት #ከአዲስ_አበባ ተነስቶ መድረሻውን #ድሬዳዋ ያደረገው ባቡር በመጀመሪያ መንገድ #ተዘጋ ተብለን 7:30 እስከ 11 ሰአት ድረስ ቆምን ከዛ 11:45ሲሆን ጉዞ ጀመርን እደገና 1:00 ሲል #የረር ስንደርስ #ግመል_ገጨ ተብሎ እስካሁን ቆመናል። ብዙ ህፃናት በረሀብ እያለቀሱ ነው። እደምናድር ወይም እደምንሄድ የደረሰን መረጃ የለም ማንም #አያናግርንም። አንድ የ4ወር ህፃን እራሱን ስቷል! መረጃው ለሚመለከተው አካል ይድረስ!"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሰበር ዜና‼️

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ንብረት የሆነ ቦይንግ 737 አውሮፕላን ዛሬ ጠዋት #ከአዲስ_አበባ ተነስቶ ወደ ኬንያ #ናይሮቢ ሲበር #ተከስክሶ የሰው ህይወት አልፏል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከወሊሶ🔝

"በወሊሶ ከተማ እየተካሄደ ባለው #ሰልፍ ምክንያት መንገድ ተዘግቶ ቆመናል። #ከአዲስ_አበባ እና #ከወልቂጤ ሚመጣ መኪና #ማለፍ አልቻለም።"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
መንገዱ ተከፍቷል...

ለ2 ቀናት ተዘግቶ የነበረው #ከአዲስ_አበባ ወደ #ወሊሶ የሚወስደው መንገድ ተከፍቶ አግልግሎት ጀምሯል።

Via ናቲ(TIKVAH-ETH)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አዲስ አበባ 🛫 መቐለ !

#ከአዲስ_አበባ ወደ #መቐለ ከነገ ጀምሮ ዳግም በረራ እንደሚጀምር የኢትዮጵያ አየር መንገድ አስታውቋል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው ዛሬ በሰጡት መግለጫ ፥ " ተቋርጦ የነበረው ከአዲስ አበባ ወደ መቐለ የአየር ትራንስፖርት በነገው ዕለት ይጀምራል " ብለዋል።

" በፌዴራል መንግስቱ እና በህወሓት መካከል የተደረገውን የሰላም ስምምነት ተከትሎ የአቬየሽን ሰራተኞች ወደ መቐለ አቅንተው የመቐለ አየር መንገድ ለበረራ ምቹ ሁኔታ ላይ መሆኑን አረጋግጠዋል " ሲሉ አቶ መስፍን ገልፀዋል።

ነገ በሚጀምረው በረራ በቀን አንድ ጊዜ የሚካሄድ መሆኑ የተጠቀሰ ሲሆን የደንበኞችን ፍላጎትን መሰረት በማድረግ የበረራው ቁጥሩ ከፍ ሊል የሚችልበትን ሁኔታ እንደሚፈጠርም አሳውቀዋል።

ዋና ስራ አስፈፃሚው ፤ ተቋርጦ የነበረውን የበረራ እንቅስቃሴ #በሁሉም የትግራይ ክልል የበረራ መዳረሻዎች ለማስጀመር ስራዎች እየተሰሩ እንደሆነም ዛሬ በሰጡት መግለጫ አንስተዋል፡፡

" ነገ የሚጀምረው በረራ (ወደ መቐለ) ከሌላው ወገኑ ጋር ግንኙነቱ ተቋርጦ የነበረውን የትግራይ ህዝብ ዳግም እንዲገናኝ ለማድረግ ትልቅ እድል የሚፈጥር " ነው ሲሉ ተናግረዋል።

ከዚህ ባለፈ የሸቀጦችና ሌሎች ተደራሽ የመሆን እጥረት የነበረባቸውን የሰብዓዊ ድጋፎችን በበቂ ተደራሽ ለማድረግ ትልቅ አስተዋጽኦ ያለው መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

ይህም ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታውን ከፍ ማድረግ የሚያስችል እንቅስቃሴ መሆኑንም ዋና ስራ አስፈፃሚው ገልፀዋል፡፡

#የኢትዮጵያ_አየር_መንገድ #ኤፍቢሲ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" ወጣቶች እንዳይንቀሳቀሱ የማድረግ ዓላማ የለንም " - የትግራይ ክልል የኮንስትራክሽን ፣ መንገድና ትራንስፖርት ቢሮ " የኢትዮጵያ መንግስት ሆነ የትግራይ ክልል ወጣቶች  #እንዳይንቀሳቀሱ_የማድረግ_አላማ_የላቸውም " ሲል የትግራይ ክልል የኮንስትራክሽን ፣ መንገድና ትራንስፖርት ቢሮ አስታውቀ። ቢሮው ለክልሉ ቴሌቪዥን በሰጠው ቃል የኢትዮጵያ አየር መንገድ በቀን እስከ 4 ጊዜ በረራ በማድረግ አገልግሎት…
#EthiopianAirlines

የኢትዮጵያ አየር መንገድ #ከመቐለ በረራ ጋር በተያያዘ መግለጫ አውጥቶ ነበር።

ምን አለ ?

- ወደ መቐለ በረራ ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ ከአዲስ አበባ ወደ መቐለ እና ከመቐለ ወደ አዲስ አበባ የሚጓዙ መንገደኞችን እያገለገለ መሆኑን ገልጿል።

- አየር መንገዱ ቲኬት ገዝተው ወደ ቼክኢን ካውንተር የሚመጡ ተጓዦችን በአግባቡ እያስተናገደ መሆኑን አመልክቷል።

- የመቐለ በረራ በቀን አንድ ጊዜ የነበረ ሲሆን አሁን በየእለቱ የሚደረገው በረራ ወደ ሶስት ከፍ ማለቱን አሳውቋል።

- እለታዊ የበረራ ብዛት ቀንሷል የሚለው የተሳሳተ መረጃ ነው ብሏል፡፡ ወደፊትም የሚኖረውን የበረራ ፍላጎት እየታየ የበረራውን ብዛት ለመጨመር ዝግጁ መሆኑን ገልጿል።

- #ከአዲስ_አበባ  ወደ  #መቐለ የሚጓዙ መንገደኞች የአየር መንገዱን የጥሪ ማእከል እና ቲኬት ቢሮዎች በመጠቀም ቲኬት መግዛት የሚችሉ ሲሆን ከመቐለ የሚነሱ ተጓዦች ደግሞ ከመቐለ የአውሮፕላ ማረፊያ የሽያጭ ቢሮ ቲኬቱን መግዛት ይችላሉ፡፡

በተጨማሪ ፦

የበረራ ቲኬቱን አ/አበባ በሚኖሩ ወዳጅ ዘመዶቻቸው በኩል መግዛት የሚፈልጉ ደግሞ ቦሌ በሚገኘው " የኢትዮጵያ ኤርፖርት ኢንተርፕራይዝ ህንጻ " የምድር ወለል ከሚገኘው የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሽያጭ ቢሮ ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 2፡00 ሰአት እስከ ከሰአቱ 11፡00 ሰአት ድረስ መግዛት ይችላሉ ብሏል።

- አየር መንገዱ ባለፉት ስምንት ወራት የመቐለ በረራን ጨምሮ በሌሎች የሃገር ውስጥ በረራዎች ቲኬት ዋጋ ላይ ጭማሪ እንዳላደረገ ገልጿል።

- የኢትዮጵያ ዜግነት ላላቸው ተጓዦች እና የኢትዮጵያ የመኖሪያ ፈቃድ ላላቸው የውጭ ሃገር ዜጎች የመቐለ በረራ የቲኬት ዋጋ ለመሄጃ ብቻ ከ3450 ብር ጀምሮ ሲሆን፣ የደርሶ መልስ ቲኬት መነሻ ዋጋ ደግሞ 6895 ብር ነው፡፡ 

- " ሻንጣን " በተመለከተ #ከገና_በዓል ጋር ተያይዞ የተጓዦች ቁጥር በከፍተኛ ደረጃ በመጨመሩ የሻንጣ አገልግሎት ላይ መለስተኛ መጨናነቅ ተፈጥሯል።  በዚህም ምክንያት አየር መንገዱ ተጨማሪ (ትርፍ) ሻንጣዎችን ለመቀበል ተቸግሮ ቆይቷል፡፡ አሁን ግን የካርጎ በረራ በመመደብ ችግሩን መፍታት ስለተቻለ ተጨማሪ ሻንጣ መቀበል ጀምሯል፡፡

Credit : Ethiopian Airlines

@tikvahethiopia
“ሹፌሩን፣ ጋቢና የነበሩ 2 ሰዎችን ጭንቅላታቸውን በሰደፍ መቷቸው። በገመድ አስረው፣ አፋቸውን በፕላስተር አስይዘው መኪናውን ይዘው ሄዱ ” - የተሽከርካሪው ባለቤት

“ እንዲህ አይነት ወንጀሎች ከዕለት ዕለት እየጨመሩ ነው ” - የከባድ መኪና አሽከርካሪዎች ማኀበር

#ከአዲስ_አበባ ተነስቶ ወደ #ወላይታ_ሶዶ 70 ኩንታል ዱቄት ጭኖ ሲጓዝ የነበረ ተሽከርካሪ በሻሸመኔ እና ሀዋሳ መካከል ከቶጋ ካምፕ አለፍ ብሎ ቢሻን ጉራቻ (ጥቁር ውሃ) መግቢያ ላይ በሚገኝ ቦታ ማክሰኞ መጋቢት 3 ቀን 2016 ዓ/ም ከምሽቱ 3 ሰዓት ገደማ ላይ በታጠቁ ኃይሎች እንደተወሰደና እንዳልተመለሰላቸው የተሽከርካሪው ባለቤት፣ ሌላ እማኝና የከባድ መኪና አሽከርካሪዎች ማኀበር ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።

የተሽከርካሪው ባለቤት በሰጡት ቃል፣ “ ሹፌሩን፣ ጋቢና የነበሩ 2 ሰዎችን ጭንቅላታቸውን በሰደፍ መቷቸው። በገመድ አስረው፣ አፋቸውን በፕላስተር አስይዘው መኪናውን ይዘው ሄዱ ” ሲሉ ገልጸዋል።

እንዲህ ያደረጉ አካላት ማን እንደሆኑ ሲያስረዱ ፣ “ ደብል ጋቢና በሆነ መኪና (አሮጌ ነገር ነው) እርሱ ላይ ሰዎች ነበሩ፣ 3 ክላሽ 1 ሽጉጥ የያዙ። ‘ኬላ ጥሳችሁ ነው የመጣችሁት አሉ’። ኬላ አልጣስንም ያው ደረሰኙ ቢላቸውም ‘አይ ውረድ ውረድ’ ብለው ሹፌሩን በሰደፍ መቱት ጭንቅላቱ ላይ፣ ጋቢና ላይ የነበሩ ሁለት ሰዎችንም አስወረዱ እነርሱንም ጭንቅላታቸውን በሰደፍ መቷቸው ” ነው ያሉት።

በገመድ አስረው ፣ አፋቸውንም በፕላስተር አስይዘው እንደነበር በኃላም አላሙዲን እርሻ ፊት ለፊት ባለው አቅጣጫ መኪናውን ይዘው እንደሄዱ ተናግረዋል።

የተሽከርካሪው ባለቤት ፤ በሰደፍ ተመቱ የተባሉት ሰዎች ቢለቀቁም ቁስሉ እንዳልተሻላቸው ገልጸዋል።

“ ዱቄቱ 70 ኩንታል ነው። 210 ሺሕ ብር ይገመታል። መኪናው  አዲስ ነው 2022 ሞዴል ቢ 24 ነው። መኪናውን ይመልሱልኝ ” ሲሉ የመኪናው ባለቤት ተማጽነዋል።

ሌላኛው ቃላቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የሰጡ አካል በበኩላቸው፣ “ ሹፌሩንና ረዳቱን ደበደቡ። የኤሌክትሪክ ፓል ጋ ሹፌሩን አሰሩ። ከዚያ መኪናውን ይዘው ሄዱ። እስከዛሬ ፋይዳ የለም ” ሲሉ አረጋግጠዋል።

ተፈፀመ የተባለውን ድርጊት አስመልክቶ ምላሽ እንዲሰጥ ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጥያቄ የቀረበለት ጣና የከባድ መኪና አሽከርካሪዎች ማኀበር ቡኩሉ ፣  70 ኩንታል ዱቄት ጭኖ የነበረው ተሽከርካሪ በሻሸመኔ ቢሻን ጉራቻ (ጥቁር ውሃ) መግቢያ ላይ እንዲቆም ተደርጎ እንደተወሰደ፣ ሰዎቹ ተደብደብዋል መባሉም እውነት ነው እንደሆነ ገልጿል።

አንድ የማኀበሩ ኃላፊ ፤ ሌላም እዚህም ኃይሌ ጋርመንት አካባቢ ከድሬዳዋ ዘይት ጭኖ የቆመ መኪና ሰሞኑን ጠፍቶ እንደነበር፣ መጨረሻም ጭነቱ ተራግፎ ቆሞ እንደተገኘ አስታውሰው፣ " ትክክል ነው የሻሸመኔውም። እንዲህ አይነት ወንጀሎች ከዕለት ዕለት እየጨመሩ ነው " ብለዋል።

" ምክያቱም በአሽከርካሪዎችና በተሽከርካሪዎች ላይ የሚደርስን ወንጀል በወንጀልነት ቆጥሮ በጸጥታ አካል አድኖ የመያዝ ሂደት አናሳ ሆኗል። አይደለም እቃውን የሰውን ሕይወት መጥፋትም በተለይ በመንግሥት ሚዲያዎች ሲዘገብ አናይም " ሲሉ አክለዋል።

" እገታና ዝርፊያ በጣም ተበራክቷል። " ያሉት እኚህ ኃላፊ " ሜዳ ላይ አስቁመው ደብድበው የሚፈልጉትን ይዘው ነው የሚሄዱት " ሲሉ የሁኔታውን አስከፊነት አስረድተዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ለጉዳዩ ምላሽ ለማግኘት ወደ ሻሸመኔ ከተማ ፓሊስ ያደረገው ሙከራ ለጊዜው አልተሳካም። #TikvahFamilyAddisAbaba

@tikvahethiopia