TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.44K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ኡቡንቱ #Ubuntu #አርባምንጭዩኒቨርሲቲ

(ዶክተር ዳምጠው ዳርዛ) የአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጋር በነበራቸው ቆይታ በዩኒቨርሲቲው ስላለው ሰላም እንዲሁም አጠቃላይ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ተከታዩን መልዕክት አስተላልፈዋል፦

"በከፍተኛ ትምህርት ተቋሙ ውስጥ የሚገኙ ተማሪዎች የአዕምሮ ሥራ የሚሰሩ ተማሪዎች ናቸው፡፡ በዩኒቨርሲቲው የሚቆዩበት ጊዜም አጭር በመሆኑ ባላቸው ጊዜ አዕምሯቸውን ሙሉ ለሙሉ በሳይንሱ ሥራ ላይ ቢያተኩሩ ወደፊት ለሀገራቸውም ሆነ ለራሳቸው ሙሉ የሆነ የዕውቀትና የክህሎት አስተሳሰብ ታጥቀው ይወጣሉ፡፡ ይህ ባልሆነበት ግን በሌሎች ሀሳብና አስተሳሰብ ጊዜን ማባከን በተሟላ መልኩ ሊያገኙት የሚችሉትን ነገሮችን ያጓድላል፡፡ እኛም እንደ አርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ አሁን ላይ ትኩረት አድርገን እየሰራን የምንገኘው ጊዜን መሻማት ላይ ነው፡፡ በዚህም የትምህርት ዘመኑ ሰላማዊ በሆነ መንገድ እንዲቀጥል እየሰራን እንገኛለን፡፡ ሌሎች ግቢዎች ላይ የሚፈጠሩ ችግሮች እኛንም እኩል የሚያሙን ጉዳዮች ናቸው፡፡ ያሉ ችግሮች ተቀርፈው ጊዜን በአግባቡ መጠቀም እንዲቻል ሁሉም የድርሻውን መወጣት ይጠበቅበታል፡፡"

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia