TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ቴዎድሮስ በእስር ላይ ይገኛል‼️

#ቴዎድሮስ_አዲሱ(ቴዲ ማንጁስ) በ80 ሺህ ብር ዋስ ቢፈቀድለትም #በሙስና_ወንጀል ተጠርጥሮ በእስር ላይ ይገኛል፡፡

ቴዎድሮስ አዲሱ ከሀምሌ 28-30 ቀን 2010ዓ.ም በጀጅጋ እና አካባቢው ተከስቶ በነበረው ሁከትና ብጥብጥ ተጠርጥሮ በተደጋጋሚ ፍርድ ቤት ቢቀርብም ዐቃቤ ህግ በጉዳዩ ላይ ምርመራውን ስላላጠናቀቀ እና በተደጋጋሚ የጊዜ ቀጠሮ መጠየቁ #ፍትሃዊ አለመሆኑንና የግለሰቡን ፍትህ የማግኘት መብት የሚጎዳ መሆኑን በማመን መዝገቡ እንዲዘጋ የጠየቀ ሲሆን ፍርድ ቤቱም በ80 ሺህ ብር ዋስ #እንዲወጣ ፈቅዶ ነበር፡፡

ሆኖም ግን ግለሰቡ በሌላ ወንጀል ከቀድሞው የሱማሌ ክልል ምክትል የትምህርት ቢሮ ኃላፊና ከኒያላ ኢንሹራንስ የጅጅጋ ቅርንጫፍ ስራ አስኪያጅ ጋር በመመሳጠር #በተጭበረበረ የኢንሹራንስ ዋስትና አፈጻጸም የቅድመ ክፍያ ቦንድ ከኢንሹራንስ እንዲጻፍ በማድረግ በውሉ ላይ ከተጠቀሰው ቅድመ ከፍያ ላይ ብር 15,306,303.3 ከክልሉ ትምህርት ቢሮ ወጪ በማድረግ የወሰደ በመሆኑ ለትምህርት ቤቱ መፀሐፍቱን ሳያቀርብ ገንዘቡን ከጥቅም ተጋሪዎች ጋር በመከፋፈል ለግል ጥቅማቸው አውለዋል በሚል በሙስና ወንጀል ተጠርጥሮ ምርመራ እየተካሄደበት ይገኛል፡፡

መርማሪ ፖሊስ በቴዎድሮስ አዲሱ ላይ #በከባድ የሙስና ወንጀል የጀመረውን ምርመራው ለማከናወን የ14 ቀን ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ተፈቀደለት ተጠርጣሪው በእስር ቤት እንዲቆይ እና ለየካቲት 5 ቀን 2011 እንዲቀርብ ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡

ምንጭ፦ የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Wanted #ይፈለጋሉ

የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ አይተንፍስ እንደሻው ስለሺ እና ያቤል መንገሻ የተባሉ ግለሰቦችን (በፎቶ ከላይ ይታያሉ) በወንጀል እፈልጋቸዋለሁ ብሏል።

ፖሊስ እነዚህን 2 ግለሰቦች የሚፈልጋቸው #በከባድ_የማጭበርበር ወንጀል መሆኑን ገልጿል።

ግለሰቦቹን ያየ አልያም ያሉበትን የሚያውቅ ዘውትር በስራ ሰዓት ከ2:30 - 11:30 በ01115309047 / 01111711206 እና በማንኛውም ሰዓት በ0111119475 / 0111711012 በመደወል እንዲያሳውቀው የጠየቀው የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ህብረተሰቡ የተለመደውን ትብብሩን እንዲያደርግ ጥሪ አቅርቧል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#WachemoUniversity ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ በስድስት ወራት ብቻ ለአንድ ሰው የ1 ሺህ 496 ቀን አበል / 1 ሚሊዮን 56 ሺህ 854 ብር አበል የተከፈለበት ግቢ ነው። የዚሁ ተቋም ፕሬዝዳንቱን እና ምክትል ፕሬዜዳንቱን ጨምሮ ሌሎችም ኃላፊዎቹ በሕግ ቁጥጥር ስር መዋላቸው ተነግሯል። @tikvahethiopia
#WachamoUniversity

#በከባድ_የሙስና_ወንጀል የተጠረጠሩት የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንትና ምክትል ፕሬዚዳንትን ጨምሮ በአጠቃላይ በ6 ግለሰቦች ላይ የ15 ቀን ክስ የመመስረቻ ጊዜ ተፈቀደ።

የክስ መመስረቻውን የፈቀደው የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ ጊዜ ቀጠሮ ችሎት ነው።

ተጠርጣሪዎቹ ፦
1ኛ. የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ሀብታሙ አበበ አጊሾ ( ዶ/ር)፣
2ኛ. የዩኒቨርሲቲው አካዳሚና ምርምር ዘርፍ ምክትል ፕሬዚዳንት ታምራት ታገሰ ተኮራ (ዶ/ር)፣
3ኛ. ኮንትራክተር የሆነው ደሳለኝ አስረዳ፣
4ኛ. የዩኒቨርሲቲው የግንባታ ፕሮጀክት ጽ/ቤት ኃላፊ ሙላቱ ኤርትሮ ጡንዳዳ፣
5ኛ. የዩኒቨርሲቲው የፋይናንስ ዳይሬክተር ማርቆስ ዮሃንስ ረገዮ እና
6ኛ. የቀድሞ የአዋሽ ባንክ ሆሳህና ቅርጫፍ ስራ አስኪያጅ የነበረው መለሰ ግርማ ኤርጋኖ ናቸው።

የዐቃቤ ሕግ የክስ መዝገብ ምን ይላል ?

ተጠርጣሪዎች በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ፣ ለንግስት ኢሌኒ መታሰቢያ ሆስፒታል የኦክስጂን ማምረቻ ለማስገንባት መቀመጫውና ዋናው መ/ቤቱን ካናዳ ቶሮንቶ ካደረገ " ኤ. ኤ. ኤምዲ. ቴክኖሎጂ ኢንካ " ለተባለ ድርጅት የመንግስትን የግዢ መመሪያው ባልጠበቀ መንገድ በ5 አመት አፈጻጸሙ እየታየ መከፈል የሚገባውን አሰራሩን በመተላለፍ በውል ላይ የተዘረዘሩ ስራዎች ሙሉ በሙሉ ባልተሰሩበት ሁኔታ ለድርጅቱ የ57 ሚሊየን 383 ሺህ 956 ብር ከ72 ሳንቲም ለታለመለት አላማ ሳይውል በመክፈል ጉዳት እንዲደርስ አድርገዋል።

የውል ማስከበሪያ የውሉን ጠቅላላ ዋጋ 10 ከመቶ ማለትም 117 ሚሊየን 10 ሺህ 859 ብር ከ60 ሳንቲም የውል ማስከበሪያ ሳይቀርብ እና ስራውም በውል ላይ በተገለጸው ጊዜ ሳይጠናቀቅ በመቅረቱ ይህ የውል ማስከበሪያ ዋስትና ቀርቦ ቢሆን ኖሮ ለመንግስት ገቢ መደረግ የነበረበትን ጥቅም አሳጥተዋል።

" ደሳለኝ አስረደ የግንባታ ስራዎች ተቋራጭ " የመምህራን መኖሪያ ቤት ሁለት (2) ህንጻ ግንባታ ስራ ግንቦት 2013 ዓ/ም እና ጥር 2016 ዓ/ም ላይ በተገባው ውል መሰረት ለዚሁ ህንፃ ተቋራጭ በተጋነነ ዋጋ በመስጠት 272 ሚሊየን 170 ሺህ 210 ብር ከ60 ሳንቲም ያለአግባብ ለተጨማሪ የግንባታ ወጪ መደረጉ ፤ ክፍያ በመፈጸም በዚህ ልክ በመንግስት ላይ ጉዳት በማድረስና ለውለታ 26 ሚሊዮን ብር ጥቅም ማስገኘትና ማግኘት።

በዝምድና እንዲሁም በትውውቅ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ባለቤት እህት እና ሌሎች 2 ሰራተኞች ባልሰሩት ስራ በአበል መልክ የዩኒቨርሲቲውን ገንዘብ ያለአግባብ በመመዝበር ከ6 ሚሊየን ብር በላይ ጉዳት ደርሷል።

ተጠርጣሪዎቹ ከሌሎች እስካሁን ድረስ እጃቸው ለጊዜው ካልተያዙ ተጠርጣሪዎች ጋር በመመሳጠር በመንግስት ላይ 487 ሚሊየን 333 ሺህ 912 ብር ከ78 ሳንቲም ጉዳት እንዲደርስና ለሌሎች ያልተገባ ጥቅም እንዲያገኙ ተደርጓል።

ዐቃቤ ሕግ 15 ቀን የክስ መመስረቻ እንዲሰጠው ፍርድ ቤትን ጠይቋል።

የተጠርጣሪ ጠበቆች ዋስታና ጠይቀዋል።

ፍ/ቤት የተጠርጣሪዎችን ዋስትና በማለፍ ለዐቃቤ ሕግ የ15 ቀን የክስ መመስረቻ ጊዜ መፍቀዱን ኤፍ ቢ ሲ ዘግቧል።

Via https://telegra.ph/FBC-08-15

@tikvahethiopia