TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Update

በ " ሸገር ከተማ " እየተካሔደ ያለውን የመስጅድ ማፍረስ ተግባር በመቃወም በዛሬው እለት በአዲስ አበባ የተለያዩ መስጂዶች የተቃውሞ ሰልፍ ተካሂዷል።

እንደ ሀሩን ሚዲያ ዘገባ ፤ በተቃውሞው ሰልፎቹ የከተማ አስተዳደሩ እየሄደበት ያለው አካሔድ #ትክልል_አለመሆኑን እና #በአስቸኳይ እንዲያቆም የተጠየቀ ሲሆን ያፈረሳቸውንም መስጂዶች ይቅርታ ጠይቆ መልሶ እንዲገነባ ተጠይቋል።

በአንዋር መስጂድ በነበረው ተቃውሞ የፀጥታ ኃይሎች ተቃውሞውን ለመበተን ኃይል ስለመጠቀማቸው የአይን እማኞች ተናግረዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከቤተሰቦቹ በደረሰው መልዕክት የተጎዱ ሰዎች ስለመኖራቸው ለማወቅ ችሏል።

እስካሁን በከተማ አሰተዳደሩ በኩል የተሰጠ ማብራሪያ የለም።

በአዲሱ የሸገር ከተማ አስተዳደር እየተካሄደ ካለው የመስጂድ ፈረሳ ጋር በተያያዘ የኦሮሚያ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤት ከቀናት በፊት በሰጠው መግለጫ ድርጊቱን እንደሚያወግዝ ገልጾ የጁመዐ ኹጥባ በሸገር ከተማ የተደረገውን መስጂዶችን የማፍረስ ዘመቻን በማውገዝ እንዲሆን ጥሪ ማቅረቡ ይታወሳል።

እንደ የኦሮሚያ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤት መረጀ ፤ በአስተዳደሩ እስካሁን ከ19 በላይ መስጂዶች ፈርሰዋል።

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤትም ፤ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ደብዳቤ መፃፉና በደብዳቤው በሸገር ከተማ እያፈረሱ ስላሉ መስጂዶች አስቸኳይ መፍትሄ እንዲሰጥ መጠየቁ የሚዘነጋ አይደለም።

ማስታወሻ 1.  https://t.iss.one/tikvahethiopia/78657?single

ማስታወሻ 2. https://t.iss.one/tikvahethiopia/78541?single

ፎቶ፦ ከማህበራዊ ሚዲያ

@tikvahethiopia