TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.8K photos
1.49K videos
211 files
4.07K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ኢሬቻ2011 እንኳን ለ2011 የኢሬቻ በአል በሰላም በፍቅርና በጤና አደረሳችሁ፤ አደረሰን!
Baga Ayyaana Irreechaa 2011'n isiin ga'e baga geessan.

#ኢትዮጵያዊነት ይለምልም!
#ኢሬቻ የኔም ነው!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ነቀምት‼️

በነቀምቴ የዘንድሮ #ኢሬቻ በዓል አከባበር በአገሪቱ የዲሞኪራሲ ሥርአት ግንባታው እያበበ ስለመምጣቱ የታየበት ነው ሲሉ አባ ገዳዎች ገለፁ።

በነቀምቴ ሀዲያ የኢሬቻ በዓል ዛሬ በድምቀት #ተከብሯል

የሌቃ አባ ገዳ አስፋው ከበደ በወቅቱ እንደገለጹት ባለፉት ዓመታት በአካባቢው የኢሬቻ በዓል በድብቅና በውስን ግለሰቦች ብቻ ሲከበር ቆይቷል።

“በዛሬው እለት ከፍተኛ ቁጥር ያለው ህዝብ በይፋና በድምቀት በዓሉን አክብሯል” ያሉት አባ ገዳ አስፋው የዘንድሮ የበዓሉ አከባበር በአገሪቱ የዴሞክራሲ ስርአት ግንባታ እያበበ ስለመምጣቱ ያሳየ መሆኑን ተናግረዋል ።

አባገዳ ምስጋኑ ለሚ በበኩላቸው “የዘንድሮ የኢሬቻ በዓል በአገሪቱ የፍቅርና የአንድነት ጉዞ በተቀጣጠለበትና የዴሞኪራሲ ስርአት ግንባታው ማበብ በጀመረበት ወቅት መከበሩ ልዩ ያደርገዋል ” ብለዋል ።

አባገዳዎች፣ ቄሮዎችና መላው ታዳሚ  በዓሉን በፍቅርና በአንድነት እንዳከበሩት የገለጹት አባገዳ ምስጋኑ ህዝቡ በበዓሉ ላይ ያሳየውን የመከባበርና የአንድነት ባህል በዕለት ተዕለት እንቅስቃሴዎም አጠናክሮ እንዲያስቀጥል ጠይቀዋል።

የዘንድሮ የኢሬቻ በዓልን ህዝቡ በብዛት ተግኝቶ በነጻነት ማክበሩ ዴሞክራሲያዊ መብቱን እየተረጋገጠለት መሆኑን ያሳያል ያሉት አባገዳ ምስጉን ህዝቡ የህግ የበላይነትን በማክበር ለባህላዊ እሴቱ መጎልበት የድርሻውን እንዲወጣም መልዕክት አስተላልፈዋል ።

ወጣት ሙሉዓለም ታደሰ በበኩሉ “የዘንድሮ ኢሬቻ በዓል ያለ ማንም ወገን ጣልቃ ገብነት በህብረተሰቡ ዘንድ በሰላም ተከብሯል ” ብሏል ።

“በዓሉ የኦሮሞ ብሔር ተወላጆች ከሌሎች ኢትዮጵያውያን ወገኖቻቸው ጋር ያላቸውን ግንኙነት ያጠናከሩበት ነበር ” ሲልም ወጣቱ  ገልጿል ።

”ዘንድሮ የኢሬቻ በዓል ከወትሮ በተለየ መልኩ  ከአዳማ፣ ከቦረናና ከሌሎች አካባቢዎች የተወከሉ ወጣቶችና የአገር ሽማግሌዎች የታደሙበት ነበር”  ያለው ደግሞ ወጣት ድንቃ ገእሳ ነው ።

በበዓሉ ክብረ በዓል ላይ ከተለያዩ አከባቢዎች የተውጣጡ የህብረተሰብ ክፍሎች መታደማቸው ከዚህ ቀደም የነበረው የስጋትና የፀጥታ ችግር እየተፈታ መምጣቱን የሚያሳይ መሆኑንም ገልጿል።

በነቀምቴ “በሃዲያ” በሚባል ሥፍራ ዛሬ በተከበረው የኢሬቻ በዓል ላይ በርካታ ህዝብ መታደመበት ነው።

ምንጭ፦ ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#እንቁጣጣሽ #መስቀል #ኢሬቻ

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የእሳት እና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የአዲስ አመት በአልን ጨምሮ የመስቀል እና የኢሬቻ በአልን ተከትሎ ሊከሰቱ ከሚችሉ ማናቸውም ድንገተኛ አደጋዎች ማህበረሰቡን መታደግ የሚያስችለውን የቅድመ አደጋ ዝግጁነት ስራ መሰራቱን አሳውቋል።

ይህ የተገለፀው በኮሚሽኑ የአደጋ ምላሽ ዘርፍ ሰራተኞች ከማዕከል እና ቅርንጫፍ መስሪያ ቤቶቹ ጋር ባደረገው ውይይት ላይ ነው።

ኮሚሽኑ ቅድመ ዝግጅቱን ያጠናቀቀ ቢሆንም አደጋ ሳይከሰት ቀድሞ ለመከላከል የህበረተሰቡ ተሳትፎ ጉልህ ሚና አለው ተብሏል።

በመድረኩም ላይ ለ2014 ዓመት መስከረም ወር ላይ ለሚከበሩት ሶስቱ በዓላት፦
- አዲስ ዓመት
- መስቀል
- ኢሬቻ በዓላት ለአደጋ ምላሽ አገልግሎት የሚውሉ በቂ ግብአቶች እና ተሽከርካሪዎች መመደባቸውን የተገለፀ ሲሆን በዚህም መሰረት በ10 ክፍለ ከተማ 918 የአደጋ ሠራተኞች ፣ 39 ከባድ የአደጋ ተሽከርካሪዎች እና 22 የቅድመ ሆስፒታል አገልግሎት የሚሰጡ አምቡላንሶች ዝግጁ መሆናቸው ተገልጿል።

#ጥቆማ

ህበረተሰቡ ሳይዘናጋ እራሱን ከድንገተኛ አደጋ መከላከል እንዳለበት ተገልጿል፤ ጥንቃቄ እያደረገ ለሚገጥመው ማንኛውም አደጋ ግን ወደ ተቋሙ ስልክ ቁጥሮች ፦
• ነፃ ስልክ መስመር 👉 939
ወይም በቀጥታ የውስጥ መስመሮች ፦
• 0111555300
• 0111568601
• 0111264848 ላይ በመደወል አገልግሎቱን 24 ሰዓት ማግኘት ይችላል ተብሏል።

@tikvahethiopia
#ኢሬቻ #መስቀል #የመንግስት_ምስረታ !

የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ከመስቀል፣ ከኢሬቻ በዓላት እና ከመንግስት ምስረታ ስነ-ስርዓት በፊትና በኋላ ሊከሰቱ የሚችሉ የፀጥታ ችግሮችን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር ፤ ችግር ቢከሰት እንኳን ህጋዊ እርምጃ ለመውሰድ የሚያስችል ጠንካራ ኮሚቴ ተቋቁሞ ወደ ስራ መግባቱን ይፋ አድርጓል።

ኮሚቴው በኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮምሽነር ጀኔራል የሚመራ ሲሆን ፦
- ከኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ፣
- ከሀገር መከላከያ ሚኒስቴር፣
- ከብሔራዊ መረጃና ደህንነት፣
-ከአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን
- ከኦሮሚያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ከተውጣጡ አመራሮች የተዋቀረ ነው።

@tikvahethiopia
#ኢሬቻ

የኢሬቻ በዓል ምንድነው ? ለምንስ ይከበራል ?

የኢሬቻ በዓል ከገዳ ሥርዓት ጋር ጥብቅ ቁርኝት ያለው ሲሆን በኦሮሞ ማኅበረሰብ ዘንድ ለዘመናት ሲከበር መቆየቱን የታሪክ ምሁራን ይናገራሉ።

የማህበረሰቡ መሪዎችም ኢሬቻ " የምስጋና በዓል " እንደሆነ ይገልጻሉ።

የኦሮሞ ሕዝብ ምድር እና ሰማይን ለፈጠረው ፈጣሪው ዋቃ ምስጋናውን ለማድረስ የኢሬቻ በዓልን እንደሚያከብሩ ያስረዳሉ።

የኦሮሞ ሕዝብ ከዘመን ወደ ዘመን በሰላም ላሸጋገረው አምላክ ምስጋና የሚያቀርብበት በዓል ነው።

የኦሮሞ ታሪክ ምሁሩ ዲሪቢ ደምሴ፤ " ኢሬቻ ማለት ዋቃ (ፈጣሪ) የፈጠረውን ማመስገን ማለት ነው " ይላሉ።

ማኅበራዊ ደረጃ እና የእድሜ ልዩነት ሳይፈጠር የኦሮሞ ሕዝብ የኢሬቻ በዓልን ለዘመናት በጋራ ሲያከብር ቆይቷል።

ኢሬቻ የዘመን መለወጫ በዓልም ነው። የኦሮሞ ሕዝብ ክረምቱ በማለፉ በኢሬቻ ቀን ምስጋናውን ለፈጣሪ ያቀርባል።

በክረምት ወራት ተራርቆ ሳይገናኝ የቆየ ዘመድ አዝማድ መስከረም ላይ ይገናኛል።

ሕዝቡም ክረምቱን በፈጣሪ ፍቃድ የሞላው ውሃ ጎድሎ ከዘመድ አዝማድ አገናኝን ብሎ ምስጋና ያቀርባል።

የአንትሮፖሎጂ ባለሙያው ገመቹ መገርሳ (ዶ/ር)፤ " ክረምት ለሊት ነው። ለሊት ደግሞ ጨለማ ነው። ጨለማ ለአውሬ እንጂ ለሰው ልጅ አይሆንም። ጨለማው ሲነጋ ደግሞ ብርሃን ነው፤ ብርሃን ሲሆን ሃሳብ የለም ደስታ እንጂ። 'መስከረም በረ'ባ ማለት ይህ ነው " በማለት የኦሮሞ ሕዝብ ከክረምት መገባደድ በኋላ የኢሬቻ በዓልን የሚያከብርበትን ምክንያት ያስረዳሉ።

ዲሪቢ ደምሴ የኢሬቻ በዓልን ለማክበረ የሚወጣ ታዳሚ እንደ ሳር ወይም አበባ ያለ እርጥብ ነገር በእጁ ይዞ እንደሆነ ይገልጻሉ።

" ፈጠሪያችን ሆይ አንተ ያጸደቅከው ነው አብቦ ፍሬ ያፈራው፤ ለዚህም እናመስግንሃለን' በማለት እርጥብ ነገር ተይዞ ይወጣል" ሲሉ የታሪክ ምሁሩ ይናገራሉ።

ዲሪቢ በኢሬቻ በዓል ላይ የኦሮሞ ሕዝብ ለመላው የሰው ልጅ ሰላምና ደኅንነት ፈጣሪውን ዋቃን ይለምናል፤ ያመሰግናል ሲሉ ገልጸዋል።

የአንትሮፖጂ ምሁሩ አለማየሁ (ዶ/ር) ፤ " የተጣላ ታርቆ፣ ቂሙን ትቶ በነጻ ልቦና ፈጣሪ ንጹህ ወዳደረገው የውሃ አካል ይሄዳል። ኢሬቻ ቀልብ የሚነጻበት ቦታ ነው " ሲሉ ነው የሚያስረዱት።

____

በኢሬቻ ላይ የሚቀርበው ፀሎት እና ልመና ምንድነው ?

(ከአፍሪካ ፍልስፍና መምህሩ ዮሴፍ ሙሉጌታ ባባ (ዶ/ር) መጣጥፍ ላይ የተወሰደ) ፦

" ሀዬ!  ሀዬ!  ሀዬ! (አሜን አሜን አሜን)
ሀዬ!  የእውነትና  የሰላም  አምላክ!
ሀዬ!  ጥቁሩና  ሆደ ሰፊው  ቻይ አምላክ!
በሰላም  ያሳደርከን  በሰላም  አውለን!
ከስህተትና  ከክፉ  ነገሮች  ጠብቀን!
ለምድራችን  ሰላም  ስጥ!
ለወንዞቻችን  ሰላም  ስጥ!
ከጎረቤቶቻችን ጋር ሰላም ስጠን!
ለሰውም  ለእንስሳቱም  ሰላም  ስጥ!
ሀዬ!  ሀዬ!  ሀዬ! (አሜን አሜን አሜን! "

____

" ከመጥፎ አየር ጠብቀን!
ንፁሕ ዝናብ አዘንብልን!
ያለአንተ ዝናብ የእናት ጡት ወተት አይሰጥምና!
ያለአንተ ዝናብ የላም ጡት ወተት አይሰጥምና!
ያለአንተ ዝናብ መልካው ውኃ አይሰጥምና!
ያለአንተ ዝናብ ምድሩ ቡቃያ አይሰጥምና!
ከእርግማን ሁሉ አርቀን!
እውነትን ትቶ ከሚዋሽ አርቀን!
ከረሃብ ሰውረን!
ከበሽታ ሰውረን!
ከጦርነት ሰውረን!
ልጄ እያሉ አልቅሶ ከመቅበር ሰውረን!
ሀዬ! ሀዬ! ሀዬ! " 

የ2016 ዓ/ም የሆራ ፊንፊኔ ኢሬቻ በዓል በአዲስ አበባ ከተማ ከንጋት ጀምሮ እየተከበረ ይገኛል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ መረጃውን ያሰባሰበው ከቢቢሲ አፋን ኦሮሞ / ሪፖርተር ነው።

ተጨማሪ ቲክቫህ አፋን ኦሮሞ ፦ https://t.iss.one/+UTMftkYHBuOGaQ23

@tikvahethiopia