TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.9K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የአዲስ አበባ ከተማ ውሃና ፍሳሽ‼️

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን #በአፍሪካ_ህብረት የመሪዎች ስብሰባ የውሃ ችግር እንዳይከሰት ልዩ ኮማንድ ፖስት አቋቁሞ እየሰራ መሆኑን አስታወቀ።

ባለስልጣኑ መሪዎቹ ስብሰባ የሚያካሂዱበትን አካባቢ ጨምሮ ያርፉባቸዋል ተብለው በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በተለዩ 56 ሆቴሎች ውሃ በአግባቡ እንዲደርስ እየሰራ መሆኑን፥ የባለስልጣኑ የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች የስራ ሂደት መሪ ወይዘሮ #ሰርካለም_ጌታቸው ተናግረዋል።

ኤፍ ቢ ሲ እንደዘገበው ይህ ስራም ከአቃቂ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ውጭ በሁሉም ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤቶች የሆቴሎቹን ዝርዝር በመበተን ከጥር 15 ቀን 2011 ዓ.ም ጀምሮ እየተሰራ መሆኑንም ነው የተናገሩት።

በዚህ ሂደትም ሆቴሎቹ ውሃ የሚያገኙበትን መስመር የመፈተሽና ሲቋረጥ ያላቸውን የውሃ መጠን በመለየት በቦቴ ተሽከርካሪ ማቅረብ የሚያስችል ስራ ሲሰራ መቆየቱን አስታውሰዋል።

ከጥር 29 ቀን 2011 ዓ.ም ጀምሮ ደግሞ በማዕከል የሚመራ ኮማንድ ፖስት እስከ ምሽቱ 4 ሰዓት ድረስ እየሰራ ይገኛልም ነው ያሉት።

ኮማንድ ፖስቱ ሆቴሎቹ በሚገኙባቸው መገናኛ፣ መካኒሳ፣ አራዳ እና ንፋስ ስልክ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤቶች ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ለመንቀሳቀስ የሚያግዝ ባጅ በመያዝ እየሰራ ይገኛል።

ልዩ ኮማንድ ፖስቱ በዋናነት በስብሰባው ወቅት ለመሪዎቹ የውሃ አገልግሎት እንዳይቋረጥና በዚህ ሳቢያ የሃገሪቱ ገጽታ እንዳይበላሽ ለማድረግ የሚሰራ ነው።

ምንጭ፦ ፋና ብሮድካስቲንግ
@tsegabwolde @tikvahethiopia