TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update በአፋር፣ በጋምቤላ እና በሶማሌ አካባቢዎች በአምስት ኩባንያዎች #ነዳጅ እየተፈለገ ነው፡፡ ኢትዮጵያ ነዳጅ እና የተፈጥሮ ጋዝ ለማምረት #ተስፋ ሰጪ ስራ እየሰራች መሆኗን የኢትዮጵያ የፔትሮሊየም ፈቃድ አስተዳደር ዳይረክቶሬት ዳይሬክተር ዶክተር #ቀጸላ_ታደሰ ተናግረዋል፡፡ኢትዮጵያ ባሳለፍናቸው ጥቂት ወራት ነዳጅ የማምረት ሙከራ ላይ ናት፡፡ ከዚህም በቀን ከ120 እሰከ 130 በርሚል ነዳጅ እየተመረተ መሆኑን የኢትዮጵያ የፔትሮሊየም ፈቃድ አስተዳደር ዳይሬክተር ዶክተር ቀጸላ ታደሰ ገልጸዋል፡፡

ምንጭ፦ የመንግስት ኮሚኒኬሽን
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ለገሀዲ ወረዳ🔝

‹‹አካባቢው ነዳጅ ካለ ይህ ዓይነት ምልክት ይታያል፡፡›› የማዕድንና ነዳጅ ሚኒስቴር

በደቡብ ወሎ ዞን ለገሂዳ ወረዳ እየታየ ያለው የነዳጅ ምልክት በአካባቢው ክምችት መኖሩን #ሊያረጋግጥ እንደሚችል የማዕድንና ነዳጅ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

በደቡብ ወሎ ዞን ለገሂዳ ወረዳ ‹‹የነዳጅ ምልክቶች›› የሚታዩበት ቦታ አለ፡፡ የአካባቢው ነዋሪዎችም መረጃው በሳይንሳዊ መንገድ እንዲረጋገጥ እየጠየቁ ነው፡፡ አብመድ ጉዳዩን ለማጣራት የማዕድን እና ነዳጅ ሚኒስቴር የስራ ኃላፊዎችን አነጋግሯል፡፡

በሚኒስቴሩ የፔትሮሊየም ፈቃድ እና አሥተዳደር ዳይሬክተር ዶክተር #ቀጸላ_ታደሰ ለአማራ ብዙኃን መገናኛ ድርጅት እንደተናገሩት መስሪያ ቤታቸው ጉዳዩን ያውቀዋል፡፡

በሥፍራው የነዳጅ ምልክት መኖሩ ከረጅም ዓመታት በፊት እንደሚታወቅ ነው ዶክተር ቀጸላ የተናገሩት፡፡ በአንድ አካባቢ ከሩቅ ቦታ ነዳጅ ካለ በመሬት ስንጥቆች መካከል እየሾለከ የመውጣት ዕድል እንዳለው የተናገሩት ዳይሬክተሩ ይህ ግን ምን ያህል ክምችት እንዳለ አያመላክትም ነው ያሉት፡፡ ዋነኛ የክምችት ቦታው የሚታወቀውም ጥልቅ እና ዝርዝር ጥናት በማካሄድ እንጂ በቀጥታ ምልክቶች የታዩበት ቦታ ላይ አለመሆኑንም ዶክተር ቀጸላ አስገንዝበዋል፡፡

ከዚህ በፊትም በስፍራው እና በአካባቢው ያለውን የነዳጅ ክምችት ለማወቅ ጥናቶች ሲካሄዱ መቆየታቸውም ታውቋል፡፡ ጥናቱንም ‹‹ፓልከን›› የተባለ የእንግሊዝ ኩባንያ ሲያካሂድ እንደነበር ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡ ኩባንያው ግን በገንዘብ ችግር ምክንያት ከአራት ዓመታት በፊት ጥናቱን አቋርጦ ወጥቷል፡፡ የመልከዓ ምድሩ አስቸጋሪነት፣ ዘርፉ ከፍተኛ ቴክኖሎጅ እና ገንዘብ የሚጠይቅ መሆኑ ‹‹ቀጣይ ጥናቶችን ማካሄድ ይገባል›› የሚል ድምዳሜ ላይ እንዳደረሳቸውም ነው የተናገሩት፡፡ በመሆኑም ለገሂዳ ላይ ያለው ዕውነታ በቀጣይ ጥናቶች የሚረጋገጥ መሆኑን ነው ዳይሬክተሩ ያረጋገጡት፡፡

በኢትዮጵያ ኦጋዴን ውስጥ‹‹ዶርካሌ›› ላይ እና በኦሮሚያ እና በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልሎች አዋሳኝ ደግሞ‹‹ገለምሶ›› ላይ ለገሂዳ ላይ ካለው ጋር ተመሳሳይ ዕውነታዎች መኖራቸውንም ዶክተር ቀጸላ አረጋግጠዋል፡፡

ምንጭ፦ አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia