TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update የተሽከርካሪዎችን የፍጥነት መገደቢያ መሳሪያ ስለመግጠም የወጣው መመሪያ ተግባራዊ መደረግ ጀመረ፡፡ የፌዴራል ትራንስፖርት ባለስልጣን ለመገናኛ ብዙሃን በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ በሁሉም ተሽከርካሪዎች ላይ ተግባራዊ የሚደረግ የተሽከርካሪዎች የፍጥነት መገደቢያ መሳሪያ ስለመግጠም እና ስለማስተዳደር የወጣ መመሪያ ቁጥር 27/2011 ተግባራዊ መደረግ መጀመሩን አስታውቋል፡፡

በመግለጫውም የፌዴራል ትራንስፖርት ባለስልጣን የመንገድ ደህንነት ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ምትኩ አስማረ እንደተናገሩት መመሪያውን ማውጣት ያስፈለገበት ዋናው ምክንያት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ ለመጣው የትራፊክ አደጋ ዋና መንስኤው አሽከርካሪዎች ከተፈቀደው የፍጥነት ወሰን በላይ ማሽከርከራቸው እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

ይህ በመሆኑም አደጋውን ለመቀነስ የተሸከርካሪዎች የፍጥነት መገደቢያ መሳሪያ በተሸከርካሪዎች ላይ ለመግጠም እና ለማስተዳደር የሚያስችል መመሪያ ማውጣት አስፈላጊ መሆኑን ጨምረው ገልጸዋል፡፡

በመመሪያው መሰረት መሳሪያው ከትላንት ተሽከርካሪዎች ላይ መግጠም ይጀምራል፡፡ አሁን ካለው ነባራዊ ሁኔታ በቅድሚያ ለንግድ አገልግሎት በሚውሉ ተሽከርካሪዎች ላይ መገጠም የሚጀምር ሲሆን በቀጣይም ሁሉም ተሽከርካሪዎች ላይ ይገጠማል ተብሏል፡፡

Via #አዲስቲቪ
@tsegabwolde @tikvahethiopia