TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update የሳይንስ እና ቴክኖ. ዩኒቨርሲቲ⬇️

አዳማና አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የሚገቡ ተማሪዎች የመግቢያ ፈተና ለ3ኛ ጊዜ ሊሰጥ ነው።

በ2011 #የአዳማና #የአዲስ አበባ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የሚገቡ ተማሪዎች ፈተና ለ3ኛ ጊዜ ‘#በቀጥታ’ በበይነ መረብ ሊሰጥ መሆኑ ተገልጿል።

በሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ስር የሚገኙት የአዳማና የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲዎች ለ2011 የትምህርት ዘመን የመሰናዶ ትምህርት ጨርሰው #ከፍተኛ ውጤት ያመጡትና ለፈተና ከቀረቡት 4 ሺህ 700 ተማሪዎች መካከል በፈተና በማወዳደር 3ሺህ ተማሪዎች ሊቀበል መሆኑ ተገልጿል፡፡

ፈተናው #ረቡዕ ነሃሴ 30፣ 2010 ከጠዋቱ 2፡00 ጀምሮ እስከ 11፡00 ድረስ በተለያዩ ክልሎች ባሉ 37 ዩኒቨርስቲዎች በቀጥታ በበይነ መረብ የሚሰጥ ሲሆን፥ የመግቢያ ውጤቱ ለታዳጊ ክልሎች፣ ለሴቶችና አካል ጉዳተኞች ዝቅ እንዲል ተደርጓል ተብሏል፡፡

ፈተናው ፊዚክስ፣ ባዮሎጂ፣ ኬሚስትሪ፣ ሂሳብና ኢንግሊዝኛ የትምህርት ዓይነቶቸን የሚያካትት ሲሆን፥ ዝቅተኛው የማለፊያ ውጤት ከ50 በላይ ሁኗል ተብሏል፡፡

ፈተናው በበይነ መረብ ከአንድ ማዕከል የሚተላለፍ ሲሆን፥ የወረቀት ብክነትንና የፈተና ስርቆትን ለማስቀረት ከፍተኛ እገዛ እንደሚያደረግ ነው የተገለጸው፡፡

ታላላቅ ድርጅቶች ብዛት ያለው የሰው ሀይል ለመቅጠር በፈተና ማወዳደር በሚፈልጉበት ጊዜ ይህንን ስርዓት በመጠቀም ፈትነው ለቃለመጠይቅ ብቻ የሚፈልጉትን ሰው በመጥራት መቅጠር እንዲችሉ ያደርጋል ተብሏል፡፡

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርም ይህንን የፈተና ስርዓት መጠቀም ለሚፈልግ ማንኛውንም አካል ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆኑንም አስታውቋል፡፡

©fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia