TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#EthiopiaAirlines

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለተከታታይ 4 ዓመታት የአለም አየር መንገዶች ብቃት መዛኝና ደረጃ መዳቢ በሆነው ስካይትራክስ የሚሰጠውን "የአፍሪካ ምርጥ አየር መንገድ ሽልማት" አሸነፈ።

ይህ ሽልማት በብዙዎች ዘንድ "የአቪየሽን ኢንዱስትሪው ኦስካር" በመባል ይታወቃል።

ምንጭ፦ የኢትዮጵያ አየር መንገድ

@tikvahethiopia
#EthiopiaAirlines🇪🇹

ኢትዮጵያ አየር መንገድ ፤ ከካርቱም ወደ አዲስ አበባ ሲበር የነበረ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የበረራ ቁጥር ET343 አውሮፕላን ነሀሴ 9 ቀን 2014 ዓ.ም ከአዲስ አበባ አየር ትራፊክ ቁጥጥር ጋር ያለው ግንኙነት ለጊዜው ተቋርጦ እንደነበር የሚጠቁም ሪፖርት እንደደረሰው አመልክቷል።

ሆኖም ግንኙነቱ ከተመለሰ በኋላ አውሮኘላኑ በሰላም እንዳረፈ ገልጿል።

ተጨማሪ #ምርመራ እስከሚያጠናቅቅ ጉዳዩ የሚመለከታቸው የበረራ ሠራተኞች ከሥራ ታግደው ይቆያሉ ብሏል።

በምርመራው ውጤት መሰረት ተገቢው የእርምት እርምጃ ይወሰዳል ያለው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ደህንነትን ማስጠበቅ  የሁልጊዜም የመጀመሪያው ተግባሩ ሆኖ እንደሚቀጥል አረጋግጧል።

@tikvahethiopia
የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ሐና አጥናፉ ለሪፖርተር ጋዜጣ የሰጡት ቃል ፦

" የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ኤርትራ በረራ እንዳያደርግ መታገዱን የሚገልጽ ደብዳቤ ደርሶናል።

ይህ ከመደረጉ ከሁለት ሳምንት በፊት ወደ ኤርትራ የምናደርገውን በረራ እንድናሳድ፣ የመጫን አቅማቸው ከፍተኛ የሆኑ አውሮፕላኖችንም እንዲጠቀም ተጠይቀን ነበር።

በረራ እንድናቆም የሚጠይቀው ደብባቤ ከመድረሱ ከሁለት ሳምንት በፊት ነው ፦
- የምናደርገውን በረራ ከ10 ወደ 15 እንድናሳድግ፣
- የምንጠቀመውን መለስተኛ አውሮፕላን ወደ ከፍተኛ አውሮፕላን እንድናሳድግ ፣
- በቀን ሁለት በረራ እንዲሁም በየሳምንቱ ዓርብ ሦስት በረራ እንድናደርግ ጠይቀውን የነበረው።

በረራ እንድናሳድግ የሚጠይቅ ደብዳቤና ፈቃድ በተሰጠን በሁለት ሳምንት ውስጥ አሁን በረራ እንድናቆም የሚገልጽ ደብዳቤ ደርሶናል።

ይህም ባልተገባ መንገድ በማኅበራዊ ሚዲያ እንዲሰራጭ መደረጉ አስገራሚና አስደንጋጭ ነው።

ወደ ኤርትራ የሚያደርገው በረራ ከመስከረም 30 / 2024 ጀምሮ እንድናቆም በሚያሳውቀው ደብዳቤ ላይ በረራው እንድናቆም የተወሰነበት ምክንያት ደብዳቤው ላይ አንዳችም ቦታ አልተገለጸም።

በማኅበራዊ ትስስር ገጾች እየተዘዋወረ የሚገኘው ደብዳቤ ለኢትዮጵያ አየር መንገድ የተላከ ባለመሆኑ፣ በደብዳቤው ላይ ለተዘረዘሩት ጉዳዮች ምላሽና አስተያየት መስጠት አንፈልግም።

በጉዳዩ ዙሪያ ከኤርትራ ሲቪል አቪዬሽን ጋር ለመነጋገር እንሞክራለን። "

#EthiopiaAirlines🇪🇹

@tikvahethiopia