TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#CBE

ባንኩ ያጋጠመውን የ‹‹ሲስተም›› ችግር ለመፍታት ጥረት እያደረገ መሆኑን አስታወቀ፡፡ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የገጠመው ‹‹የሲስተም›› ችግር በሁለት ቀናት ውስጥ ሙሉ በሙሉ ሊፈታ እንደሚችልም አስታውቋል፡፡

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ላለፉት ሁለት ቀናት የ‹‹ሲስተም›› ብልሽት አጋጥሞታል፡፡ በዚህም የተነሳ ደንበኞች ለእንግልት መዳረጋቸውን ተናግረዋል፡፡

እንደ ሀገር በየወቅቱ እየተፈጠረ ባለው የ‹‹ኔት ወርክ›› እና የኤሌክትሪክ ኃይል መቆራረጥ ባንኩ ለችግር እየተጋለጠ መሆኑን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ የአብሥራ ከበደ ለአብመድ ገልጸዋል፡፡ ይህም ደንበኞቹን ለእንግልት እየዳረገበት እንደሆነም ነው አቶ የአብሥራ ያስታወቁት፡፡

ለሁለት ቀናት በባንኩ ደንበኞች ላይ የተፈጠረው መጉላላት ምክንያቱ የ‹‹ሲስተም›› ብልሽ እንደሆነ የገለጹት የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊው ችግሩ ከተከሠተበት ጊዜ ጀምሮ በፍጥነት ለመፍታት ጥረት እየተደረገ እንደሆነ ነው የተናገሩት፡፡

ባንኩ በመላው ሀገሪቱ ከ 1ሺህ 450 በላይ ቅርንጫፎች አሉት ተብሏል፡፡ ደንበኞች በበዙ ቁጥር ችግሩ ስለሚኖር ይህንን የሚፈታ ዘመናዊ ቴክኖሎጂ ወደ ሥራ ለማስገባት በእቅድ እየተሠራ እንደሆነ ነው ባንኩ ለአብመድ ያስታወቀው፡፡ ችግሩ ዛሬ ወይም ነገ ሙሉ በሙሉ ሊፈታ እንደሚችልም አቶ የአብሥራ አስታውቀዋል፤ ለተፈጠረው ችግርም ይቅርታ ጠይቀዋል፡፡ ደንበኞች ችግሩ እስኪፈታ #በትዕግሥት እንዲጠብቁም ባንኩ ጠይቋል፡፡

Via #AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia