TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update ኦሮሚያ ክልል⬇️

በተለያዩ የኦሮሚያ ክልል ከተሞች የሕግ የበላይነትን ለማስከበርና ሕገ ወጥነትን ለመከላከል በተሰራው ስራ የተለያዩ ሕጋዊ እርምጃዎች ተወስደዋል፡፡

#ሱሉልታ

በቄሮ ስም እንቅስቃሴ በማድረግ ሌሊት የግለሰቦችን ቤት በማፍረስና ቆርቆሮ በመውሰድ ላይ የተሰማሩ 4 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር
ውለዋል፡፡

#ሻሸመኔ

ባለፈው ሳምንት በከተማው የተፈጸመው ወንጀል እጃቸው አለበት ተብለው የተጠረጠሩ 7 ሰዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡

#ቡራዩ

የቄሮ አመራር ነኝ በማለት መታወቂያ አዘጋጅቶ የተለያዩ ተቋማት በግድ ስፖንሰር እንዲያደርጉት ሲጠይቅ የነበረ፣ ቲተር: ማዕተምና የመታወቂያ ወረቀት በቄሮ ስም አዘጋጅቶ በመሸጥ ሲነግድ የነበረ ተጠርጣሪ በቁጥጥር ስር ውሏል፡፡

#ለገጣፎ_ለገዳዲ

በቄሮ ስም የ62 ወጣቶችን ፎቶ በማሰባሰብና ወረቀት ላይ በመለጠፍ የቄሮ አደረጃጀት ከቀበሌ እስከ ላይ መኖር አለበት በሚል ወጣቶችን
ሲያታልሉና ሲያደረጁ የነበሩ 2 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡

#ጅማ

በሕገ ወጥ ስራ ላይ ተሰማርተው ሕገ ወጥ ግንባታ ሲያካሄዱ የነበሩ 42 ሰዎች በቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን፣ ከእነዚህ ውስጥ 8 ሰዎች ላይ ሙሉ መረጃ ተሰባስቦ ለሕግ ሊቀርቡ ነው፡፡
ድንገት በተደረገው ፍተሻም 2ሽጉጥና 180 ጥይቶች ተይዘዋል፡፡

#አዳማ

በቅርቡ በከተማው ለተከሰተው ግጭት መነሻ በመሆን ሰዎችን ሲያነሳሱ የነበሩና ግጭቱ የብሔር መልክ እንዲይዝ አድርገዋል የተባሉ 8 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡

#ሞጆ

ጨለማን ተገን በማድረግ ፋብሪካን ለመዝረፍ ሲንቀሳቁ የነበሩ 2 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን፣ በአንደኛው ግለሰብ እጅ ሽጉጥ ተይዟል፡፡

#ሰበታ

በሕገ ወጥ ግንባታ ላይ የተሰማሩ፣ ምግብ ቤት ገብተው በመመገብ ሒሳብ የማይከፍሉና ተደራጅተው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ 14 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡

ምንጭ:- የኦሮሚያ ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከ40 በላይ ክላሽንኮቭ መሣሪያዎች ተያዙ⬇️

ሐሙስ መስከረም 10 ቀን 2011 ዓ.ም. ከአዲስ አበባ ከተማ በስተሰሜን አቅጣጫ በአይሱዙ መኪና ተጭነው ወደ አዲስ አበባ ከተማ ሲገቡ የነበሩ ከ40 በላይ ክላሽንኮቭ መሣሪያዎች በቁጥጥር ሥር ዋሉ፡፡

መሣሪያዎቹ የተያዙት #ሱሉልታ ኬላ ላይ እንደሆነም ምንጮች ለሪፖርተር አስታውቀዋል፡፡

መሣሪያዎቹን ጭኖ ወደ አዲስ አበባ ከተማ እየገባ ሳለ በቁጥጥር ሥር የዋለው መኪና ሾፌር ሊያመልጥ ሲል የኦሮሚያ ክልል የፀጥታ አካላት በተሸከርካሪዎች መንገድ በመዝጋት በቁጥጥር ሥር ሊያውሉት ችለዋል፡፡

©ሪፖርተር
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጥቆማ‼️

#ሱሉልታ አካባቢ ላለፉት ሁለት እና ሶስት ቀናት የኔትዎርክ ችግር እንዳለ ነዋሪዎች ጠቁመዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ሱሉልታ

"ሱሉልታ መንገድ ውሀ ሞልቶ የገኛል በዚህ የተነሳ ለሰአታት ቆመናል።" #Sington #ETHIOPIA

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#attention

#ሱሉልታ ከተማ ዛሬም አለመረጋጋት ይታያል። መንገዶች ተዘግተዋል። በየአስፓልቱ የሚቃጠል ጎማዎችም ይታያሉ። መንግስት ለከተማይቱ ትኩረት እንዲሰጥ የቲክቫህ ሱሉልታ ቤተሰቦች አሳስበዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia