TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#የመንግስት_ጥብቅ_ማስጠንቀቂያ

በጎንደር ከተማ የተፈጠረውን ክስተት ተከትሎ ግጭትን ለማስፋፋት እየሰሩ ያሉ የግጭት ነጋዴዎች ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ መንግስት አስጠንቅቋል።

የጎንደሩን ክስተት ተከትሎ ግጭት ወደ ሌሎች አካባቢዎች እንዲስፋፋ እየተሰራ ያለው አሳፋሪ ተግባር በክርስትናም ሆነ በእስልምና ሃይማኖት ተቀባይነት የለውም ብሏል።

የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዶ/ር ለገሰ ቱሉ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ በሰጡት መግለጫ ፤ መንግስት የግጭቱ ምክንያት ምንም ይሁን ምን ተግባሩ የሚወገዝና ተቀባይነት የሌለው አሳፋሪ ተግባር ነው ብሎ እንደሚያምን ተናግረዋል።

ህዝቡ የግጭት ነጋዴዎች የሚያተርፉት አንዱን ከአንዱ በማጋጨት መሆኑን በመረዳት ከግጭት አባባሽ ተግባራት እንዲቆጠብ ጥሪ አቅርበዋል።

ግጭትን ለማስፋፋት የሚደረገውን የትኛውንም እንቅስቃሴ መንግስት አይታገስም ብለዋል።

ጎንደር ከተፈጠረው ክስተት ጋር በተያያዘ እስካሁን በርካታ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን አሳውቀዋል።

ሀሰተኛ መረጃ በማሰራጨት ተጨማሪ ግጭት እና ጥፋት እንዲፈጠር እየሰሩ ያሉ አካላት አሉ ያሉት ዶ/ር ለገሰ ፤ በዚህ አፍራሽ ተግባር እየተሳተፉ ያሉ አካላት ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡም አስጠንቅቀዋል።

ችግሩን ወደ ሌሎች አካባቢዎች ለማስፋት እየሰሩ ያሉ አካላትን መንግሥት እንደማይታገስ ገልፀው ፤ ወንጀልን በወንጀል ለማካካስ የሚደረግ ማንኛውም ጥረት ከወንጀል ፈፃሚነት ተለይቶ አይታይም ብለዋል።

የአማራን ህዝብ በሃይማኖት፣ በብሔርና በአካባቢ ለመከፋፈል የሚሰሩ አካላትም ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ መንግስት አስጠንቅቋል።

#የመንግስት_ኮሚኒኬሽን

@tikvahethiopia