የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት
"ወረፋ በመብዛቱ ምክንያት ወርሃዊ የፍጆታ ሂሳብ ክፍያ በወቅቱ ባለመፈፀማቸው ደንበኞች ላይ ምንም አይነት ቅጣት አይጣልባቸውም" - የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት
.
.
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት፣ ወርሃዊ የአገልግሎት ክፍያ ለመክፈል ወረፋ በመብዛቱ ምክንያት ደንበኞች ላይ ምንም ዓይነት ቅጣት እንደማይጣልባቸው አስታወቀ።
አገልግሎቱ በአዲስ አበባ ለሚገኙ ደንበኞች የአገልግሎት ክፍያ መፈጸሚያ 33 የክፍያ ማዕካላት እንዳለው ገልጾ ደንበኞች ወረፋ በማይበዛባቸው አካባቢዎች በመሄድ የፍጆታ ሂሳባቸውን መክፈል ይችላሉ ብሏል።
ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት እንዳገኘነው መረጃ ከቀጣይ ወር ጀምሮ በአዲስ አበባ አሁን የተፈጠረውን መጨናነቅና መጉላላት ለመቅረፍ ደንበኞችን ቀድሞ እንደነበረው በአራት ምድብ በመክፈል ማለትም ግሩፕ 1- ከ26 እስከ 30፣ ግሩፕ 2- ከ1 እስከ 8፣ ግሩፕ 3- ከ7 እስከ 15 እና ግሩፕ 4- ከ12 እስከ 17 ባሉት ቀናት አገልግሎቱን የሚሰጥ ይሆናል፡፡
አገልግሎቱ አክሎም ፍቃደኛ የሆነ የመኖሪያ ቤት ደንበኛ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሂሳብ ደብተር በመክፍት በአቅርቢያው በሚገኝ የተቋሙ የአገልግሎት መስጫ ማዕከል የተዘጋጀውን የስምምነት ቅፅ በመሙላት ወርሃዊ ክፍያውን በባንኩ በኩል መፈፀም እንደሚችል ገልጿል፡፡
ለቅድመ ክፍያ የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ደንበኞችም የወረፋ መብዛትና መጨናነቅን ምክንያት በማድረግ ካርድ እንሙላላችሁ እያሉ የሚያጭበረብሩ ግለሰቦች ስላሉ ጥንቃቄ ማድረግ ይኖርባችኋል ሲል ተቋሙ አስጠንቅቋል።
Via #EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia

ከአህመዲን ጀበል
በትናንትናው እለት የፈረሰውን የአሊፍ መስጊድን ምክትል ከንቲባ ታከለ ዑማ ነገ ጠዋት በአካል በቦታው ተገኝተው በነበረበት ሁኔታ እንዲገነባ ያስደርጋሉ።
በከተማ አስተዳደሩ ያለከንቲባው ጽ/ቤት አውቅና መስጊዱ በመፍረሱና የመስጊድ ችግሮችን አጥንቶ መፍትሄ እንዲያቀርብ የተቋቋመው ኮሚቴ ሳያውቅ መስጂዶቹን አፍርሰዋል የተባሉና በትናንትናው እለት መስጊዱን የማፍረሱን ሂደት የመሩ አቶ ፀጋዬ ደምሴ የወረዳው የደንብ ማስከበር ኃለፊ እና አማን ገ/ሚከኤል የወረዳው ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ ዛሬ በተደረገ ግምገማ ከስራ ተባረው በቁጥጥር ስር ዉለዋል። አቶ ታከለ ዑማም ነገ ጠዋት በ3:30 በስፍራው በመገኘት ህብረተሰቡን ይቅርታ በመጠየቅ መስጊዱ በነበረበት መልኩ እንዲገነባ ያስደርጋሉ።
የአከባቢው ሙሰሊሞች፣ የአዲስ አበባ መጅሊስ አመራር አባላትም በስፍራው እንዲገኙ ጥሪ ቀርቧል። የአከባበው ሙስሊምም በስፍራው በመገኘት መስጊዱን እንዲገነባ ጥሪ በቀርቧል። በዚህ አጋጣሚ አቶ ታከለ ኡማ ጋር በመሆን በኢስላማዊ አደብ በትብብርና በወንድማማችነት መንፈስ መስጊዱን እንዲገነባ እኔ አህመዲን ጀበል ጥሪ አደርጋለሁ።
ከአቶ ታከለ ኡማ ጋር በስልክ ባደረግነው ንግግር እንደገለፁት በየቀኑ በአዲስ አበባ ከተማ 118 ወረዳዎች ዉስጥ የሚደረገውን እያንዳንዱን ነገር በቀጥታ እንደማያዙና ከዚህ የተነሳ መስጂዱ እንደሚፈርስ ምንም መረጃ እንደሌላቸው እንዲሁም ህገወጥም ቢሆን እንኳ የከንቲባ ፅ/ቤቱ ሳያውቅ የትኛውም የሃይማኖት ተቋም እንዳይፈርስ ከተሰጠው አቅጣጫ ዉጭ በመንቀሳቀስ መስጂዱን ባፈረሱት አካላት ላይ እርምጃ መወሰዱንና ከአሁን በዃላም ሆነ ብለው ህዝብና መንግስትን የሚያጋጩት ላይ የማያዳግም እርምጃ ይወሰዳል ብለዋል።

መስጅድ እንዲፈርስ ያደረጉት በቁጥጥር ስር ዋሉ!
የከተማውን አስተዳደር ከሕዝበ ሙስሊሙ ጋር ለማጣላት እና በጋራ ኮሚቴው የተሰራውን ሥራ ለማጠልሸት የሚሞክሩ፣ የተገኘውን አጋጣሚ ሁሉ በመጠቀም መልካም ስም ለማጉደፍ የሚኳትኑ እንዳሉ ልንገነዘብ ይገባል።
የእኩይ ተግባር ሥራ አንዱ መስጅድ በማፍስ እና የተጀመረውን መግባባት ለመናድ መሞከር ቢሆንም ግን እንደማይቻል ሊታወቅ ይገባል። ነገ ጠዋት የመጀመሪያ ሥራችን የተሻለ ቦታ በመስጠት ለሙስሊም ወንድሞችና እህቶች ያለንን የማይነቃነቅ ድጋፋችንን እናሳያለን።
ለማንኛውም ለተፈጠረው ስህተት እና ዕኩይ ድርጊት በራሴ እና በከተማችን አስተዳደር ስም ይቅርታ እጠይቃለሁ። በዚህ ተግባር ላይ የተሳተፉት እና ድርጊቱን ያስፈፀሙት በሕግ እንዲጠየቁ እና ተልዕኮአቸውን ለማጣራት ፖሊስ በቁጥጥር ሥር አውሏል።
ኢ/ር ታከለ ኡማ

#ድሬዳዋ
"አንድ ዕድል ለሰላም" በሚል መሪ ሃሳብ የተዘጋጀ የዛፍ ጥላ ሥር ውይይት ነገ በድሬዳዋ አስተዳደር እንደሚካሄድ የአስተዳደሩ የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ አስታወቀ። በውይይቱ የሚስዝ ወርልድ 2019 አሸናፊ ፣የክቡር ዶክተር አርቲስት አሊቢራና ሌሎችም ተዋቂ ሰዎች እንደሚሳተፉም ተመልክቷል። ፕሮግራሙን አስመልክተው የድሬዳዋ የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ አቶ እስቅያስ ታፈሰ ዛሬ እንደተገለጹት ሀገር በቀል ዕውቀቶችና ባህሎችን በመጠቀም ሽምግልና በአካባቢና በሀገር ሰላም ዘላቂነትን ላይ ያለውን ሚና በትውልድ ውስጥ ማስረጽ ነው፡፡ የዛፍ ጥላ ስር ውይይትን በመጀመርና ተቋማዊ አደረጃጀትን በማኖር ከባቢያዊ ግጭቶች በመከላከል ሀገር አቀፍ ሰላም እንዲረጋገጥ እንደሚሰራ ተናግረዋል፡፡

የአንድ ተጨዋች ወርሃዊ የደመወዝ ጣሪያ ከ50 ሺ ብር እንዳይበልጥ ተወሰነ!
በኢትዮጵያ ክለቦች የአንድ ተጨዋች ወርሃዊ የደመወዝ ጣሪያ ከ50 ሺ ብር እንዳይበልጥ መወሰኑን የወጣቶችና ስፖርት ኮሚሽን አስታወቀ። በተጨዋቾች ወርሃዊ ደምወዝ ጣሪያ ዙሪያ በቢሸፍቱ ውይይት ተካሂዷል። መድረኩን የኢፌድሪ ስፖርት ኮሚሽን ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጋር በመተባበር ያዘጋጁት ሲሆን የፕሪምየር ሊግ ክለቦች አመራሮችና ስራ አስኪያጆች ፣ የክልልና ከተማ አስተዳደር ኮሚሽነሮች እና የክልል ፌዴሬሽን አመራሮች፣ የተጨዋች ተወካዮች እና የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ተሳታፊ ሆነዋል።
በመድረኩ የተጨዋቾች የደምወዝ አከፋፈል የሀገራችንን ከሌሎች ሀገራት ጋር በማነፃፀር አቶ ተድላ ዳኛቸው ጥናታዊ ፅሑፍ አቅርበዋል። ጥናታዊ ፅሑፋን መሠረት በማድረግ የመድረኩ ተሳታፊዎች የተጨዋች ደመወዝ ጣሪያ ማስቀመጥ ከሀገር ከተጨዋች እና ከክለብ አንፃር ያለው ጠቀሜታ ፣ ተግዳሮቶችና አማራጮች ላይ በቡድን በቡድን በመሆን ውይይት አካሂደዋል።
በውውይቱም የተጨዋች ደመወዝ ጣሪያ መቀመጡ አዳዲስ ተጨዋቾችን ለማፍራት ፣ የገንዘብ ብክነትን ለመቀነስ፣ ተመጣጣኝ የሆኑ ክለቦች እንዲኖሩ ስለሚያግዝ፣ ስፖርታዊ ጨዋነትን ስለሚያሰፍን፣ ሌሎች ስፖርቶችን ለመደገፍ ስለሚያግዝ፣ ብቁ እና ተፎካካሪ ተጨዋች ለማፍራት ስለሚገዛ እና በርካታ ጠቀሜታ ስላለው ጣሪያ ማስቀመጡ አስፈላጊ መሆኑን ተወያዮች አንስተዋል።
ከኮሚሽኑ የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው ውይይቱን መሠረት በማድረግም የአንድ ተጨዋች ደመወዝ ጣሪያ 50 ሺ ብር እንዲሆን የተወሰነ ሲሆን ውሳኔውንም የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከዚህ ወር ጀምሮ በመመሪያ በማስደገፍ እንዲያስፈፅም አቅጣጫ ተቀምጧል።
Via ኢፕድ

የኦሮሞ ባህል ማዕከል~አዳማ!
በአዳማ ከተማ 700 ሚሊዮን ብር በሚጠጋ ወጪ የኦሮሞ ባህል ማዕከል ግንባታ እየተካሄደ መሆኑን የከተማዋ ማዘጋጃ ቤት አስታወቀ። የማዕከሉ ግንባታ እየተካሄደ ያለው ካለፉት ሁለት ወራት ወዲህ ነው።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በአዳማ ከተማ 700 ሚሊዮን ብር በሚጠጋ ወጪ የኦሮሞ ባህል ማዕከል ግንባታ እየተካሄደ መሆኑን የከተማዋ ማዘጋጃ ቤት አስታወቀ። የማዕከሉ ግንባታ እየተካሄደ ያለው ካለፉት ሁለት ወራት ወዲህ ነው።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የሰኔ 15ቱ ጥቃት ሰለባ ቤተሰቦች አቤቱታ አሰሙ!
የጀርመን ራድዮ ካነጋገራቸው ሁለት እናቶች አንደኛዋ የባለቤታቸው የጡረታ መብት መከበሩን እንዲሁም የስድስት ወር ደሞዝ ማግኘታቸውን ቢገልፁም ከ4, ሺህ ብር በላይ የወር የቤት ክራይ እየከፈሉ ሦስት ሕጻናትን በማሳደግ ላይ መሆናቸውን ይናገራሉ። ድርስ ነፍሰጡር መሆናቸውን የተናገሩት ሌላኛው በበኩላቸው የጡረታ መብታቸውን ተሯሩጠው ማስፈፀም እንዳልቻሉ፤ የስድስት ወር ደመወዝም እንዳላገኙ ገልጸዋል።
ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/SENE15-08-09

የተወሰኑ ኢትዮጵያውያን ከእስር እየተፈቱ ነው!
በደቡብ አፍሪካ ጆሃንስበርግ ውስጥ ታስረው ከሚገኙት ኢትዮጵያውያውያን መካከል የተወሰኑት ፕሪቶሪያ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኢምባሲ ባደረገው ጥረት ከእስር እየተለቀቁ መሆኑ በቦታው የሚገኙ ነጋዴዎች ለአሜሪካ ድምፅ ራድዮ ገለፀዋል። ነገር ግን የተወረሰባቸው ንብረት መጠን ብዙ በመሆኑ ከፍተኛ እገዛ እንደሚፈልጉ ገልፀዋል። የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በበኩሉ በደቡብ አፍሪካ የሚገኘው ኢምባሲ ከፍተኛ ጥረት እያደረገ መሆኑን እና ይህንኑ ጥረቱንም እንደሚቀጥል አስታውቋል። በአሁኑ ሰዓት በእስር ላይ የሚገኙት ኢትዮጵያውያን 150 ናቸውም ብሏል።

#ሊቢያ
የዓረፋ በዓልን ምክንያት በማድረግ የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲደረግ ተጠየቀ!
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሊቢያ ተፋላሚ ሃይሎች የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲያደርጉ ጥሪ አቀረበ፡፡ ተፋላሚዎቹ የኢድ አል አድሃ(ዓረፋ) በዓልን ምክንያት በማድረግ የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲያደርጉ ነው በመንግስታቱ ድርጀት ጥሪ የቀረበው፡፡
እስከ ዛሬ ምሸት ድረስም ሁለቱ ተፋላሚዎች ጥሪውን ስለመቀበል አመቀበላቸው ለመንግስታቱ ድርጅት የሊቢያ መልዕክተኛ የጽሁፍ ማረጋገጫ ያቀርባሉ ተብሎ ይጠበቃል። ከአውሮፓውኑ ሚያዚያ ወር ጀምሮ በጄኔራል ከሊፋ ሃፍጣር የሚመራው ሃይል የሊቢያን መዲና ትሪፖሊን ለመቆጣጠር በሚያደርገው ዘመቻ በተመድ እውቅና ከተሰጠው የፋይዝ አል ሳራጅ አስተዳደር ጋር ግጭት ውስጥ ገብቷል።
በዚህ ግጭት ሳቢያም ከ1 ሺህ በላይ ዜጎች ህይወት ሲያልፍ 5 ሺህ 700 ያህሉ ለአካል ጉዳት ዳርጓል፡፡ ከዚህም ሌላ 120 ሺህ ያህል ነዋሪዎችን ከመኖሪያ ቀያቸው ማፈናቀሉን የዓለም ጤና ድርጅት መረጃ ያመላክታል፡፡
ምንጭ፡- ሲ ጂ ቲኤ ን/fbc

#ቤንች_ሸኮ
በቤንቺ ሸኮ ዞን ተፈጥሮ በነበረው የጸጥታ ችግር በመሳተፍ የተለያዩ #ወንጀሎችን ፈጽመዋል የተባሉ ግለሰቦች በህግ ተጠያቂ እየተደረጉ መሆኑ ተገለፀ። ካለፈው ህዳር ወር ጀምሮ በቤንች ሸኮ ዞን ተፈጥሮ በነበረው የጸጥታ ችግር በመሳተፍ በሰው ግድያ፣ የአካል ጉዳት በማድረስ፣ ንብረት በማውደምና ዘረፋ በመፈጸም ወንጀል ተሳትፈዋል በሚል የተጠረጠሩ ግለሰቦች በህግ ተጠያቂ እየተደረጉ ነው።
የቤንች ሸኮ ዞን ፖሊስ መምሪያ አዛዥና የኮማንድ ፖስት አባል ዋና ኢንስፔክተር ምናሉ ታደሰ እንደገለፁት ከ100 በላይ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለው ጉዳያቸው በፍርድ ቤት ተጣርቶ በእስራት እንዲቀጡ እየተደረገ ነው። በጦር መሳሪያ ታግዘው ከባድ ወንጀል የፈጸሙና በአስገድዶ መድፈር መሳተፋቸው በማስረጃ የተረጋገጠባቸው አራት ግለሰቦች ከ8 እስከ 20 ዓመት በሚደርስ እስራት እንዲቀጡ መደረጉን ዋና ኢንስፔክተሩ ተናግረዋል።
Via #ENA

ተወዳጁ የእንግሊዝ ፕሪሜርሊግ ጀምሯል!
TIKVAH-ETH ስፖርት ከቅዱስ እና ጎይቶም ጋር!
ይህ የTIKVAH-ETH የስፖርት ገፅ ነው ይቀላቀሉ👇
https://t.iss.one/joinchat/AAAAAFb8M0pNEZTiGM68rg

ለመሆኑ ስፖርት ሲባል እግር ኳስ ብቻ ነው?
TIKVAH-ETH የስፖርት ገፅ ይዞ ብቅ ያለው የተደገመውን ለመድገም የተሰማውን ድጋሚ እያሰማ ለማሰልቸት አይደለም። የስፖርት ገፁ የመጣው በአጠቃላይ በሀገሪቱ ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች ትኩረቱን አድርጎ ለመስራት ነው። ያልተዳሰሱትን በስፋት ለመዳሰስ፤ የልተነገረላቸውን ለመናገረ፤ እየጠፋ የመጣውን ባህላዊ ስፖርታዊ ውድድሮችን ለመዳሰስ፤ ካራቴውን፣ ቴኳንዶውን፣ የሳይክል ውድድሩን የመኪና ውድድሩን፣ ቅርጫት ኳሱን፣ መረብ ኳሱን ... ለመዳሰስ ነው የመጣው።
በቅርቡ እጅግ ያማረ እና የወጣ አቀራረብ ይዞ ወደናተ ይደርሳል። ለጥቂት ጊዜ የሀገር ውስጥ እና የውጭ የእግር ኳስ ውድድሮች እየዳሰስን አብረን እንቆያለን።
ይህ የTIKVAH-ETH የስፖርት ገፅ ነው ይቀላቀሉ👇
⛹♀🏋♀🏂🏄♂🚴♀🥊🥋⛷🏇🤼♂https://t.iss.one/joinchat/AAAAAFb8M0pNEZTiGM68rg
@tikvahethsport

በኢሕአዴግ ጽህፈት ቤት የፖለቲካ ፓርቲዎችና ሲቪክ ጉዳዮች ኃላፊ አቶ ፍቃዱ ተሰማ፦
ኢሕአዴግ "ዝርዝርና ብስል" ግምገማ አድርጊያለሁ ብሏል። አቶ ፍቃዱ ተሰማ እንዳሉት ሥራ አስፈጻሚው በኢሕአዴግ አባል ፓርቲዎች መካከል አንድነትን የሚጎዱ ነገሮች እንዲታረሙ፣ ፓርቲዎቹም እርስ በርስ #ከመወነጃጀል እንዲቆጠቡ ድምዳሜ ላይ ተደርሷል።
"የተቀመጡ አቅጣጫዎችን በሙሉ ልብ ሁሉም ወስደው በተመሳሳይ ሁኔታ ያለመፈጸም" ችግር በኢሕዴግ አባል ፓርቲዎች መካከል መኖሩን ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴው እንደደረሰበት አቶ ፍቃዱ ተናግረዋል። በጋራ የተወሰኑ ጉዳዮች እኩል ተግባራዊ አይሆኑም ብለዋል።
የሕግ የበላይነትን ማስከበር ፣ ለውጡን ተቋማዊ ማድረግ፣ "የለውጡን ምንነት ማስረዳት"፣ በ2012 "ሰላማዊ፣ ዴሞክራሲያዊና ፍትኃዊ ምርጫ" ለማካሔድ መዘጋጀት፣ ደኢሕዴን ላሰራው "ሳይንሳዊ ጥናት" ድጋፍ ማድረግ ከኢሕአዴግ ውሳኔዎች መካከል ይገኙበታል።
Via #EshetBekele
@tsegabwode @tikvahethiopia

የዕለቱ መልዕክት፦
”ማንም ሰው ሌላውን ሰው በዘሩ እና በቆዳው ቀለም፤ ውይም በሃይማኖቱ እንዲጠላ ሆኖ አልተወለደም፤ ሰዎች መጥላትን ተምረውት ነው። የሰው ልጅ #ጥላቻን ከተማረ፤ ፍቅርንም መማር ይችላል፤ እንደውም ፍቅር ለሰው ልጅ ተፈጥሮ ከጥላቻ ይልቅ ቅርብ ነው።” ኔልሰን ማንዴላ
#share #ሼር
@tsegabwolde @tikvahethiopia
”ማንም ሰው ሌላውን ሰው በዘሩ እና በቆዳው ቀለም፤ ውይም በሃይማኖቱ እንዲጠላ ሆኖ አልተወለደም፤ ሰዎች መጥላትን ተምረውት ነው። የሰው ልጅ #ጥላቻን ከተማረ፤ ፍቅርንም መማር ይችላል፤ እንደውም ፍቅር ለሰው ልጅ ተፈጥሮ ከጥላቻ ይልቅ ቅርብ ነው።” ኔልሰን ማንዴላ
#share #ሼር
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ኢ/ር ታከለ ኡማ ለቡ አከባቢ ሰሞኑን በፈረሰው አሊፍ መስጅድ በመገኘት ከሀይማኖት አባቶች ጋር ተነጋግረዋል፡፡
-
ኢ/ር ታከለ ኡማ በን/ስ/ላፍቶ ክ/ከተማ ያለ ከተማ አስተዳደሩ እውቅና ውጪ የፈረሰውን የአሊፍ መስጅድ ዛሬ ጎብኝተዋል፡፡
ኢ/ር ታከለ ጥቂቶች የከተማ አስተዳደሩን በተንኮል ከሙስሊሙ ማህበረሰብ ጋር ሊያጋጩ እና በሴራ ሊበትኑ ቢያስቡም እኛ ግን ችግሮችን በተሻለ መንገድ እናልፋቸዋለን ብለዋል።
የከተማ አስተዳደሩ የማምለኪያ ቦታዎችን በተመለከተ ያለውን ችግር በዘላቂነት ለመቅረፍ ከሁሉም የእምነት ተቋማት ጋር በትብብር እየሰራ እንደሆነም ኢ/ር ታከለ ኡማ ተናግረዋል፡፡
መስጅዱን በማፍረስ የተሳተፋ አካላትን ተጠያቂ ከማድረግ ጎን ለጎንም መስጅዱን በተሻለ ሁኔታ ለመገንባት በን/ላ/ክ/ከተማ ወረዳ አንድ 4 ሺህ ካ.ሜ ተለዋጭ ቦታም ለአዲስአበባ መጅሊስ ተላልፏል፡፡
ከተጀመረው የለውጥ ጉዞ የሚያስተጋጉሉንን ለመግታት አሁንም የጋራ ጥረታችን ሊቀጥል እንደሚገባም ኢ/ር ታከለ ኡማ ተናግረዋል፡፡
Via @mayorofficeAA

4 ሺህ ካ.ሜ ተለዋጭ ቦታ ተላለፈ!

#Congratulations #ASTU የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስክ ያስተማራቸውን ተማሪዎች እያስመረቀ ይገኛል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia