TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.7K photos
1.49K videos
211 files
4.06K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
አሳዛኝ ዜና‼️

3 የአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የወሃ ማጠራቀሚያ ገንዳ(water treatment pond) ውስጥ ገብተው #ህይወታቸው_አልፎ መገኘቱ ተሰምቷል። ተማሪዎቹ መቼ ገንዳ ውስጥ ገብተው ህይወታቸው እንዳለፈ እስካሁን #አልታወቀም። የአንደኛው ተማሪ አስክሬን ትላንት 5:00 የተገኘ ሲሆን የቀሩት ሁለት ተማሪዎች አስክሬን ዛሬ ጥዋት 3:00 እና 5:00 በፍለጋ ተገኝቷል። ስለተማሪዎቹ ህልፈትም የተማሪዎች ህብረቱን ጠይቄ አረጋግጫለሁ። ስለአሟሟታቸው በፖሊስ ማጣራት እየተደረገ ይገኛል። የተማሪዎቹ አስክሬን ለህክምና ምርመራ ወደሆስፒታል ተወስዷል።

🔹መረጃውን ያረጋገጠልኝ የተማሪዎች ህብረት ተወካይ የሟች ተማሪዎችን ስም ዝርዝር አድርሶኛል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አ.ሳ.ቴ.ዩ‼️

ሶስቱ የአዳማ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች አማሟት ላይ ፍንጭ ለማግኘት ፖሊስ #ምርመራ እያደረገ እንደሆነ ገለፀ።

ከሰሞኑ በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ ለፍሳሽ ቆሻሻ ማጣሪያ ባዘጋጀው የውሃ ገንዳ ውስጥ ሶስት ተማሪዎች #ህይወታቸው_አልፎ መገኘቱ በማህበራዊ ሚዲያ መነጋገሪያ ሆኖ ቆይቷል።

ስለተማሪዎቹ አሟሟት ከተለያዩ አቅጣጫዎች የተለያዩ መላምቶች ቢሰነዘሩም ይሄ ነው የሚባል ተጨባጭ መረጃ አልተገኘም ነበር።

በዚሁ ጉዳይ ላይ ትክክለኛ መረጃ ለማግኘት ቢቢሲ የአዳማ ፖሊስ መምሪያ ሃላፊ ኮማንደር ደረጀ ሙልዕታ ስለሁኔታው ማብራሪያ ጠይቋቸዋል።

ኮማንደሩ እንደገለፁት ዩኒቨርሲቲው ፍሳሽ ቆሻሻን ተመልሶ ጥቅም ላይ ለማዋል የሚረዳ የውሃ ማጠራቀሚያ ኩሬ ውስጥ አንድ ሰው ህይወቱ አልፎ እንደታየ ለፖሊስ በዩኒቨርሲቲው በኩል ጥቆማ ይደርሰዋል።

ጉዳዩን ለማጣራትም የፖሊስ አባላት የተላኩ ሲሆን እንደተባለውም አንድ ሬሳ መርማሪ ፖሊሶቹ በማግኘታቸው፤ የሞቱን ምክንያት ለማጣራት ጥረት የተደረገ ሲሆን ተጨማሪ ምርመራ ለማድረግ ሬሳው ወደ አዲስ አበባ ተልኳል።

በማግስቱም ሌላ ሬሳ በውሃ ኩሬው ውስጥ እንደታየ ጥቆማ ለፖሊስ መድረሱን ኮማንደሩ ገልፀው ፖሊሶች በቦታው ሲደርሱም ተጨማሪ ሁለት ሬሳዎች በውሃው ውስጥ አግኝተዋል።

ፖሊስ ባደረገው ማጣሪያ መሰረትም ሶስቱም የዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች ሲሆኑ "በጣም የሚዋደዱና የማይለያዩ የአራተኛ ዓመት ተማሪዎች እንደነበሩ አረጋግጠናል" ብለዋል ኮማንደር ደረጀ።

ተማሪዎቹን ለሞት ያበቃቸው ምክንያት ምን እንደሆነ ለማጣራት የጀመሩት ምርመራ እንዳለ ሆኖ ተጨማሪ የህክምና ማስረጃ ለማግኘት ሶስቱንም አስከሬኖች ወደ ጳውሎስ ሆስፒታል የተላኩ ሲሆን የምርመራው ውጤት ሲደርሳቸው ለህዝብ ይፋ እንደሚያደርጉ ኮማንደሩ በተጨማሪ ገልጸዋል።

ተማሪዎቹ የሞቱት ከዘር ጥቃት ጋር በተያያዘ እንደሆነ በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች እየተሰራጨ ሲሆን ከዚህ ጋር በተያያዘስ ምን አይነት መረጃ አግኝታችኋል? ሲል ቢቢሲ ለኮማንደሩ ጥያቄ አቅርቦ ነበር።

ኮማንደሩ ሲመልሱም "ተማሪዎቹ ከመጡበት አካባቢ ጋር ተያይዞ ጥቃት እንደደረሰባቸው የሚያሳይ ምንም አይነት መረጃ አላገኝንም፤ ተማሪዎቹም ከተለያየ አካባቢ ነው የመጡት" ብለዋል።

''እንደውም ተማሪዎቹ ከአዲስ አበባ፣ ከባህርዳርና ከአሰላ የመጡ ጓደኛሞች ሲሆኑ በምርመራ ወቅትም ሰውነታቸው ላይ ምንም አይነት ምልክት አላገኘንም።'' ብለዋል።

ከዚህ በኋላ መሰል ክስተቶች እንዳያጋጥሙ ፖሊስ በውሃ ማጣሪያ ኩሬው አካባቢ ጥበቃ እየተደረገ እንደሆነና ኩሬው ለወደፊቱ በአጥር እንዲከለል ከዩኒቨርሲቲው ጋር ስምምነት ላይ መድረሳቸውን አክለዋል።

በመጨረሻም በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች የሚተላለፉ የተሳሳቱ መልእክቶችን ሳያጣሩ ከማመን ማህበረሰቡ እነዲቆጠብና እንዲህ አይነት ክስተቶች ሲያጋጥሙ ትክክለኛውን መረጃ ከሚመለከተው አካል እንዲጠብቁ ኮማንደሩ አሳስበዋል።

ምንጭ፦ BBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia